TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UpdateSport የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በአዘርባጃኗ ዋና ከተማ ባኩ መካሄዱ ብዙ ቅሬታዎችን አስነስቷል።

የፊታችን ቅዳሜ የሚደረገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ለመታደም ብዙ እንግሊዛውያን ወደ ስፔኗ መዲና ማድሪድ እንደሚጎርፉ ይጠበቃል።

ነገር ግን ዛሬ የሚካሄደውን የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ለማየት ወደ አዘርባጃን መዲና ባኩ መምጣት የሚችሉት የአርሰናልና የቼልሲ ደጋፊዎች ቁጥር ከ6000 እንደማይበልጥ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የአርሰናሉ ሄነሪክ ሚኪታሪያን #በአርሜኒያዊ ዜግነቱ ምክንያት ደህንት አይሰማኝም በማለት ወደ አዘርባጃን እንደማይሄድ አስታውቋል። አርሜኒያ እና አዘርባጃን 'ናጎርኖ ካራባክ' የተባለው #ክልል የይገባኛል ፍጥጫ ውስጥ ያሉ ሲሆኑ የሚኪታሪያንም #የስጋት ምንጭ ይሄው ነው።

ብዙዎችም የፍጻሜ ጨዋታውን ለምን በአዘርባጃን ማካሄድ አስፈለገ? በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ግን ሃገሪቱ ለምስራቅ አውሮፓ ሩቅ በመሆኗ ምክንያት ውድድሩን ከማዘጋጀት ልትታገድ አይገባም ብሏል።

ባላት የነዳጅ ሃብት ምክንያት እጅግ የበለጸገችው አዘርባጃን ብዙ ሚሊዮን ዶላሮችን ፈሰስ በማድረግ በዓለማቀፍ ስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ያላትን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ እየሰራች ነው።

Via #ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia