TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አንድነታችንን የሚያጠናክሩ፥ ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን የሚያጎለብቱ እንጂ ወንድማማች በሆነው ህዝብ መካከል ጥርጣሬንና #ጥላቻን ብሎም ጠብን የሚዘሩ ፅሁፎችም ሆኑ ንግግሮችን አጥብቄ #እቃወማለሁ!

#ETHIOPIA
#አንድነታችንን የሚያጠናክሩ፥ ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን የሚያጎለብቱ እንጂ ወንድማማች በሆነው ህዝብ መካከል ጥርጣሬንና #ጥላቻን ብሎም ጠብን የሚዘሩ ፅሁፎችም ሆኑ ንግግሮችን አጥብቄ #እቃወማለሁ!

#ETHIOPIA #ሼር
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ🔝

‹‹እኛ ተማሪዎች ለህዝባችን አንድነት ምሰሶ ፤ #ለችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ እንጂ ለቁርሾዎች መነሻ መሆን የለብንም። ተማሪዎች ህዝባችንን #በድህነት ያስቀሩ ድክመቶቻችን የምንቀርፍ ኃይሎች እንጂ የቁርሾ መመስረቻዎች መሆን አንፈልግም፡፡›› የደብረ ማርቆስ ተማሪዎች

ተማሪዎቹ በትላንትናው ዕለት ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ #አብሮነትን የሚያጠናክሩ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡

• የአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች አንድነት #ለኢትዮጵያውያን ደኅንነት እንዲሆን አሻራችንን እናሳርፋለን ። እኛ አንድ ህዝቦች ነን ። አንድ ህዝብ መሆናችን ዩኒቨርሲቲዎች ምሳሌ እንዲሆኑ እንሰራለን ።

• እኛ ተማሪዎች ህዝባችንን በድህነት ያስቀሩ ድክመቶቻችን የምንቀርፍ ሀይሎች እንጂ የቁርሾ መመስረቻዎች መሆን አንፈልግም።

• ወደ ቤተሰቦቻችን ይዘን የምንመለሰው #ፍቅር እና #መፍትሄን እንጂ #ልዩነት አይሆንም።

• የምንማረው ህዝባችንን በፍቅር ለመምራት ነው ፤ #አንድነታችንን የሚያሳጡ ሀሳቦች እንዳይተባበሩ እናድርግ።

• ደም የመተካኪያ ፍሬ እንጂ ከዛሬ በኋላ የልዮነት ሀሳብ ሁኖ #ለሚከፋፍሉን እድል ሰጥቶ ወደኋላ የሚመልሰን ሊሆን አይገባም።

በደም ተለያይተን በድህነት ውስጥ መኖር በለውጡ ትውልድ አይቀጥልም፤ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ግቢያቸው ላይ በማድረግ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ‼️

ከሰሞኑ #እየሰማን እና #እያየናቸው የሚገኙት ነገሮች የብሄር ካርታው ተመዞ ተመዞ ሀገር #ለመበታተን አልሳካ ሲል #ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሀገር ለመበትን፤ ህዝብን ግጭት ውስጥ ለመክተት እየተሰራ ያለ ይመስላል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች፦ በሁሉም ክልሎች፣ ወረዳዎች፣ ዞኖች፣ ከተሞች...የምትገኙ #አንድነታችንን በማጠናከር እየታዩ ያሉ እኩይ ድርጊቶችን #ልናወግዝ እና ሰለማችንን ልንጠብቅ ይገባናል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግል ብቻ እድሜያችን እንዳያልቅ‼️

በትግል ብቻ እድሜያችን #እንዳያልቅ ቆም ብለን #እናስብ። 24 ሰዓት መስራት፤ መልፋት አለብን፤ በርካታ ሀገራት ጥለውን እየሄዱ ነው(ጎረቤቶቻችን ሳይቀሩ)። #ህብረታችንን ለልማት እናድርግ፤ #አንድነታችንን ይህ አስቀያሚ የድህነት ኑሮ ለመቀየር እናድርግ!!

መልካም ምሽት~TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia