TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ?

ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱና የክልሉ አስተዳደራዊ ወሰን እንዲከበር ጠይቀዋል።

በጥቅሉ ያነሷቸው ጥያቄዎች  ምንድናቸው ?

- የመከላከያ አባላት የነበሩት ጨምሮ ሌሎች የፓለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤
- የትግራይ ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት የወሰዱት የብድር ወለድና ቅጣት ይነሳ፤
- የመንግስት ሰራተኞችና የጡረተኞች ውዙፍ ደመወዝና አበል ይከፈል፤
- ከትግራይ ሰራዊት (TDF) ለተሰናበቱ ታጣቃዊች ማቋቋምያ ይከፈል፤
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር፤
- ከረሃብ ጋር በተያያዘ እርዳታ ይደረግ ፤
- የህወሓት የህጋዊነት ጥያቄ ለምን ዘገየ ?
የሚሉና ሌሎች ይገኙባቸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምን መለሱ ?

ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ ብዙ ስኬቶች እንዳሉ አሁንም ግን የሚቀር ብዙ እንዳለ ገልጸዋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በጥይት ሰው እንዳልሞተ ተናግረዋል። በትግራይ መረጋጋት ፤ መንግሥት መመስረት ፣ ህወሓት (TPLF) ከሽብርተኝነት መፋቅ የስምምነቱ ውጤት ነው ብለዋል።

ከስምምነቱ በኃላ በርካታ ቢሊዮን ብሮች በካሽም በቁሳቁስም ወደ ትግራይ ክልል መላኩን ገልጸዋል።

እስረኞችን መፍታት በተመለከተ ፦

" ስብሃትን ፈትቼው የለም እንዴ ? ፣ አልፈልግም እንዲታሰሩ።

የመከላከያን በተመለከተ እራሱ ይነግራችኋል (ዶ/ር አብርሃምን ማለታቸው ነው) አላውቅም በእኔ እውቀት #አንድም_የታሰረ_ሰው_የለም።  ከስራ ያቆምናቸው ታጋዮች ነበሩ እርቁ ሲፈፀም መፍታት እኮ አይደለም ወደቦታቸው ነው የመለስናቸው። አሃዱ አለቃ ናቸው ሁሉም በየቦታው በየደረጃው ኃላፊዎች ናቸው መከላከያ ውስጥ ...

እስረኛ በሌብነት ምክንያት ካለ አላውቅም ፤ እስረኛ ሰው ገድሎ የታሰረ ወንጀለኛ ካለ አላውቅም። ከግጭቱ ጋር የሚያያዝ ግን በመከላከያ ወጥተው የነበሩት ተመልሰው መከላከያ ውስጥ ገብተዋል።

እኛ እንደዚህ አይነት ፍላጎት የለንም። የምናውቀውም የለም። እኛ እስረኛ ፈተን ስራ አስፈፃሚ ፈተን ጌታቸው ጋር የቀሩ እስረኞች ነበሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያልፈታቸው ። "

ትግራዋይ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ፤ ተፈናቃዮች በስምምነቱ መሰረት ቤታቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የአማራ ክልሉ አቶ አረጋ ፣ ዶ/ር አብርሃም ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰሞኑን ንግግር ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ የተፈናቀሉ ሰዎች በሙሉ ቤታቸው እንዲመለሱ ነው ያሉ ሲሆን " በማንኛውም ሰዓት ነገ ሁመራ ያለው ቤቴ መመለስ እፈልጋለሁ የሚል ካለ እኛ ለመመለስ ዝግጁ ነን " ብለዋል።

#መከላከያ በአካባቢው የትግራይም ይሁን የአማራ ፀጥታ ኃይል እንዳይኖር ኃላፊነት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

ሁሉም ሰዎች ወደ ቤታቸው #ከተመለሱ_በኃላ እራሱ ህዝቡ አስተዳዳሪውን እንዲመርጥ እንደሚደረግና ከተረጋጋ በኃላ ህዝቡ ሪፈረንደም በማድረግ " እኔ አማራ ነኝ ፤ እኔ ትግራይ ነኝ " የሚለውን እንደሚወስን ተናግረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ተፈናቃዮች መቐለ ፣ ሽረ መቀመጥ እንደማያስፈልጋቸውና ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ረገድ ፌዴራል መንግሥት የሚጠበቅበትን እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በነበረው ሁኔታ ውጭ ሀገር የሄደ ባለሃብት ካለ መመለስ ይችላል ፣ ከባላሃብቶች ጋር በተያያዘ ችግር ካለም ይፈታል ብለዋል።

#ረሃብን በተመለከተ ጉዳዩን ፖለቲካዊ ማድረግ እንደማይገባና ትግራይ ተርባ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በልቶ ጠግቦ እንደማያድርግ ገልጸዋል። " ጌታቸውንም ወቅሼዋለሁ ረሃብ ካለ መደወል ነው እኔ ጋር ያለ አምጡ አግዙ ማለት ነው ቀላል ነው በትዊተር ከሆነ ግን እኛ በትዊተር አንነጋገርም ብሄዋለሁ ለሌሎች ነው የነገርከው እንጂ እኔ አልሰማሁም " ሲሉ ገልጸዋል። " ረሃብ ረሃብ ችግር ችግር አለ የሚል ፖለቲካ " ማድረግ ተገቢ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሚቴ ተቋቁሟል ሄዶ ጥናት አድርጎ መደረግ ያለበት ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/TPLF እውቅናን በተመለከተ ጉዳዩ የምርጫ ቦርድ ቢሆንም " በእኛ በኩል መሰጠት አለበት ብለን እናምናል ፤ በቅርብም #አነጋግረናቸዋል የሚፈታ ይመስለኛል ፤ ብዙም ከባድ አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#ከባንክ ጋር በተያየዝ ጉዳዩ ውስብስብ መሆኑን በማስረዳት መናገር ያልፈለጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢሯቸው አማካሪዎች እና ጉዳዩን በቀጥታ የሚያዩ የሚመለከታቸው አካላት ተነጋገረው የሚቻል ነገር ካመጡ ለማገዝ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ከባንክ ብድር ጋር በተያያዘ " ብድር ተከለከልን " የሚሉ ባላሃብቶች ካሉ ከዶ/ር አብርሃም እና ከሌሎች የሚመደቡ ሰዎች ጋር እንዲነጋገሩ አቅጣጫ ሰጥተው አልፈዋል። በመንግሥት ፖሊሲ ሊፈታ የሚችል ካለ ግን እንደሚታይ ገልጸዋል።

በኤርታራ መንግሥት (በሻዕብያ ኃይል) ስለተያዙ መሬቶች በተመለከተ ፤  የፌዴራል እና ከትግራይ የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙን በዚህም የሀገር መከላከያ ከትግራይ ጓዶች ጋር በመሆን ቦታዎችን እንዲያዩ እንደሚደረግ ገልጸዋል። " #ከአልጀርስ_ስምምነት ውጭ የሆነ ካለ ሪፖርቱ ሲመጣ እናያለን ፤ ማንም የማንንም ቦታ በኃይል ይዞ ለዘላለም መኖር አይችልም እንዳንዋጋ፣ ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር ትርፍ ነገር የተካሄደ ካለ አይተን ቦታውን ለይተን ኦፊሻሊ እነዚህ ነገሮች ይስተካከሉ ብለን በንግግር መልክ ልናበጅ እንችላለልን " ብለዋል። ውጤቱ ታይቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተግረዋል።

➡️ የጡረተኞችን ውዝፍ ክፍያን በተመለከተ ምንም ሳይሉ አልፈው በአቶ ጌታቸው በኩል ያለውን ነገር እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ሌሎችም አንዳንድ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ በቀጥታ አስተያየት ባይሰጡም በጥቅሉ በክልሉ ካሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በውይይት በምክክር እንደሚፈቱ ቃል ገብተዋል።

#TikvahFamilyMekelle
#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia