TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢሬቻ2012

በኢሬቻ በዓል ወቅት የሚከናወኑ የባዕድ አምልኮዎች የኦሮሞን ባህል የማይወክሉ በመሆናቸው ሊቆሙ እንደሚገባ የአባገዳዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ጫላ ሶሪ ተናገሩ፡፡ የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አፈ ጉባኤው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የኢሬቻ በዓል ሲከበር ባዕድ አምልኮ የሚመስሉ ኦሮሞ የማይፈፅማቸው ነገሮች ይከናወናሉ፡፡ በተለይ የኢሬቻበዓል ሲቃረብ በግ በማረድ ጭንቅላቱን ውሃ ውስጥ መጣል፣ ጥቁር ዶሮዎችን እራስ ላይ በማዞር ውሃ ውስጥ መክተት፣ አረቄና ውስኪ ውሃ ውስጥ መጣል እና ሽቶ ማርከፍከፍ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ የኢሬቻን በዓል ስለማይወክሉ ሊቆሙ ይገባል፡፡ ‹‹በእነዚህ ነገሮች ኦሮሞ ፈጣሪውን አይለምንም፤ ምስጋናም አያቀርብም›› የሚሉት አቶ ጫላ፣ እነዚህ ነገሮች ሰው ሰራሽ በመሆናቸው ምክንያት አይለመንባቸውም፤ ምስጋናም አይቀርብባቸውም ብለዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ከለገ ጣፎ ለገዳዲ ከተማ 50 ፈረሰኞችና በርካታ ፎሌዎች የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የተለያየ የባህል ትርኢት ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ ነው፡፡

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ነገ መስከረም 24 በሆራ ፊንፊኔ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የመጡ የባህል ቡድኖች አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ነገ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ከ49 ኩንታል በሶና ከ3 ሺ 5 መቶ 35 ኪ.ግ ቅቤ የተሰራው 4 ሺህ ሜትር ጩኮ ለእይታ ቀርቧል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ሙስጠፌ መሀመድ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ታኮን ጆክ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የዋዜማ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል።

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

"አዲስ አበባ የሁሉም #ኢትዮጵያዊያን ከተማ እንደመሆኗ መጠን የኦሮሞ ህዝብም በከተማው የኢሬቻን በዓል ለማክበር በመቻሉ የተሰማኝ ደስታ ከፍ ያለ ነው፡፡ በቀጣይነትም ከተማችን አዲስ አበባ ኃላፊነት ወስዳ የኢሬቻን በዓልን ጨምሮ ሌሎችን የሃገራችን በዓላት እና እሴቶች በሃገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ እና በዓለም መድረኮች ሁነቶችን በመጠቀም ታስተዋውቃለች። ከተማ አስተዳደራችን እና ነዋሪዎቿ በታሪክ አጋጣሚ የዚህ ታሪካዊ ኃላፊነት አስተናጋጅ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል፡፡ በመጨረሻም የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በዚህ ደረጃ በተቀናጀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ የከተማችን ነዋሪወች እና ባለሃብቶች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡" ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ከኮልፌ...

"ኮልፌ ኮምፕሬንሲቭ ትምህርት ቤት አካባቢ ህብረተሰቡ እና አመራሮች ለነገው የኢሬቻ በዓል ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ያሉ እንግዶችን ውሃና ዳቦ በማቅረብ በክብር እየተቀበሉ ነው።" #Amanuel

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

የኢሬቻ በዓል ቡራዩ በሚገኘው መልካ አቴቴ እየተከበረ ይገኛል፡፡ በመልካ አቴቴ የኢሬቻ በዓል ላይ የጋሞ አባቶችና ሌሎች የጋሞ ብሔረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012 | ህዝቡ ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ ሊቆም እንደሚገባ የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አባገዳዎች አስገነዘቡ። በዞኑ የኦዳ ቡሉቅ ኢሬቻ በዓል ተከብሯል።

https://telegra.ph/ETH-10-15

PHOTO: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia