TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባህር ዳር🔝

#በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉት የፀጥታ ችግሮች በርካቶች ከቀያቸው #እንዲፈናቀሉ እና የሰው ሕይወት በየቦታው #እንዲቀጠፍ ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ 51 አህጉረ ስብከቶች ስለሰላም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና አተገባበር ዙሪያ ለሃይማኖት አባቶች እና ለምዕመናን በባሕር ዳር ስልጠና እየሰጠች ነው፡፡

በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ደብረ ፀሐይ ሰላም አድርጊው ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ፍቅረ ማርያም ‹‹አሁን ላይ በሀገሪቱ የተፈጠረው የሰላም እጦት የሰው ልጆች ለእግዚአብሔር ያለመታዘዝ ምንጮች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ ሳለን የሰላም አስፈላጊነት የሁሉም ነገር ቁልፍ ናት ብሎ አስተምሮናል፤ ይህ ሰላም እንዲኖር የሃይማኖት አባቶች በጸሎት እና አስተምህሮ ከዚህ የበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅብን አመላካች ነው›› ብለዋል፡፡

የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ሰፊው ወልደትንሳኤ ካህናት ሕዝቡ ሰላምን ያገኝ ዘንድ እንዲያስተምሩ አደራ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ካህናት ስለሰላም የሠራነው ሥራ ስለምን በዚህ ትውልድ ፍሬ #አላፈራም? ሕዝቡስ ስለምን ሰላምን አጣ? ብለን ሁከት የሚፈጥር እንዳይኖር በትኩረት እንድንሠራ ኃለፊነት አለብን›› ብለዋል፡፡

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ #አብርሃም ደግሞ ሀገሪቱ ዜጎች እየተሰደዱ፣ ሀብት ንብረታቸው እየወደመ እና ሕይወታቸውን እያጡ ያሉበት ወቅት ላይ እንደምትገኝ ነው የተናገሩት፡፡ ሁኔታው ቤተ ክርስቲያን #ስለሰላም ከዚህ በላይ መሥራት እንዳለባት አመላካች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ብጹዕነታቸው ‹‹ሰላምን የማይሻ ሰው ውስጡ የፍርሃት ባሕር አለ፡፡ በፍርሃት የሚቅበዘበዝ ትውልድ ደግሞ የተዋቡ ከተሞችን ዶግ አመድ ያደርጋል›› ነው ያሉት፡፡ ግጭት የሕጻናት እና እናቶችን ዋይታ እንደሚያበዛና ለፀብ የሚያነሳሱ ሰበቦችና መደለያዎች ግን በርካታ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡ ‹‹የምንመራው ሕዝብ #ሰላም_ከሌለው አይጸድቅም፤ ጽድቅ የማያገኝ የእግዚአብሔር ትውልድ እንዳይኖር ደግሞ የሃይማኖት አባቶች ከዚህም በላይ መሥራት ይኖርብናል›› በማለትም አቡነ አብርሃም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethioia