TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል‼️

በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ጠዋት ላይ በደረሰ #የመኪና_አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር #አባሃጅ_ጉጆ እንደገለጹት የካቲት 19/2011 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ላይ በአርባምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 53362 ኢት የሆነ ሲኖ ትራክ መኪና እና ኮድ 4-15376 ኢት የሆነ ፒካፕ መኪና ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረክሩ በተፈጠረ አደጋ እስከ አሁን የ5 ሠዎች ሕይወት አልፏል፡፡

በቦታው ከነበሩ አይን እማኞች በተገኘ መረጃ አደጋው የተፈጠረው በፍጥነት ሲያሽከረክር የነበረው የሲኖ ትራክ አሽከርካሪ ባለ 3 እግር ባጃጅን ለማትረፍ የቀኝ መስመሩን ትቶ ወደ ግራ በመታጠፍ ፒካፕ መኪናን በመግጨት ከመስመር ያስወጣው ሲሆን በእግረኛ መንገድ ስትጓዝ የነበረች የ13 ዓመት ሕጻንን ጨምሮ በፒካፕ መኪናው ውስጥ የነበሩ 3 ተሳፋሪዎች ሕወታቸው አልፏል፡፡

ይሕ በእንዲህ እንዳለ የሲኖ ትራክ አሽከሪው #በፀፀት ራሱን ከመብራት ታዎር ላይ በመጣል ሕይወቱ ማለፉን ም/ኢንስፐክተር አባሃጅ ገልጸው በአደጋው ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

አሽከርካሪዎች ከተፈቀደ ፍጥነት ወሰን በላይ ባለማሽከርከር በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ #መቀነስ እንደሚጠበቅባቸው የከተማው ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር አባሃጅ ጉጆ አሳስበዋል፡፡

Via Gamo Zone Administration public Relation office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጣልያን የሟቾች ቁጥር መቀነስ አሳየ!

በጣልያን የሟቾች ቁጥር #መቀነስ አሳይቷል። በ24 ሰዓት የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 727 ሲሆን ባለፉት 6 ቀናት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ነው።

በሀገሪቱ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች 110,574 የደረሱ ሲሆን፤ 13,155 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። 16,847 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው!

በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱማሊያ ፣ ሱዳናና ጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

ከዚህ ቀደም በጎረቤቶቻችን ሀገራት ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ስንቆጥር እንዳልነበር አሁን ሟቾችን ወደ መቁጠር እየተሸጋገርን ነው።

በሩቅ ሀገራት ስንሰማ የነበረው አሳዛኝ የሞት ዜና እኛም ጋር እየቀረበ ያለ ይመስላል። ኮቪድ-19 አይገልም የሚባለውም ስህተት መሆኑን ተመልክተናል።

በእርግጥ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተይዘው ከሚሞቱ ሰዎች ይልቅ የሚያገግሙት ይበልጣሉ። ግን ለምን የ1 ሰው ህይወት ከጥንቃቄ ጉድለት ይጠፋል ? ለምን በቸልተኝነት ሊተካ የማይችለው የሰው ልጅ ህይወት ያልፋል ? ሁላችንም ልንመልሰው የሚገባ ጥያቄ ነው።

'የጤና ባለሞያዎችን' ምክር የምንሰማ ከሆነ ይህ ወረርሽኝ መፍትሄ እስኪያገኝለት ድረስ ጉዳቱን በእጅጉ #መቀነስ እንችላለን። ጦርነቱ የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን መደማመጥ ከቻልን ማሸነፋችን አይቀርም!

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia