TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን 96 ሰዎች መገደላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል #ዘይኑ_ጀማል ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት ቀውሱ በተነሳበት የመጀመርያው ቀን #ሐምሌ 27፣ 2010 ዓ. ም. ሲሆን፤ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች #ግድያው መፈጸሙን ተናግረዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት #በአሰቃቂ ሁኔታ መሆኑን ተናግረው፤ ሀይማኖትና ብሔርን ለይቶ የተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነ አክለዋል።

"ከዘር #ጭፍጨፋ አይተናነስም" ብለዋል። መነሻው የክልሉ አመራሮች አቅደው፤ ተግባሩን የሚፈጽሙ ሰዎች አሰልጥነውና አሰማርተው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

እስከ አሁን የክልሉን የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኡመርን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

'ሄጎ' በመባል የሚታወቀው ቡድን በግድያው እጁ ስለመኖሩ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ "በዋናነት በግጭቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት #ሄጎ በሚባለው ቡድን አባላት ናቸው። ሄጎ የሚባለውን #የፈጠሩ፣ እቅዱን ያቀነባበሩ የክልሉ የፖለቲካ #አመራሮች፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ #ባለስልጣኖችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየሰራን ነው" ብለዋል።

ልዩ ፖሊስ በግድያው ተሳትፎ ስለመሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ማን በምን ደረጃ ተሳተፈ የሚለው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል" ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በጅግጅጋ የሚኖሩ የተለያዩ አካባቢዎች ተወላጆች ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ጄኔራል ዘይኑ፤ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት የክልልሉን ዋና ዋና ከተማዎች መቆጣጠሩ አንጻራዊ ሰላም ማስፈኑን ገልጸዋል።

በአሁን ወቅት አዲሱ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ አካባቢው መመለስ ቀጣዩ ስራ መሆኑን ተናግረው፤ በዚህ ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ እየተባበራቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሻሸመኔ⬇️

በሻሸመኔ ከተማ ሰው በመግደልና ዘቅዝቆ በመስቀል ወንጀል የተጠረጠሩ 14 ግለሰቦች በቁጥጥር ስል አውሎ በስድስቱ ላይ #ክስ እንደሚመሰርት የከተማው ፓሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ ነሃሴ 6 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር አቶ #ጃዋር_መሀመድ አቀባበል ስነ ስርዓት ላይ ግርግር በመፍጠር አንድ ግለሰብን #በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ በመስቀል ወንጀል ጠርጠራቸውን የአቃቤ ህግ መዝገብ ይጠቁማል።

የከተማው ፓሊስ መምሪያ አዛዝ ኮማንደር መኮንን ታደሰ ለጣቢያችን እንዳሉት፥ ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል በስድስቱ ላይ አቃቤ ህግ ክስ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ በማግኘቱ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን  ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት እንደሚቀርቡም አስታውቋል።

ነሃሴ 6 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት በተፈጠረው ግርግርና ግፊያ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የከተማው ፓሊስ ተሽከርካሪ ቃጠሎ እንደደረሰበት ይታወሳል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣቷን #በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ #ሞት ተፈረደበት‼️
.
.
አንዲት ወጣት ላይ አሰቃቂ ግድያ ፈፅሟል ያለውን ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ፍርድ ቤቱ ቅጣቱ የወሰነው በሐረማያ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ በሆነው #ጫላ አህመድ ሙመድ የተባለው ግለሰብ ላይ ነው።

የፍርድ ቤቱ ዳኛ አቶ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በግለሰቡ ላይ ቅጣቱን የወሰነው በቤት ሠራተኝነት ሕይወቷን ትመራ የነበረች ወጣትን በግፍ መግደሉ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት ነው።

ሟች በአወዳይ ከተማ ከባለቤቷ ጋር ተጋጭታ በሐረር ከተማ በቤት ሠራተኛነት ስትሰራም ነበር።

“ግለሰቡ ወጣቷን ለትዳር እንደሚፈልጋት በመግለፅ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት በመውሰድ ከአቅም በላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከፈፀመባት በኋላ ጆሮዋ አካባቢ እንደመታትና አንቆ እንደገደላት ታውቋል” ብለዋል።

“ወጣቷ ላይ ግድያ ከፈፀመ በኋላ ቤቱ ቆልፎባት ጠፍቷል” ያሉት ዳኛው፣የቤቱ ባለቤቶች ግለሰቡ በመጥፋቱ መጋቢት 24 ቀን 2010 ቤቱን ለሌላ ግለሰብ ለማከራየት ፈልገው በሩን ሲከፍቱ አስከሬኑን እንዳገኙት አስረድተዋል።

“የተዘጋውን በር ሲከፍቱ ያልጠበቁት መጥፎ ጠረን ያጋጠማቸው አከራዮች ዘልቀው ሲገቡ በቤቱ ወለል ላይ የፈረሰ የወጣቷን አስከሬን አግኝተነዋል” ሲሉም አብራርተዋል።

የሐረማያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወንጀሉ ወደ ተፈፀመበት ቤት በማምራት አስከሬኑን ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ ከተደረገለት በኋላ መቀበሩን ተናግረዋል።

“ግለሰቡ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የወሲብ ጥቃት ይፈጽሟል በሚል ጥርጣሬ በመኖሪያ ቤቱ በተደረገ ፍተሻ የሟች አልባሳት፣ የተለያዩ ሴቶች ፎቶግራፎች፣ ማሰቃያ ሰንሰለትና ሌሎች ወንጀል መፈፀሚያ ቁሶች ተገኝተዋል” ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ የቀረቡለትን የሕክምናና የሰው ማስረጃዎች በመመልከት ቅጣቱን መበየኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሻሸመኔ ከተማ ተካሂዶ በነበረው ህዝባዊ የአቀባበል ስነስርዓት ጊዜ #በአሰቃቂ ሁኔታ የሰው ህይወት አጥፍተዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ።

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #መኮንን_ታደሰ ለሸገር ራድዮ እንደተናገሩት በሻሸመኔ በነበረው ህዝባዊ የአቀባበል ስነ ስርዓት ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ የአንድ ሰው ህይወት አጥፍተዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ ሰሞኑን እያንዳንዳቸው በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል ብለዋል። ኮማንደር መኮንን ውሳኔውን ያሳለፈው የምዕራብ አርሲ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሆነም ተናግረዋል።

በሻሸመኔ ከነበረው ህዝባዊ የአቀባበል ስነ ስርዓት ጋር በተገናኘ የሰው ህይወት አጥፍተዋል ንብረትም አውድመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 16 ሰዎች ተይዘው እንደነበር በምስክር #መጥፋትም አስሩ ተለቀው ስድስቱ ተጠርጣሪዎች እንደቀሩ ሸገር በዘገባው አስታውሷል።

Via Shger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ...

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ተማሪ ሞት የተጠረጠሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ ዓርብ ግንቦት 16/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ምንጩ ያልታወቀ ጥቃት በተማሪዎች ላይ ደርሷል ብሏል።

ጥቃቱ ከተለመደው የተማሪ #ፀብና #ግርግር ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሲሆን፥ ጩኸትና ግርግር የማይታይበት ተማሪዎችን #በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የሚያደርስ ነበርም ነው ያለው።

ጥቃት አድራሾችም ፊታቸውን በመሸፈናቸው በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ነበር ያለው ዩኒቨርሲቲው፥ ሆኖም ግን አርብ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከግቢ ወጥተው ወደ ጫካ ሲገቡ በማህበረሰቡ ጥቆማ የተወሰኑትን የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር አውሏቸው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ስለ ችግሩ እና ስለ ቀጣይ የተማሪዎች ሰላም ተወያይተዋል። ድርጊቱን ያወገዙት ተወያዮቹ ችግር ፈጣሪዎቹን በማጋለጥ ለፀጥታ አካላት እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ተማሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው በውይይቱ ላይ የተገለፀው።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም የክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ #ተመራቂ ተማሪ ላይ በደረሰዉ የሕይወት መጥፋት ከልብ ማዘኑን በመግለፅ ድርጊቱን አጥብቀው #እንደሚያወግዙት ገልጿል።

የክልሉ መንግሥት ከሕዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለሕግ እንደሚያቀርብ ማስታወቁንም ነው አብመድ የዘገበው።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው የሀዘን መግለጫም በደብረማርቆስ ዩንቨርሲቲ ተማሪ በነበረው ወጣት ሰዓረ አብርሃ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉ #ጥልቅ_ሃዘን ገልጿል።

ጉዳዩን በአፅንኦት እየተከታተለው እንደሚገኝ የገለፀው የክልሉ መንግስት፥ ወንጀለኞች ወደ ህግ እንዲቀርቡ እና አስፈላጊዉ ፍርድ እንዲያገኙ ከሚመለከተዉ አካል ሆኖ እንደሚሰራ በመግለፅ ለሟች ቤተሰብ፣ ወዳጅና ዘመድ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia