TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.35K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፍቅር ከሌለህ የከንቱ ከንቱ ነህ!!

"እውነተኛ #ፍቅር ቀለም፣ ብሄር፣ ጎሳ፣ ክልል፣ ዜግነት፣ ሀገር፣ የኑሮ ደረጃ... አይመርጥም ሁሉንም #ያቅፋል፤ ሁሉንም #ይስማል!"
.
.
እውነተኛ ፍቅር በውስጥህ ሳይኖር ስለሰው ልጅ ክቡርነት ሳትረዳ ስለብሄር፣ ጎሳ፣ ክልል፣ ሀገር፣ ባንዲራ ብታወራ የከንቱ ከንቱ ነህ እልሃለው። አጠገብህ ያሉትን ወንድሞችህንና እህቶችህን ወደው ባላመጡት ብሄራቸው እየለየህ #እያቋሸሽክና #እየሰደብክ፤ እያሳደድክና እያዋረድክ፤ እየገደልክ እና እያፈናቀልክ ስለዴሞክራሲ እየታገልኩ ነው፤ ስለብሄሬ እና ማንነቴ እየታገልኩ ነው ብትል የ ዓለም #ማፈሪያ እልሃለሁ።
.
.
እውነተኛ #ፍቅር ቀለም፣ ብሄር፣ ጎሳ፣ ክልል፣ ዜግነት፣ ሀገር፣ የኑሮ ደረጃ... አይመርጥም ሁሉንም #ያቅፋል፤ ሁሉንም #ይስማል!
.
.
ዶክተር አብይን #ማድነቅ እና #መስማት፤ መደገፍ እና መከተል ብቻ በቂ አይደለም የሚሰራውን እያዩም መማር ትልቅነትና አዋቂነትም ጭምር ነው!

🔹ፀጋአብ ወልዴ ኢትዮጵያ🔹
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊1