TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለወጣቶች አሁን ያየናት ትንሽዬ የተስፋ ጭላንጭል እንዳትጠፋ ልንጠነቀቅ ይገባል። ከአመታት በፊት ብዙ ነገር አጥተን የቆየን ቢሆንም አሁን ላይ ጥሩ ጅምሮች እየታዩ መጥተዋል። ነፃነት የማይወዱ እና በዘረፋ መኖርን የለመዱ የለውጥ ጠላቶች ሀገሪቷን እንዲያተራምሷት እድል ልንሰጥ አይገባም። አንዳችን አንዳችንን እየጠበቅን በፍቅር እና በአንድነት ይህን ጊዜ ልንሻገር ይገባል። ስሜታዊ ከመሆን ተቆጥበን የነገን አሻግረን እንመልከት።

*የሶሻል ሚዲያ አርበኞች ደግሞ ግጭት እና ሰላም እጦት እናተው ጋር እስኪደርስ ምንም ላይመስላችሁ ይችላል። ስለሆነም ለዚህ ህዝብ አስቡለት። ያልሆነውን አትፃፉ። ብትችሉ ወጣቱን አረጋጉ።

ዶክተር ተመ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችና ሼዶችን በችግር ውስጥ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የማስተላለፉ ስራ ቀጥሏል። ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 302 የመንግስት ቤቶች ቤት ለሌላቸው በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚኖሩ #ነዋሪዋች እና #አካል_ጉዳተኞች ተላልፈው ተሰጥተዋል።

ያልአግባብ ተይዘው የነበሩ እና አዲስ የተሰሩ 16 የጥቃቅን እና አነስተኛ ሼዶችም #ለወጣቶች ተላልፈዋል። በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ህገወጥነትን በሁሉም መልኩ ለመዋጋትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ላይ አስተዳደሩ ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እነደሚሰራ ገልፀው በተመሳሳይ ይህ ተግባር በሁሉም ክፍለከተሞች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
2:30 ይጀመራል ተብሎ 5:30 የተጀመረው ስብሰባ...
-----------------------------------------------------------
መሪዎች የሰዓት #ቀጠሮን በማክበር #ለወጣቶች አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ ተቀዳሚ ሙፍቲ ዑመር እድሪስ ጠየቁ። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ይህን ያሉት ሁለት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ይጀመራል ተብሎ ከረፋዱ አምስት ሰዓት በተጀመረው የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ሰባተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው። ለጋዜጠኞች የተሰጠው የመግቢያ ካርድ ላይ “ሰዓት ይከበር” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ሰፍሯል። ለዚህም ይመስላል ጋዜጠኞችና ተሳታፊዎች በሰዓቱ ታድመዋል፤ ይሁንና የክብር እንግዶቹ በወቅቱ ሊገኙ ባለመቻላቸው ጉባኤው በሰዓቱ ሊጀመር አልቻለም። የዘገየበትን ምክንያት የገለጸ፣ #ይቅርታ የጠየቀም ሆነ ኃላፊነት የወሰደ አካልም የለም። በጉባኤው የከተማዋ ምክትል ከንቲባና የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ ከፌዴራልና ከከተማ አስተዳደሩ የተወጣጡ እንግዶችና የማህበሩ አባላት ታድመዋል። ተቀዳሚ ሙፍቲ ዑመር በዚሁ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱ ስብሰባዎች በተባሉበት ጊዜ #እንደማይጀመሩ ነው የገለጹት። በተባለበት ሰዓት በመገኘት ቀጠሮ በማክበር መሪዎች ለወጣቶች አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ በመግለጽ አገር፣ ሰላምና አንድነት የጋራ በመሆኑ ወጣቶች አንድነትን በተግባር በማሳየት ሰላምን ሊጠብቁ እንደሚገባም ገልጸዋል።

Via #ENA
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለሃብቱ ለወጣቶች ስራ ፈጠራ 10 ሚሊዮን ብር አበረከቱ !

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ ፤ #ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተሰማ።

አቶ በላይነህ ለሰከላ ወረዳ ወጣቶች ነው የስራ ዕድል መፍጠሪያ የሚውል 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉት፤ ድጋፉንም ሰከላ ወረዳ ግሽ ዓባይ ላይ ተገኝተው ለወጣቶቹ አስረክበዋል።

ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ ለወጣቶቹ የህይወት ተሞክሯቸውን እና ምክር አካፍለዋል።

አቶ በላይናህ ክንዴ በርክክብ መድረኩ ላይ ፦

" መንግስት ብቻ ሳይሆን ባለሀብቱ #ለወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ትልቅ ሀላፊነት አለበት።

ወጣቶቻችን የስራ ዕድል ካልተፈጠረላቸው እና ሀብት ማፍራት ካልቻሉ የባለሀብቱ ዕድገትም ይገታል። ስለሆነም ለወጣቶቻችን የስራ ዕድል በመፍጠር ተያይዘን ማደግና ሀገር መለወጥ ይገባናል።

ለእኛ ሀብታችን ወጣቶቻችን ናቸው ፤ ወጣቶች በገቢ እራሳቸውን ችለው ለቤተሰብና ለሀገር እንዲተርፉ እንደ ዜጋ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል።

ወጣቶችም የትኛውንም ስራ ሳይንቁ መስራት አለባቸው። እኔ ከዝቅተኛ ስራ እና ከትንሽ ገንዘብ ተነስቼ ነው እራሴን እየለወጥኩ የመጣሁት።

ይህ በድጋፍ የተሰጠ 10 ሚሊዮን ብር በተዘዋዋሪ ብድር መልክ ነው።

ወጣቶች አሁን የወሰዳችሁትን ገንዘብ ቁምነገር ላይ በማዋል አቅም እንድትፈጥሩ እና ብድሩን በመመለስ ለሌሎች ወንድሞቻችሁ የስራ ዕድል መፍጠሪያ እንዲሆን መስራት አለባችሁ " ሲሉ ተናግረዋል። (APP)

@tikvahethiopia