TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Assosa : በአሶሳ ከተማ የጋሪ-ዎሮ የቦሮ-ሽናሻ የዘመን መለወጫ በዓል ተከበረ።

በበዓሉ የብሔረሰቡ ባህላዊ ቱፊቶች የሚንጸባረቁበት፣ አዛውንት እስከ ህጻናት በጋራ ተሰባስበው የሚያከብሩት በዓል ነው።

የብሔረሰቡ አባቶች መጪው ዘመን የሠላም፣ የጤና፣ የአብሮነትና የአንድነት ዘመን እንዲሆን መርቀዋል።

@tikvahethiopia
#Assosa

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሰሜን ሱዳን ብሉ ናይል ግዛት መካከል የሚደረግ የሰላምና የፀጥታ እንዲሁም የልማት ጉዳዮች ላይየሚደረገው ምክክር ዛሬ በአሶሳ ከተማ ይጀመራል።

የምክክር መድረኩን ተሳታፊዎች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሰላም፣ በፀጥታ፣ በልማትና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በሚመክረው መድረክ የሁለቱን አጎራባች ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሻግሩ ጉዳዮች ትኩረት ይደረግባቸዋል ተብሎም እንደሚጠበቅ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Iftar የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው። አርብ በደሴ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የሆነ የጎዳና ላይ ኢፍጧር መካሄዱ ይታወሳል። ትላንት ደግሞ በቡታጅራ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ ኢፍጧር ከማርስ ታወር ህንፃ - መናኸሪያ ድረስ ተካሂዷል (ፎቶው ከላይ ተያይዟል) ። ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኢኽላስ በጎ አድራጎት ማህበር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀውልናል። በአሁን ሰዓት ደግሞ በኮምቦልቻ…
#Iftar

#Assosa #Kombolcha #AA #Harar #Metu #Tullubolo

ዛሬ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በተለይም በታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ሀረር ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በተገኘበት ነው የአፍጥር ስነ ስርኣቱ የተካሄደው።

በኮምቦልቻ ከተማ ፥ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር " ኑ አብረን እናፍጥር " በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ባለፈ የሌሎች እምነት ተከታዮች የተገኙ ሲሆን ስነስርኣቱ እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

በመዲናችን አዲስ አበባ ደግሞ በነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት አስተባባሪነት ዛሬ በ11 ጎዳናዎች ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዶ በሰላም መጠናቀቁን አዘጋጆች አሳውቀውናል።

በተጨማሪ ዛሬ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል አሶሳ አንዷ ስትሆን ፤ ስነ ስርዓቱ በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች አስተባባሪነት ነው የተካሄደው። በመርሃ ግብሩ ላይ ወላጅ አልባ እና አቅመ ደካሞች፣ አረጋዊያን እና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች ከከተማው ሙስሊም ህብረተሰብ ጋር በጋራ አፍጥረዋል።

በአፋር ክልል ዱብቲ ከተማም ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል ፤ " አንድነታችንን እያጠናከርን ኑ በጋራ እናፍጥር " በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

በመቱ እና በቱሉቦሎም ዛሬ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

@tikvahethiopia
#Assosa

ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተማሪ ደራርቱ ገዳይ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል። ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ…
#Assosa

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ ዮሐንስ መርጋ በይግባኝ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ።

ደራርቱን በጩቤ ሶስት ቦታ ጀርባዋን በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ይታወሳል።

በውሳኔው ቅር የተሰኘው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቋል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከሳሹ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከአሶሳ  ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Via @tikvahuniversity