TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD #FDREDefenseForce ሀገር መከላከያ ሰራዊት፥ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል ደመሰስኩኝ አለ። የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ ተልዕኮ ውስደው የተንቀሳቀሱና ሰራዊቱ የማያዳግም እርምጃ የወሰደባቸው ኃይሎች (የተገደሉ) በቁጥር 50 ሲሆኑ ፤ ከ70 በላይ የሚሆኑት…
ሱዳን ምላሽ ሰጠች...

ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በኩል የኢትዮጵያ መንግስትን እየተዋጉ ለሚገኙት የትግራይ አማፅያን ድጋፍ ታደርጋለች መባሉን አጥብቃ አስተባበለች።

ትላንት ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል መደምሰሱን (50 መግደሉን፤ 70 ደግሞ ማቁሰሉን) ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር አል-ታሂር አቡ ሀጃ "መሰረተ ቢስ ውንጀላ" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

አቡ ሃጃ ፥ "ሱዳን እና ሰራዊቷ በአጎራባች ኢትዮጵያ ወይም በሌሎች ሀገሮችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቀ አይገቡም" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፤ "ይህ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት ጥሰቶች በመቀጠላቸው ምክንያት የኢትዮጵያ አገዛዝ የገጠመውን ከባድ እውነታ ያንፀባርቃል” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሱዳን ለአማፅያን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገችን እንደሆነ ሲገልፅ ነበር።

በትላንትናው ዕለት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከገለፀው በተጨማሪ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ #የሱዳን_እጅ በጣም ረጅም መሆኑን ገልጿል።

የክልሉ ም/ኮሚሽነር "በሱዳን አካባቢ የነበረው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነው፤ በመሳሪያ በሃሳብ፣ እዛ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን መልምሎ ሱዳን አስቀምጦ የሚደግፉበትና ሽፋን የሚሰጡበት ሁኔታ አለ" ሲሉ አስረድተዋል።

ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፤ በካማሺ ዞን ፤ በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሴቶች በጅምላ በግፍ መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ሪፖርት ማድረጉ፤ ለጥቃቱ ደግሞ "ጉህዴን"ን ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia