TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

"ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ የሱማሌ ክልል #ባለስልጣናትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት #ተጠናቋል"- ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
.
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ዛሬ ከሰዐት በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ 46 ያህል ተጠርጣሪዎች በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት #እንዲጠፋ፣ ህገመንግስታዊ ስርዐትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ንብረት እንዲወድምና በተያያዥ ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የተናገሩ ሲሆን ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ሌሎቹ 40 ግን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ተሸሽገዋል ብለዋል።

እንደ አቶ ዝናቡ ገለፃ ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን በሀገር ውስጥ የተደበቁትንም አፈላልጎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች #ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ መብታቸውን #በማንሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትልቅ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት አቶ ዝናቡ ህዝቡ የተሸሸጉ ግለሰቦችን አሳልፎ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሚዲያ ሁለት #ስለት ያለው መሳሪያ ነው፤ መልካም ከሰራህበት ትውልድ ታድንበታለህ፤ መጥፎ ነገር ካሳየህበት ደግሞ ትውልድ #እንዲጠፋ ታደርግበታለህ።...በፍፁም አግላይ የሆኑ፣ ስሜታዊ የሆኑ፣ ዘርን አመላካች የሆኑ፣ የሰው ልጆችን ወደክፋት እና ወደጥላቻ ሊወስዱ የሚችሉ ድምፆችን #በፍፁም ሚዲያዎች ይዘው መውጣት የለባቸውም።" ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia