TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Italy #Russia #COVID19

ሩስያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ በብርቱ እየተጠቃች ያለችውን ጣልያንን ለመደገፍ ሐኪሞችን እና የህክምና ቁሳቁስ እየላከች መሆኗን አስታውቃለች።

ሩስያ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችዉን ጣልያንን ለመደገፍ በዘጠኝ የጭነት አውሮፕላኖች የሕክምና ባለሞያዎች እና ቁሳቁስ ወደስፍራው ለማጓጓዝ በችካሎቭስኪ ወታደራዊ ሰፈር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጻለች።

በተልዕኮው ስምንት (8) ተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድኖችን ጨምሮ የሕክምና ቁሳቁስ እና የጸረ ቫይረስ [COVID-19] ርጭት ተሽከርካሪዎች ያካተተ መሆኑን ተገልጿል።

#AFP #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy

በየዕለቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሚረግፉባት ጣልያን የ101 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ አዛውንት ከሪሚኒ ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ITALY

የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው ቀንሷል። ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 606 ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 17,127 ደርሷል።

በሌላ በኩል በጣልያን ተስፋ ሰጪ ምልክቶች እየታዩ ነው። አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ባለፉት 24 ሰዓት ሪፖርት የተደረገው 3,039 ኬዝ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት በጣልያን ፦

- የሟቾች ቁጥር ቀንሷል።
- አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችም ቀንሷል።
- የፅኑ ህሙማን ቁጥር ቀንሷል።
- ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የሚወጡ ጨምረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy

በሮም የኢፌዴሪ ሚሲዮን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከ03/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በሳምንት ሁለት (2) ቀን ብቻ ተወስኖ የቆየው የቆንስላ አገልግሎት ከ10/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ #መደበኛ ስራውን የሚጀምር መሆኑን ገልጿል። የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከአስፈላጊ ጥንቃቄ ጋር እንዲሆንም #ማሳስቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy #Ethiopia

#ጣሊያን እና #ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል የጤና ስርዓቱን ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

" በኦሮሚያ ክልል የጤና ስርዓትን ማጠናከር " የተሰኘው ይኸው ፕሮጀክት የጤና ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት፣ የእናቶችና ህፃናት አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እና ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር የተያያዙ ተግባራትን መደገፍ ያለመ ነው።

በተጨማሪ ፕሮጀክቱ የሎጂስቲክስ አስተዳደርን ማጠናከር ፣ የመረጃ ሥርዓቱን እና የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (CBHI) ልማትንም ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Africa-Italy የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ጣልያን፣ ሮም ገብተዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ሮም ይገኛሉ። የሀገራት መሪዎች ፣ እና የመንግሥታት ተወካዮች በሮም እየተሳብሰቡ የሚገኙ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ዛሬ እና ነገ ለሚካሄድ የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ነው። የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ…
ፎቶ ፦ የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በጣልያን፣ ሮም ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የበርካታ ሀገራት መሪዎችና የመንግስት ተወካዮች ጉባኤውን እየተካፈሉ ይገኛሉ።

በዚህ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙት መሪዎች መካከል፦
* የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣
* የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
* የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
* የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ይጠቀሳሉ።

የሁለት ቀኑ የአፍሪካ-ጣሊያን የመሪዎች ጉባኤ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በኢኮኖሚና መሰረተ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢነርጂ ደህንነት እና ሽግግር እንዲሁም በሙያ ስልጠናና በባህል ዘሪያ እኩል አጋርነትን መፍጠር ላይ ያተኩራል።

#Africa #Italy

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Italy

ኢትዮጵያ ዛሬ ከጣሊያን ጋር የ25 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት እንደተፈራረመች ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

13 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ በድጋፍ መልክ ሲሆን 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ብድር ነው፤ ይህም ለአካባቢና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ይውላል ተብሏል።

በተጨማሪም ስምምነቱ የ ' ገበታ ለትውልድ ' ን እንደሚደግፍ ገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል።

@tikvahethiopia