TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የውጭ ባለሃብቶች በኮንዶሚኒየምና ሪል እስቴት ቤቶች ግንባታ ዘርፍ እንዲሳተፉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ያቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንደገና እንዲታይ ገንዘብ ሚንስቴር ወስኗል፡፡ እንደ ካፒታል ዘገባ በዘርፉ የውጭ ኩባንያዎች መሳተፋቸው ለዜጎች ሥራ ፈጣሪ አይሆንም፤ መንግሥትንና የቤት ገዥዎችንም ከፍተኛ ወጭ ይጠይቃል- ብሏል ገንዘብ ሚንስቴር፡፡ ሃሳቡ ቢያንስ ለ3 ዐመታት እንደገና እንዲጠናም አሳስቧል፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር መነሻ ሃሳብ የሀገር ወስጥ ባለሃብቶች ለቤት ግንባታ በቂ የገንዘብ አቅም የላቸውም የሚል ነው፡፡

Via #CAPITAL
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እፀገነት አንተነህ⬆️

"የ27 አመቷ የአየር መንገድ ሒሳብ ሰራተኛ እፀገነት አንተነህ ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ወደ ሰራ በምታመራበት ወቅት #ጭካኔ በተሞላበት ወንጀል አቃቂ መንገድ ላይ ተገድላ ተጥላ ተገኘች። ፓሊስ ምርመራ ላይ ነው። ቀብሯ ዛሬ ተፈፅሟል። ቀለበት አድርጋ ሰርግ ለመደገስ ዝግጅት ላይ ነበረች።" ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት/#CAPITAL/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም - ኢትዮጵያ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሥራ እንደሚጀመር አሳውቋል።

የድርጅቱ የቁጥጥር እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ከመንግስት ጋር ያላቸው ስምምነት እንደሚያሳየው ፍቃድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በዘጠኝ ወር ወደ ስራ መግባት እንደሚኖርባቸው ገልፀው ከመጪው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በይፋ የንግድ ሥራ ለመጀመር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው ይህን የገለፁት ለካፒታል ጋዜጣ ነው።

እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 9፣ 2021 ጀምሮ የሚቆጠር የመሥሪያ ፍቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የቴሌኮም ማስፋፊያ ስራዎችን ጀምሯል።

ባለፈው ወር የኩባንያው የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከል ስራ የጀመረ ሲሆን ኩባንያው የኔትወርክ ዝርጋታውን እየሰራ ነው።

ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ሳፋሪኮም ከ2 የኔትወርክ አቅራቢዎች ኖኪያ እና ሂዋዌ ጋር እየሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በአዲስ አበባ እና አካባቢው ያለውን የኮር ኔትወርክ መሠረተ ልማት በኖኪያ ኩባንያ እንደሚሰራ ሁዋዌ ቀሪውን የአገሪቱን ክፍል እንደሚሸፍን አስረድተዋል።

" የመሰረተ ልማት መጋራት በተመለከተም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እስካሁን በድርድር ደረጃ ላይ ነን " ሲሉም አክለዋል።

ከመሰረተ ልማት ጎን ለጎን የሳፋሪኮም ደንበኞች እና የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች እንዲገናኙ ለማድረግ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልፀዋል።

#Capital_Newspaper

@tikvahethiopia
#የውሃ_ዋጋ 📈

🔹" በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም " - ውሃ አምራች ኩባንያዎች

🔹" ከአከፋፋዮች የሚሸጥልን ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል " - ነጋዴዎች

🔹" የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲቀርብ ጭማሪ ተደርጓል " - አከፋፋዮች

▪️ የታሸገ ውሃ አከፋፋዮች ምን ያህል ዋጋ ነው የጨመራሁት ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ዋጋውን ከመናገር ተቆጥበዋል።

በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ከሰሞኑ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።

በታሸጉ የፕላስቲክ ጠርሙስ ዉሃ ምርቶች ላይ የተደረገዉ የዋጋ ጭማሪ ከጥሬ ዕቃ መወደድ ጋር የተያያዘ መሆኑ አምራቾች ሲገልፁ በአንድ በኩል ደግሞ ከአከፋፋዮች የምንረከበዉ ምርቶች ላይ ጭማሪ በመደረጉ ነዉ ሲሉ ነጋዴዎች ተናግረዋል።

በተለይ ከሶስት ሳምንታት ወዲህ በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሲሸጡ ከነበረበት ዋጋ ላይ በእያንዳንዱ ምርት የ5 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ካፒታል ጋዜጣ አደረኩት ያለውን ቅኝት ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

የዋጋዉን ጭማሪ አስመልክቶ ማን ምን አለ ?

#አምራች_ኩባንያዎች ፦ ጭማሪው ከጥሬ እቃ መወደድ እና በቅንጦት እቃዎች ላይ በሚጣለዉ ኤክሳይስ ታክስ ሳቢያ መሆኑን አንስተዋል። ቢሆንም ግን በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም ሲሉ አሳውቀዋል።

" በሁሉም ምርቶች ላይ ከአንድ ብር በላይ ጭማሪ አልተደረገበትም " የሚሉት የዉሃ አምራች ፋብሪካዎቹ ነገር ግን በገበያ ላይ የሚሸጥበት ዋጋዉ ከእነርሱ እዉቅና ዉጪ መሆኑን አስረድተዋል።

#ነጋዴዎች ፦ ከዚህ ቀደም ሲረከቡበት የነበረዉ የዋጋ ተመን ላይ ጭማሪ መደረጉን ገልፀዉ ከአከፋፋዮች የሚሸጥላቸዉ ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።

#አከፋፋዮች ፦ የዋጋዉ ጭማሪ ከፋብሪካዎቹ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲያቀርብ ጭማሪ ማድረጋቸዉን ተናግረዋል። ምን ያህል እንደሆነ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ የዉሃ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ መርዕድ ፤ የዋጋዉ መጨመር መኖሩን አረጋግጠዋል።

ለዚህ በምክንያትነት ያነሱት " ፕላስቲክ ጠርሙሶቹ የሚሰሩት ከነዳጅ ተረፈ ምርት በመሆኑ የነዳጅ ምርቶች በጦርነቱ ሳቢያ ሊጨምር በመቻሉ ፣ ኤክሳይስ ታክስ ከፍተኛ መሆን ፣ ለአምራቾቹ ለስራ ማስኬጃ የብድር እጥረት መኖር ዋነኛዎቹ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

በገበያ ላይ ያለዉ የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግበት ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበዉ ምላሻቸዉን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

Credit - #CAPITAL #ካፒታል_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#አህያ🫏

በአዲስ አበባ ከተማ ከተለመደው " የከብት ስጋ ውጪ ህገወጥ እርድ እየተፈፀመ ነው " የሚል ጥርጣሬን ተከትሎ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ማሳወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

ህገወጥ እርድ የሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚጣለው ቅጣት መሻሻሉንም ባለስልጣኑ የገለፀ ሲሆን ህገወጥ እርድ የሚፈፀም ወይም የሚያቀርብ ማንኛውም አካል እስከ 15ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት አመልክቷል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፤ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚደረግን ህገወጥ እርድ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጋር በመሆን ህገወጥ እርድን የመቆጣጠርና የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ፤ ከእንስሳት ዝውውር፣ ግብይትና ዕርድ ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦች ተሻሽለዋል ፤ ደንቦቹን ተላልፈው የተገኙ አካላትም እስከ 15 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲል ገልጿል።

ከህገወጥ ዕርድ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ በከተማዋ ከተለመደው የከብት ስጋ ውጪ እየተሸጠ ተድርጎ ቢወራም  ከዚሁ ጋር  ተያይዞ ባለስልጣኑ ምንም ጥቆማ እንዳልደረሰው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል።

ነገር ግን ባለስልጣኑ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው እንደሆነ አስታውቋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ በ119 ወረዳዎች እንዲሁም በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለባለስልጣኑ የደረሰው  ጥቆማ አለመኖሩን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የስጋ ነጋዴዎች " የአህያ ስጋ በአዲስ አበባ እየተሸጠ ነዉ " በሚል ምክንያት የቀድሞ ገበያችን በከፍተኛ ደረጃ ተቀዛቅዟል ሲሉ ለ ' ካፒታል ጋዜጣ ' ተናግረዋል።

" በኢትዮጵያ ከተሞች በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ የአህያ ስጋ ለምግብነት እየቀረበ ነዉ " በሚል ተሰራጭቷል በተባለው መረጃ ሳቢያ የዕለት ገበያቸዉ ከቀድሞ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ " ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ ከገበያዉ እንድንወጣ ሊያደርገን ይችላል " ብለዋል።

" አሁን እስከ 80 ሺህ ብር የተገዛው ሰንጋ በሬ ወደ ተጠቃሚዎች በሚቀርብ ጊዜ የአህያ ነዉ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እናስተናግዳለን " በዚህ ምክንያት ሳይሸጥ የሚያድርበት ቀናቶች በርካታ ናቸዉ " በማለት ተናግረዋል።

ከገቢ አንፃር ምን ያህል አጣችሁ ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸዉ ሁለት የስጋ ሽያጭ ሉካንዳ ቤቶች "ከገቢ አንፃር ብቻ ሳይሆን በፊት ለገበያ የምናቀርበው ሁለት ሰንጋ ከብቶች በህጋዊ መንገድ በቄራ እርድ ተፈፅሞ ቢሆንም አሁን ግን አንዱን በትግል ነዉ የምንጨርሰዉ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሁኔታዉ አሳስቦናል ያሉት የስጋ ነጋዴዎቹ  ከገቢ አንፃር ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነዉን ማጣታቸዉን ለ 'ካፒታል ጋዜጣ' ገልጸዋል።

ከሰሞኑን፤ 'ብሩክ ኢትዮጵያ' የተሰኘ የአህያ መብት ተሟጋች ተቋም በኢትዮጵያ በመንግስት ዕውቅና ተሰጥቶት ስራ የጀመረው የአሰላ የአህያ ቄራ ምንም እንኳን ለውጭ ገበያ ታስቦ ቢከፈትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሰላ አካባቢ ያሉ ስጋ ቤቶችም ስጋውን ለሽያጭ ሲያቀርቡ እንደተገኙ ተናግሯል።

በአህያ ቆዳ ንግድ ሳቢያ አህዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ መመናመን እየታየ ነው ብሏል።

በመንግስት እውቅና የተሰጠው የአሰላ የአህያ ቄራ በቀን ከ100 - 300 አህዮች ለእርድ ያቀርባል፤ በዚህ የተነሳ ከዚህ ቀደም ከ2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው አህያ አሁን ከ9,000 እስከ 11,000 ብር እየተሸጠ ነው ተብላል።

ለቻይና ባሕላዊ ሕክምና እና ለኮስሞቲክስ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ጄልቲን ‘ኢጂአኦ’ ለማምረት የአህያ ቆዳ ተፈላጊ እንደሆነ ይነገራል።

Credit - #Capital #EthioFM

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" ከነገ ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት 5 ሺህ ብር ፈጣን ደግሞ 25 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት 5 ሺህ ብር የሚጠይቅ ሲሆን ፣ ፈጣን ፓስፖርት ለማግኘት ደግሞ 25 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል ብሏል።

ጭማሪው ከነገ ከነሐሴ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይጀመራል።

አገልግሎቱ ለአዲስ ፓስፖርትና ለእድሳት 5 ሺህ ብር፣ አስቸኳይ በ2 ቀን የሚደርስ 25 ሺህ እንዲሁም በ5 ቀን ደግሞ 20 ሺህ ብር መሆኑን ገልጿል።

የጠፋ ፖስፖርት ለማግኘት ተገልጋዮች 13 ሺህ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

#Capital #Ethiopia #ImmigrationandCitizenshipServices

@tikvahethiopia