TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ጣሊያን የቀበረው ወርቅ አለ ተብሎ የተቆፈረው ጉድጓድ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል፡፡ #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ ተጨማሪ ጉማሬዎች ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ስጋት መኖሩ ተነገረ፡፡ እንስሳቱ በበሽታ #እንዳልሞቱም ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትናንት በንፋስ ስልክ ወረዳ ሁለት በሚገኝ የወታደሮች መኖሪያ ግቢ በተነሳ እሳት ቃጠሎ ጉዳት መድረሱን ሸገር ዘግቧል፡፡ በአደጋው የአንዲት ሴት ሕይወት ጠፍቷል፤ 3 ሰዎች ቀላልና ከባድ መቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ 13 መኖሪያ ቤቶችም ተቃጥለዋል፤ በጠቅላላው 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ተብሏል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ-ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 21 የስራ አስፈጻሚ አባላትን መምረጡን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡ በመንግስት ትይዩ በተዋቀረው ስራ አስፈጻሚ ውስጥ የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ምክትል መሪው አንዷለም አራጌን ጨምሮ 7 ሰዎች በአባልነት ተካተዋል፡፡ የፓርቲውን የዕለት ተዕለት በሚከታተለው ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ደሞ የፓርቲው ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ፣ ምክትላቸው ጫኔ ከበደ፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ዋሲሁን ተስፋዬን ጨምሮ 14 የፓርቲው አባላት ተመርጠዋል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopi
“የቻላችሁትን ያህል ክፍሉ…”

“በዚህች ምድር ለብቻችን አይደለም የምንኖረው፤ አንዳችን ለሌላችን እንደምንኖር ነው የማምነው፡፡ ስለዚህም ማንም ቢሆን… የገቢ መጠኑ የቱንም ያህል ይሁን መሰረታዊ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት አለበት ብዬ ነው የማምነው” ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ…

“10 ራንድም የሚከፍል አለ፤ 500 ራንድም የሚከፍል እንደዛው፡፡ ሁሉም ሕክምናውን ካገኘ በኋላ የቻለውን ይከፍላል” ይላል ደቡብ አፍሪካዊው ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ፡፡

ዶ/ሩ የዛሬ አራት ሳምንታት ግድም፣ በደቡብ አፍሪካዋ ብሎምፎንቲየን ከተማ የከፈተው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒኩ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

የዚህ ምክንያቱ ደግሞ … ወደ ክሊኒኳ ያለ ቀጠሮ ዘው ብለው ገብተው፣ ሕክምናዎትን አግኝተው ሲያበቁ የሚከፍሉት “የቻሉትን ያህል” ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ በቀን 20 ያህል በሽተኞችን የሚያክመው ዶ/ሩ የታካሚ ቁጥር እንደጨመረ ይገልፃል፡፡ዶክተሩ፣ የሕክምና አገልግሎቱን እና መሰረታዊ የሚባሉ መድሃኒቶችን ለሕመምተኛው ከሰጠ በኋላ ታካሚው የሚችለውን ከፍሎ ይሄዳል፡፡

“ይህ አሰራር ያዋጣሃል ወይ” ተብሎ የተጠየቀው ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ፣ “ኑሮዬን በገቢዬ መጠን አደርገዋለሁ፡፡ ደግሞም … እኔ ዶክተር ነኝ፤ የእኔ ሃላፊነት የሕክምና አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ሃላፊው እግዚአብሄር ነው” ብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገባው … ዶ/ሩን ለመርዳት ገንዘብ የሚያሰባስቡ ሰዎች እየመጡ ነው፡፡

ምንጭ - ቢቢሲ/#ሸገርFM
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮቴሌኮም ለደምበኞቹ በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ነፃ አገልግሎት እሰጣለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ዛሬ የሚጀምረውን አዲስ የበጀት አመት አስመልክቶ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡ በመሆኑም የኢትዮቴሌኮም ደምበኞች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ 1 ጊጋባይት ኢንተርኔት፣ 20 ደቂቃ የሐገር ውስጥ የስልክ ጥሪ እንዲሁም 30 የሐገር ውስጥ አጭር የፅሁፍ መልዕክት በነፃ መጠቀም ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ አገልግሎቱንም ከዛሬ ሐምሌ 1 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2011 ድረስ መጠቀም እንደሚቻል ተሰምቷል፡፡

Via #ሸገርFM
🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተደራጅታችሁ በሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ ብንባልም እስካሁን #መመሪያ ስላልተዘጋጀ ስራ ፈትተናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናገሩ፡፡ አስተዳደሩም መመሪያው #በቅርቡ ይወጣል ብሏል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia