TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#2 እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ተፍቀው ጥቅም ላይ በዋሉ የሞባይል ካርዶች ላይ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በሚፋቀው ቦታ ላይ ተመሳሳይ ቀለም ወይም ስቲከር በመቀባትና በመለጠፍ ጥቅም ላይ ካልዋሉ አዳዲስ ካርዶች ጋር በማመሳሰል ወደ ገበያ በማሰራጨት ደንበኞቻችንን እያጭበረበሩ መሆኑን ደርሰንበታል። ስለሆነም ክቡራትና ክቡራን ደንበኞቻችን የሞባይል ካርዶችን ስትገዙ በሚፋቀው የሚስጥራዊ ቁጥር ቦታ ከተለመደው የተለየ ቅብ ወይም ተለጣፊ ነገሮች አለመኖራቸውን አስተውላችሁ እንድትገዙ በተቻለ መጠን ካርዱን ከገዛችሁበት ቦታ ወዲያውኑ እንድትሞሉ እየጠየቅን ሂሳቡ በትክክል ከተሞላ በኃላ ካርዱን በመቅደድ በተገቢው የቆሻሻ መጣያ ውስጥ በመጣል ለአጭበርባሪዎች ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እንጠይቃለን።

#ETHI_TELECOM #ኢትዮ_ቴሌኮም

@tsegabwolde @tikvahethiopia