#ADAMA #JIMMA #BALE_ROBE
ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ዛሬ በአዳማ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በኮንፈረንሱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
በተመሳሳይም በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ካሉ ዞኖችና ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ የሆኑበት የሰላም ኮንፈረንስ በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው። በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር ዞን፣ ባሌ ሮቤ እና ከጅማ ከተማ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 600 የሚልቁ ነዋሪዎች ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመምከር ላይ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት፥ በጥፋት ድርጊቶች ውስጥ የተሳተፉ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነት ይረጋገጣል።
ባሌ ሮቤ ላይ በተደረገው ውይይት የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ሰሞኑን የተፈጸመው ድርጊት ህብረተሰቡን እንደማይወክል ተናግረዋል። አያይዘውም እንደዚህ አይነት ዋጋ መክፈል እንደማያስፈልግ ጠቅሰው፥ ችግሮች ሲከሰቱ መመካከርና መደማመጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ውይይቱ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የታየውን የሰላም እጦት ችግር ከመሰረቱ ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia