TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጥላቻ ንግግሮች‼️

#በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግሮች እና ቅስቀሳዎች ለብዙዎች ሞት፤ ለበርካቶች መፈናቀል እና ለዘመናት የተገመዱ ማኅበራዊ ትስስሮች መላላትን ንብረት መውደም ምክንያት መሆናቸው በከፍተኛ መጠን ማደግ ምክንያት መሆናቸው ተነገረ።

በብሄር አደረጃጀት የተዋቀረው የሃገሪቱ የፖለቲካ ስርአተ ማህበር የችግሩ ዋነኛ ምንጭ በመሆኑ የህግ ማእቀፎችን ከማውጣት በላይ መዋቅሩ ላይ መስራት እንደሚገባም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ከካናዳ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ስለ ጥላቻ ንግግር ምንነ፤ #የጥላቻ_ንግግር በኢትዮጵያ ሕግ ማእቀፍ እንዴት ይታያል፤ የማኅራዊ ሚዲያ መስፋት አጠቃቀም እና የጥላቻ ንግግር አዝማሚያዎች ምን ይመስላሉ? በሚሉ እና ከማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምጋር በተገናኙ ያሉ ክፍተቶችን ለመዳሰስ ዛሬ ውይይት ተደርጓል።

ብሄርን እንደ #አቀጣጣይ ነገር መጠቀም፤ ከዚህ በፊት ተበድያለሁ የሚል ስሜት ማደግ እና የማኅበራዊ መገናኛዎችን በስፋት የመጠቀም ባህል እያደገ መምጣት ችግሩን ተቆጣጣሪ አልባ እያደረገው መሆኑም በውይይቱ ተዳስሷል፡፡

የብሄር ማንነትን እንደ ስነልቦናና ማህበራዊ ወሳኝ እሴት በማየት ቋንቋ የሚጎለብበት፤ ባህል የሚዳብርበትና ታሪክ ጥበቃ የሚደረግበት ተቋማዊ ቅርጽ መፍጠር ለችግሩ መቃለል እንደመፍትሄ ተቀምቷል በውይይቱ።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia