TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በሀገር #ደህንነት እና #ሰላም ጉዳይ ላይ #ጠንካራ ውሳኔዎች እንደሚያሳልፍ እምነቴ ነው። ከዚህ በኋላ ችግር እና መከራ የምንሰማበት ጊዜ ማብቃት አለበት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ‼️

በምዕራብ ኦሮሚያ ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መከሰቱን እና አሁን ግን #በቁጥጥር_ሥር እየዋለ መሆኑን የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም አስታወቁ። ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ በተጠቀሰው አካባቢ ተስፋ ሰንቆ ከውጭ የገቡ አካላትን የተቀበለው ሕዝብ መልሶ ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጉን አመልክተዋል። አሁን እየተወሰደ ባለው #ጠንካራ_እርምጃ አማካኝትም የተዘጉ መንገዶች እና አደጋ ላይ የወደቁ የመንግሥት የመዋቅር ሥፍራዎች መከፈታቸውንም ዘርዝረዋል።

ከተማዎቹን እየዞሩ ያተራምሱ ነበር ያሏቸው አባ ቶርቤ በሚል መጠሪያ የሚታወቁ ኃይሎችም በመንግስት ቁጥጥር ሥር መግባታቸውንም ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ገልጸዋል።

«አሁን #ትጥቅ_ማስፈታት ጀምረናል፤ እነዚያ የተዘጉ ከተሞች ነጻ አውጥተናቸዋል። የተዘጉ መንገዶች ተከፍተዋል፤ ሰዎች እንደተዘረፉ አውቃለሁ፤ ሸሽተው አዲስ አበባ የገቡ እንዳሉ አውቃለሁ፤ አባ ቶርቤ የሚባል በየከተማው እየዞረ ነፍስ የሚገድል ፤ የሚያስፈራራ ይሄን ለቅመነዋል።» ብለዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ከሰሞኑ በተከሰተው ወቅታዊ ሁኔታ መከላከያ ሰው አልገደለም ያሉት ጀነራሉ ክስተቱ #እንዲጣራ መወሰኑን፤ ድርጊቱ ተፈፅሞም ከሆነ መከላከያ ይቅርታ እንደሚጠይቅ #ካሳም እንደሚከፍል አመልክተዋል። ባለሥልጣኑ በተለያዩ አካባቢዎች ስለደረሰዉ ጉዳት ምንም አይነት አሃዛዊ መረጃ መስጠት እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ክቡር ፕረዝዳንት ለማ መገርሳ #ኢፍትሃዊነት እና #የአሻጥር ፖለቲካን የሚጸየፉ፣ በህዝቦች ወንድማማችነት፣ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በጽኑ የሚያምኑ ይንንም በተግባር ታግለዉ #ጠንካራ ሥብዕናቸዉን በተግባር ያረጋገጡ የህዝብ ልጅ ናቸዉ፡፡" አቶ አዲሱ አረጋ
.
.
.
ሠሞኑን አንዳንድ #አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች የክቡር ፕረዝዳንት ለማ መገርሳን ንግግሮች ከተነገረበት አዉድ ዉጪ እና ትርጉም ጭምር አጣምመዉ በማቅረብ ፕረዝዳንት ለማን የአሻጥር ፖለቲካ አራማጅ አስመስለዉ በማቅረብ የማጥላላት ዘመቻቸዉን ተያይዘዉታል፡፡ ለአብነትም በአንድ መድረክ ስለ ከተማ ዲሞግራፊ የተነገረዉን ንግግር በአሻጥር ፖለቲካ ተርጉመዉ እያራገቡት ይገኛሉ፡፡

በዚህ መድረክ አንዱ ተሳታፊ በኦዲፒ የእስካሁን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የኦሮሞ ህዝብ በኢኮኖሚ ሆነ በማህበራዊ እድገቱ እምብዛም እንዳልተሻሻለ አሁንም በገጠር በሞፈር እና ቀንበር እያረሰና የከብት ጭራ እየተከተለ እየኖረ እንደሆነ፣ ኦሮሞነት በገጠር እና በኋላ ቀር ኑሮ እየተመሰለ ነዉ የሚል ጠንከር ያለ ትችት አዘል ጥያቄ ከአንድ ተሳታፊ ለክቡር ፕረዝዳንቱ ተነስቶ ነበር፡፡ ለዚህም ጥያቄ ፕረዝዳንት ለማ ማብራሪያ ሲሰጡ ይህንን ችግር እንደ ፓርቲ ለመቀየር መስራት አለብን ከሚል ቅን ሀሳብ በመነሳት ኦሮሞነት በኋላ ቀር እና በገጠሬነት ብቻ ሳይሆን የከተማ ዘመናዊ ኑሮም መገለጽ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ በዚህም ረገድ ኦዲፒ ጠንክሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝና ከኢትዮጵያ ሶማሌ በኦሮሞነታቸዉ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ጭምር በኦሮሚያ ከተሞች በህዝቡ ተሳትፎና ድጋፍ እንዲሰፍሩና የከተማ የኑሮ ዘይቤን እንዲለማመዱ መደረጉን፤ የልማት ተነሽ አርሶ አደሮች እና የአርሶ አደር ልጆች በከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታን እንዲያገኙ መደረጉን፤ በኦሮሚያ ከተሞች የኦሮሞ ህዝብ ወደ ከተማ ኑሮ እየተሰባጠረ መምጣቱን፤ ወደ ፊትም የኦሮሞ የስነ ህዝብ ስብጥር (ዲሞግራፊ) በገጠር ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደሌለበትና ህዝባችን በከተማም መኖር እንዳለበት ለዚህም ኦዲፒ ጠንክሮ እንደሚሰራ አጥብቀዉ ምላሽ ሠጥተዋል፡፡

የሚገርመዉ ጉዳይ ኦሮሞ ህዝብ አኗኗር በኋላ ቀር የገጠር ኑሮ ብቻ መታወቅ የለበትም፣ ህዝባችን ኑሮዉ መሻሻል አለበት ገጠርም ከተማም መኖር አለበት የሚል ሃሳብ እንዴት የአሻጥር ፖለቲካ ሊሆን ይችላል? የኦሮሞን ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል እና ወደ ከተሜነት ማዘመን የክልሉ መንግስት ግዴታ ነዉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የክልሉ መንግስት የማንም ፈቃድ እና ቡራኬ አያሻዉም፡፡

ክቡር ፕረዝዳንት ለማ መገርሳ ኢፍትሃዊነት እና የአሻጥር ፖለቲካን የሚጸየፉ፣ በህዝቦች ወንድማማችነት ፣እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በጽኑ የሚያምኑ ይንንም በተግባር ታግለዉ ጠንካራ ሥብዕናቸዉን በተግባር ያረጋገጡ የህዝብ ልጅ ናቸዉ፡፡ አምርረዉ የሚጠሉትንና ሲታገሉት የነበረዉን የሴራ እና የአሻጥር ፖለቲካ በማራማድ የኦሮሞን ህዝብም ሆነ በግላቸዉ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚያስብ ስብዕና ፈጽሞ የላቸዉም፡፡

ነገር ግን ፕረዝዳንት ለማ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕረዝዳንት እንደመሆናቸዉ የኦሮሞን ህዝብ ኑሮ ለመለወጥ መስራት ግዴታቸዉ እንደሆነም መዘንጋት የለበትም፡፡ ስለሆነም ፕረዝዳንቱ የኦሮሞን ህዝብ የልማት እና የለዉጥ አጀንዳዎች ባነሱ ቁጥር በአሻጥር ለመክሰስ መሯሯጥ ኢ-አመክኖአዊ እና ተቀባይነት የሌለዉ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

#AddisuArega

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech🔝

የትላንት ምሽቱ የTIKVAH_ETHIOPIA #STOP_HATE_SPEECH 3ኛው መድረክ እጅግ በጣም በተሳካ ሁኔታ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ(WSU) በተገኙበት ተካሂዷል። ዶክተር ታከለ #ለመላው ሀገራችን ህዝብ የሚሆኑ #ጠንካራ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትም በቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።

⌚️ምሽት 1:30 የዶክተሩን ንግግር ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን አቀርብላችኃለሁ!!

ማስታወሻ🗓

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ #StopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ስለሚኖር ተዘጋጁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UpdateAU #ETHIOPIA የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት…
#USA #ETHIOPIA

" አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው።

ብሊንከን ፤ የአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሲባል ከህወሓት ጋር " በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ "  ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ ያስታወሱት ብሊንከን ለዚህ የመንግስት ዝግጁነት የሚሰጥ ምላሽን እናበረታታለን ብለዋል። ህወሓት (TPLF) ግጭት ለማቆም እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያወጣውን መግለጫ እናበረታታለን ሲሉም አክለዋል።

ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰላም ሂደቱን ለማገዝ ዝግጁ ናቸውም ብለዋል።

ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማቀጣጠል ማቆም አለባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ የኢትዮጵያን #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት እንደምትደግፍ የገለፁት አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ #ጠንካራ_አጋርነት መመለስ ትፈልጋለች ሲሉ ገልፀዋል።

" የአዲስ ዓመት መንፈስን ታሳቢ በማድረግ የአገሪቱ መሪዎች አገሪቱ መከራዋ ወደሚያበቃበት እና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኝ ወደሚያስችል መንገድ እንደሚሯት ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
የዋጋ ንረት . . . #ኢትዮጵያ

" አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና #ጠንካራ ሆኖ ቀጥሏል " - አቶ አህመድ ሽዴ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ረቡዕ ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን እና ታጠሪ ተቋማትን የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ፥ በመጋቢት ወር አገራዊው አጠቃላይ የፍጆታ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት 33.7 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።

የምግብ ነክ ዋጋ ንረት 34.5 በመቶ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ዋጋ ንረት 32.5 በመቶ ደርሷል ሲሉ አመልክተዋል።

አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና ጠንካራ ሆኖ መቀጠሉን ያሳያል ብለዋል።

" ይህም በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጫና የሚያሳድር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ምን አደረጋችሁ ?

አቶ አህመድ ሽዴ ፦

- የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ዘንድሮ የብር 17 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል።

የማዳበሪያ ዋጋ በተለይ በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ያለው ዋጋ እድገትን ተከትሎ የማዳበሪያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ነው ያደገው።

ይህም አንደኛ የውጭ ምንዛሬ ጫና በከፍተኛ ደረጃ አስከትሏል በሀገር ደረጃ። ሁለተኛ ሙሉ በሙሉ በብር ተመንዝሮ ወደ ገበሬው ይተላለፍ ቢባል የገበሬውን የመግዛት አቅም ታሳቢ በማድረግ ጫናው ከፍተኛ መሆኑ በመንግስት ታምኖበት 17 ቢሊዮን ብር ከበጀት ፀድቆ ድጎማ አድርገናል።

- ለአፈር ማዳበሪያ መግዣ ለክልሎች ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር 56.7 ቢሊዮን ዋስትና ተሰጥቷል።

በየክልሉ ያሉ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዲቀርብላቸው ለማድረግ በክልሎቹ በቀረበ ጥያቄ 56.7 ቢሊዮን ብር ዋስትና ተሰጥቷል።

- #ነዳጅ ላይ አሁንም መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እየደጎመ ነው ያለው። ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ ተደጉሟል ባለፉት ዓመታት ፤ ዘንድሮም ያለው ከፍተኛ ነው ፤ ደረጃ በደረጃ ከአጠቃላይ ድጎማ ወጥተን ወደ targeted subsidy የመግባት ስራው ከአንድ ዓመት በላይ እየተሰራ ነው። መሉ በሙሉ ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት እየተሰራ ያለው ስራ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ነው።

- መንግሥት በ97 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር 43 ሚሊዮን ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ለመግዛት ውል ገብቷል። ከዚህ ውስጥ በ33.8 ሚሊዮን ዶላር 15 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከውጭ ተገዝቶ ወደ ሀገር ገብቷል።

- የሡፍ የምግብ ዘይት አቅርቦትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው።

- ዘይት፣ ሩዝ፣ ስኳር፣ ከውጭ ሲገቡ ሆነ በሀገር ሲመረቱ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ታደርገዋል። የዋጋ ንረቱ ከዚህም ከፍ እንዳይል እያገዘ ነው።

- ለሀገር ውስጥ አምራቾች ከለላ ለመስጠት መኮሮኒ እና ፓስታ #ከተጨማሪ_እሴት_ታክስ ነፃ ታደርጓል። ይሄም የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ለማድረግ ታልሞ የተሰራበት ነው።

- መሰረታዊ ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት መንግሥት ብር 11.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ሳይሰበስብ ቀርቷል። ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉት መግባታቸው የዋጋ ንረቱ ከዚህ በላይ እንዳይባባስ ጥሩ ሚና አለው።

... በማለት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ወስደናቸዋል ስላሏቸው እርምጃዎች አስረድተዋል።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia