TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰው አግተው ከፍተኛ ገንዘብ ሊቀበሉ የነበሩ አጋቾች #ተገደሉ

እንደ መተማ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ ፦

1ኛ. አጋች ጥጌ አበበ አለሙ
2ኛ. አጋች ባበይ አበባው የተባሉ ግለሰቦች አድራሻቸው መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ሲሆን ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በመሄድ " በመተማ ወረዳ ገንዳውሃ ከተማ #ሱቅ ብትሰሩ ቶሎ መቀየር እና ሀብታም ትሆናላችው " በማለት  የላሊበላ ከተማ ነዋሪ እና በአነስተኛ ጥቃቅን የሚሰሩ ግለሰቦችን ፦

1ኛ. አፀደ መኮነን
2ኛ. እመቤት መለሰ
የተባሉ ግለሰቦችን ተሰፋ በመስጠት በቀላሉ እንደሚከብሩ በመግለፅና ደውሉልን በማለት ስልክ ሰጠው ይሄዳሉ።

በኃላን እነዚህ ግለሰቦች ይህን ተሰፋ በማድረግ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በመነሳት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አይከል ከተማ ካደሩ በኃላ በነበራቸው የስልክ ልውውጥ በሁለተኛው ቀን ከአይከል ከተማ  በመነሳት ወደ #ገንዳውሃ _ከተማ ይመጣሉ።

1ኛ.አጋች ጥጌ አበበ አለሙ
2ኛ. አጋች ባበይ አበባው የተባሉት ግለሰቦች ህዳር 21ቀን 2015 ዓ.ም መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ዝንጀሮ በር ከተባለው ልዩ ቦታ ፦
1ኛ አፀደ መኮነን ከ2 ዓመት ልጇ ጋር ፤ 2ኛ እመቤት መለሰ ከ3 ዓመት ልጇ ጋር ከተቀበሏቸው በኃላ ወደ መቃ ቀበሌ ባርኩርኩር ጎጥ ጫካ ውሰጥ በመውሰድ እያንዳንዳችው ታግታችሁዋል  ብር ካልከፈላችው አትለቀቁም ይሏቸዋል።

አጋቾቹ በአጠቃላይ " 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ክፈሉ ካልከፈላችው ህይወታችሁን ታጣላችው " በማለት ለቤተሰቦቻቸው የደወሉ ሲሆን ቤተሰቦችም " እኛ ትንሸ ብር ነው ያለን ይህን መክፈል አንችልም " ሲሉ ይመልሳሉ።

አጋቾቹ፤ " ላሊበላ ከተማ ላይ ብር በልመና ስለሚገኝ  የቤተክርሰቲያን ሄዳችሁ ጥላ ይዛችው ለምኑ  ያለዚያ ህይወታቸውን ታጣላችው " በማለት በማስለመን 600,000 ብር ከብዙ ክርክር ካደረሱ በኃላ ሊከፍሉ ሲሉ የመተማ ወረዳ ፓሊስ ከማህበረሰቡ ጥቆማ ይደርሰዋል።

የወረዳው ፖሊስም ፤ ከአማራ ክልል ፓሊሰ ልዩ ሃይል " ኮከብ ክፍለጦር " ጋር በመቀናጀት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ታጋቾችን ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ላይ መቃ ቀበሌ ባርኩርኩር ላይ የተኩሰ ልውውጥ በማድረግ ታጋቾችን አስለቅቋል።

አጋቾቹ በፀጥታ ሀይሉ የተገደሉ ሲሆን አምስት ቦንብ መያዙ ተገልጿል።

መገጃው ከምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ከተገኘ ነው።

@tikvahethiopia