TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትኩረት_የሚሻ_የፀጥታ_ጉዳይ 📣

በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ እና በአፋር ተላላክ ወረዳ በአንድ ግለሰብ ሞት ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ወደ ተኩስ ልውውጥ ተቀይሮ ለሰዎች ሞት እና መቁሰል ምክንያት ሆኗል።

አሁን ያለው የፀጥታ እጅግ ልዩ ትኩረት የሚፈልግ ነው ተብሏል።

ችግሩ የተከሰተው ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ሲሆን አንድ የአፋር ተወላጅ አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ መድና ከተማ ገበያ ውሎ ሲመለስ መሃል መንገድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከተገደለ በኃላ ነው።

ባለፉት ተከታታይ ቀናት መዲናን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ላይ የተኩስ እሩምታ የሚሰማ ሲሆን የግለሰብ ቤቶችም መቃጠል መጃመራቸው ተነግሯል። እስካሁን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ማወቅ አልተቻለም።

ችግሩን ለመፍታት በአፋርም አማራ ክልል በኩልም ብዙ ቢጣርም ውጤት አላመጣም ይልቅም እየባሰ ሄዷል።

በርካቶች ባለው የፀጥታ ችግር ከቄያቸው እየሸሹ መሆናቸውም ተነግሯል።

የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሰኢድ ኢብራሂም አሁን ያለው ሁኔታ ከግለሰብም አልፎ መልኩን ቀይሮ እጅግ አሰቃቂ የሆነና መጥፎ ጉዳት ሊያደርስ በሚችልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው የክልሉ መንግስት እና የፌዴራል መንግስት መኃል ገብተው ካላስቆመው ቀጠናው በጣም አስጊ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከአፋር ክልል ተላላክ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት እና የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት በኩል ለቪኦኤ ሬድዮ የሰጡት ቃሎች በዚህ ተያይዟል ያንብቡ ⬇️

https://telegra.ph/Attention-06-04-2

#አርጎባ_ብሄረሰብ_ልዩ_ወረዳ #ተላላክ_ወረዳ

#ቪኦኤ

@tikvahethiopia