TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ናዝራዊት ቻይና ውስጥ #በሞት እንድትቀጣ አልተፈረደም!"

ቻይና ውስጥ ላለፉት #ሶስት_ወራት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ ስለምትገኘው #ናዝራዊት_አበራ በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ #ነቢያት_ጌታቸው ከአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። የሰጡት መረጃምይህንን ይመስላል፦

"ቻይና ሀገር ያሉ የኛ የቆንስላ ፅ/ቤት ሰራተኞች ሶስት ግዜ እስር ቤት ሄደው አይተዋታል። የመጨረሻው ጉብኝት እንደውም ያለፈው አርብ ነበር። ላረጋግጥልህ የምችለው የሞት ፍርድ ተፈረደባት የሚባለው ውሸት መሆኑን ነው። ሂደቱ ገና ነው። የሀገሪቱ አቃቤ ህግ ገና ክሱን ያቀርባል። ከዛ በሁዋላ ነው ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሄዶ የሚወሰነው። እስካሁን እፅ ነክ በሆነ ወንጀል ተጠርጥራ ነው ያለችው። እንደ ዜጋችን አሁን መጠየቅ የምንችለው የኮንሱላር ድጋፍ ማረግ ነው። እሱን ደሞ እያገኘን ነው። #ትክክለኛ_ፍርድ እንድታገኝ እና ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲኖራት ክትትል ይደረግበታል። የፍርድ ደረጃ ላይ ሲደረስም clemency (ምህረት) የሚጠየቅበት ሁኔታ የተለመደ ነው። እነሱም ያሉን ጉዳዩ በቻይና ህግ የተያዘ ነው ብለውን ነው።"

ምንጭ፦ ETHIO-NEWSFLASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያያ ቪሌጅ ሪዞርት ማናጀር ዛሬ ጠዋት በስልክ በአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ የሚከተለውን ብለዋል፦

"ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አምስት የሪዞርቱ ሰራተኞች በጥርጣሬ ተይዘዋል። እነዚህ በወቅቱ የሆቴል ክፍሎችን ቁልፎች ይዘው የነበሩ ናቸው። አሻራ እና ቃል ሰጥተዋል። ምን ያህል ብር እንዲሁም ምን አይነት የእጅ ሰአት እንደተሰረቀበት አላወቅኩም። ሆቴሉ ካሜራ የለውም ስለዚህ ሰራተኞቹ በጥርጣሬ ነው የተያዙት። ሞ ፋራህ አሁንም በሪዞርቱ ይገኛል። ነገር ግን ፌስቡክ ላይ እንደፃፈው ሳይሆን እኛ በጣም ተባብረነዋል። ሶስት እና አራት ግዜ በየቀኑ ፖሊስ ጣብያ እኔ እራሴ እየተመላለስኩ ነበር። የምርመራው ውጤት እስኪያልቅ ትብብራችንን እንቀጥላለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት የታሰበ፦

"የሀገራችን አክቲቪስቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም opinion leaders ከቀናት በሁዋላ በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ ቁጭ ብለው ይወያያሉ። የውይይቱ አላማ ምንም ያህል የተለያየ ሀሳብ ቢኖረን አንድ ላይ ቁጭ ብለን በጉዳዮቻችን ዙርያ ልንመክር እንደምንችል ማሳየት እና መፍትሄም መፈለግ ነው። ውይይቱ ላይ ለመካፈል እሺታችሁን ለለገሳችሁኝ ግለሰቦች እንዲሁም ለዚህ ፓነል ማካሄጃ የሆቴል አዳራሹን በነፃ ለፈቀደልኝ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምስጋና አቀርባለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert
/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

አቶ አረጋዊ በርሄ "መቐለ ላይ ታሰሩ" ተብሎ በአንዳንድ ሚድያዎች የተዘገበው ዘገባ የሀሰት መሆኑ ታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15 ጦር ሀይሎች አካባቢ ምን ተከሰተ?
/ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

ሰኔ 15 ቀን አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ አካባቢ የተከሰተው ግርግር እና ግድያ ብዙ ትኩረት ቢስብም #ጦር_ሀይሎች በተለምዶ ሲግናል (በድሮ አጠራሩ #መኮ) የተከሰተው ሁነት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ቢያንስ ሶስት ምንጮች አረጋገጡልኝ እንዳለው ጦር ሀይሎች አካባቢ በነበረው ግጭት ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። እስከ ለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር። ይህ ክስተት በእለቱ ከነበሩት ሌሎች ግድያዎች ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

በቅርቡ ስለ ጉዳዩ በAPው ጋዜጠኛ የተጠየቁ አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ "ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም። አጣርቼ መልስ ልሰጥህ እሞክራለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ አለኝ ያለ አንድ ግለሰብ ለጋዜጠኛው ተከታዩን መረጃ አቀብሎ ነበር፦

"ስለ ሰኔ 15ቱ (የጦር ሀይሎች አካባቢ ጉዳይ) የተወሰነ መረጃ አለኝ። መረጃውን ላገኝ የቻልኩት ደግሞ በዛ ምሽት ከሞቱት ሶስት የፌዴራል ኮማንዶዎች አንዱ የአክስቴ ልጅ ስለነበር ሬሳ ለመቀበል ከቤተሰብ ጋር በሄድንበት ጊዜ የአሟሟቱ ጉዳይ ስለተነገር ነው። እናም ጉዳዩ ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረ አንድ ኮሎኔል ለመያዝ በሄዱበት ጊዜ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነው። ግን እስካሁን አንድ የመንግሥት አካል ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር አለማለታቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል።"

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

እናስተውል!

/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

አሁን ላይ ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ በእርግጥ በጣም ወደ #ከፋ ሌላ መንገድ ሊወስደን እንደሚችል በዚህ ወቅት መገንዘብ ካልቻልን ችግር ውስጥ ነን። #የመበታተን እና #የመጠፋፋት ምልክቶች እያየን ነው። ቤተሰብ ያለው ስለቤተሰቡ ያስብ፣ ሀገሩን የሚወድ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨንቀው፣ ህይወቱን የሚወድም እንዴት እሆናለው ብሎ ያሰላስል።

በስሜታዊነት እና በደመ ነፍስ የሚደረጉ ድርጊቶች እና የሚወሩ ጉዳዮች እዚህ አድርሰውናል። እነዚህ ነገሮች አሁኑኑ ካልተገቱ ሀገራችንን በምናውቃት መልኩ #በቅርቡ ላናገኛት እንችላለን።

ፖለቲከኞች ህዝብ ላይ #አትቆምሩ፣ ህዝቤ ፖለቲካ ቀነስ አርገህ ስራህ ላይ አተኩር፣ አክቲቪስቶች አደብ ግዙ፣ እኔን ጨምሮ ጋዜጠኞች ለማንም ሳንወግን ስራችንን እንስራ።

አሜን!

/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

ሰላም ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!!

🗞ቀን ሃምሌ 8/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል ውስጥ #በሚገኝ አንድ የኢንዱስትሪ መንደር በሰባት የቻይና ዜጎች ላይ በተፈፀመ የዘራፊዎች ጥቃት አንድ ቻይናዊ መገደሉንና ሌላ አንድ መቁሰሉን የቻይና ኤምባሲን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በጉዳዩ ላይ የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ #አሰግድ_ጌታቸው እሁድ ቻይናውያን ላይ ደረሰ ስለተባለው አደጋ ለጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ይህን ብለዋል፦ "ድርጊቱ የተፈፀመው አዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ አቅራቢያ እሁድ አንድ ሰአት ገደማ ነው። እራት ከበሉ በሁዋላ በግሩፕ ወጡ። የሄዱበት ቦታ ከፓርኩ ሶስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያለ ሲሆን ጭለማ እና ገደላማ ስፍራ ነው። የአካባቢው ሰው እንኳን አይሄድበትም። ለምን ወደዛ እንደሄዱ ገና እየተጣራ ነው። ከዛም ቻይናዎቹ እርስ በርስ እንደተወጋጉ ሟቹ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ተናግሮ ነበር። ከዛ በሁዋላ ግን ሌሎች ሰዎች እንዳረጉት ለማስመሰል ተሞክሯል። በጥርጣሬ የተወሰኑ ቻይናውያንም፣ የአካባቢ ሰዎችም ተይዘዋል። ዝርፊያ ስለተባለው ግን አላውቅም እነሱም ተዘረፍን ብለው ሪፖርት አላደረጉም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ችግኝ ተከላውን ጊነስ መዝግቧል
/ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

"ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የዛፍ ተከላ ሪከርዱን እንዲመዘግብ ተጋብዞ ነበር፣ ግን ለፕሮግራሙ አልደረሱም!" ሲሉ የግብርና ሚንስትር አቶ ኡመር ሁሴን ተናገሩ።

ሚኒስትሩን "ሰኞ የተተከለውን 343 ሚልዮን ችግኝ ጊነስ መዝግቧል ወይ?" ተብለው ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ለተጠየቁት ጥያቄ ይህን ምላሽ ሰጥተዋል፦

"አሜሪካ ባለው ኤምባሲ በኩል ጥሪ ደርሷቸው ነበር። አምባሳደር ፍፁም አረጋ ጉዳዩን ይዞት ነበር። ነገር ግን ለፕሮግራሙ አልደረሱም። ኮሚኒኬሽኑ ትንሽ ዘግየት ብሎ ነበር መሰለኝ። ተከላው እና የቆጠራ ሂደቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የውጭ ዜጎችም እንዲያዩት ክፍት ሆኖ ነበር። ነገር ግን የኛ ሀሳብ ከዛ የዘለለ ነው። አሁን ይህንን ያህል ስራ ከሰራን መድገምም እንደምንችል እናውቃለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለAdey Employment Agency ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የተሰጠ ምላሽ እና ማብራሪያ፦

ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት መረጃዎቹ እኚህ ናቸው ያወጣሁትም መረጃ በቂ ማጣራት አድርጌባቸው ነው ብሏል፦

1.የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ እንዳረጋገጠልኝ ድርጅቱን አያውቀውም፣ ምዝገባም አላካሄደም። በአሁን ሰአት ወደ ውጪ ሰው ለመላክ ፈቃድ ያላቸው ወደ ሳውዲ፣ ጆርዳን እና ኳታር ሰው የሚልኩ ድርጅቶች ናቸው።

2.አዲስ አበባ ያለው የካናዳ ኤምባሲ እንዳሳወቀኝ ማንም ድርጅት ሰው ወደ ካናዳ ለመላክ ፈቃድ የለውም።

3.በአንድ የAdey ማስታወቂያ ላይ የተጠቀሰ Canada International የተባለ ድርጅት "እኛ ኢትዮጵያም ሆነ ሳውዲ አብሮን የሚሰራ ድርጅት የለም። ይህንን ለካናዳ መንግስት እና ፖሊስ እናሳውቃለን" ብለው መልስ ሰጥተውኛል (አባሪ ማስረጃ ተያይዟል)

4.Gillam Group ሰው ይፈልጋል ተብሎ በAdey ፌስቡክ ላይ የተፖሰተው ማስታወቂያ ላይ ያለው ድረ-ገፅ አይሰራም፣ የድርጅቱም አይደለም (አባሪ ማስረጃ ተያይዟል)

5.Sollatek የተባለ ድርጅትም እንልካለን ተብሎ የቀረበው የኢሜል አድራሻ አይሰራም (አባሪ ማስረጃ ተያይዟል)

6.Rev የተባለ ድርጅትም እንልካለን ተብሎ የቀረበው የኢሜል አድራሻ አይሰራም (አባሪ ማስረጃተያይዟል)

7.Coffee Day Hotel Resorts እንልካለን ተብሎ የቀረበው ድረ-ገፅ አይሰራም (አባሪ ማስረጃ ተያይዟል)

8.ሰራተኛና ማህበራዊ ተመዝግበናል ተብሎ እንደ አድራሻ የተቀመጠው ስልክ ቁጥር አይሰራም (አባሪ ማስረጃ ተያይዟል)

🏷ይህንን ድርጅት ለማስተዋወቅ አንዳንድ አርቲስቶች ሼር ሲያረጉት ነበር ሲል ጋዜጠኛ ኤልያስ ጨምሮ ገልጿል።

ማስረጃዎቹ👇
https://telegra.ph/EL-08-02

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

22 አካባቢ ዛሬ የሁለት ሰው ህይወት አለፈ!

የአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛው #ኤልያስ_መሰረት በስፍራው ተገኝቼ አየሁት እንዳለው ፖሊስ ሁለት የሰው ህይወት ያለፈባቸው ስፍራዎችን ከቦ መረጃ ሲወስድ ነበር። ፖሊሶች "እያጣራን ስለሆነ መረጃ አሁን የለንም" ብለዋል።

በአካባቢው የነበሩ እማኞች ግን አንድ ግለሰብ "ሞባይል ሊሰርቀኝ ነበር" በማለት የሌላ ሰው ጭንቅላት ላይ ተኩሶ ገድሏል። ከዛም ተኳሹ በሰዎች ተይዞ አካባቢው ወዳለ ፖሊስ ጣብያ ቢወሰድም የገዳዩን ሽጉጥ ይዞ የነበረው ፖሊስ "ባርቆበት" በአካባቢው የሱቅ ባለቤት የነበረን ግለሰብ መትቶ እሱም ህይወቱ አልፏል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia