TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቴፒ #አሽከርካሪዎች

° “ ከቴፒ ቡና ጭነን ለመውጣት ተከልክለን ከቆምን ወር ሊሞላን ነው ” - አሽከርካሪዎች

° “ ክልል ኮሚቴ አቋቁቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ”- ቡናና ሻይ ባለስልጣን

የጫኑትን ቡና ይዘው እንዳይንቀሳቀሱ በመከልላቸው ያለምንም መፍትሄ ከሦስት ሳምንታት በላይ ለመቆም እንደተገደዱ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

“ ለሥራ የምንወጣው ቤተሰቦቻችንንም ለማስተዳደር ነው ” ያሉት አሽከርካሪዎቹ፣ “ ሥራ ፈትተን የቆምንበት ጊዜ ቀላል አይደለም። እንኳን ቤተሰብ ልናስተዳድር ለእኛም ለእለት ለምግብ ገንዘብ ተቸግረናል ” ብለዋል።

“ የተከለከልንበትን ምክንያት እንኳን #አላወቅንም። መንግስት ግን አሽከርካሪዎች እያስተናገዱት ላለው ተደራራቢ ችግር መፈትሄ የማይሰጠው እስከመቼ ነው? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

አንዳንዶቹ በወባ ተይዘው መተኛታቸውንም ለመስማት ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሽከርካሪዎቹ ጉዳዩን በተመለከተ ይጠየቅልን ያሉት ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ችግር ለምን ተፈጠረ? ችግሩን ለመቅረፍስ ምን እየተሰራ ነው? ሲል ተይቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፋ ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር፣ “ ቡና በአገር ኢኮኖሚ፣ የአገር ሀብት ነው። ይቺ ቡና ከሌለች አገርም የለችም ማለት ይቻላል። 40 በመቶ ገደማ ቡና ነው ይዞ ያለው ” የሚል ቃል ሰጥተዋል።

“ ግን ቴፒ ላይ እያደረጉ ያሉት የExport ቡናን በአፈር እያሹ፣ በውሃ እያሹ ወደ Local መልሰው ቡናው ለExport እንዳይሆን እያደረጉ ነው፤ አቅራቢዎቹ ” ብለዋል።

“ ጅምላ ነጋዴዎቹ ይሄ ቡና በውሃና በአፈር ታሸ እንጂ ንጹህ ስለሆነ ጥሩ ያወጣላቸዋል። ለመሸጥ ነው የሚፈልጉት ” ያሉት አቶ ሻፊ፣ “ ለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ መመሪያ አውጥተን ችግሩ እንዲቆም ብዙ ጊዜ ተናግረን ሳይፈታ ቀረ ” ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለው፣ “ ይህ ብቻ ሳይሆን በአፈር የታሸ ቡናም መጋዚን ውስጥ አከማችተዋል። ይህ አገር ማጥፋት፤ አገርን ገቢ ማሻጣት ነው ” ብለዋል።

“ ላለፉት ስድስት (6) ወራት ቴፒ ብቻ ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ድረስ 34 በመቶ ንጹህ ቡና Local ነው የወጣው። ስለዚህ ምንም Local የማውጣት መብት የላቸውም። የሚያወጣው ማዘጋጃና ማከማቻም በአካባቢው የለም ” ነው ያሉት።

መፍትሄውን በተመለከተ ፤ “ አሁን ላይ ጉዳዩን ለክልል ሰጥተናል። ክልል ኮሚቴ አቋቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ስለዚህም አሽከርካሪዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ የተደረጉት የExport ቡናን ወደ Local በሚለውጡ አቅራቢዎች መሆኑን ያስረዱት አቶ ሻፊ፣ “ እንደዚያ በሚያደርጉት ላይ ባለሙያዎች አጣርተው እርምጃ እንዲወሰድ ኮሚቴ ተቋቁሟል ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia