TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DW

"ህወሓት አይዋሀድም ይሄ ምንም ይቅርታ አያስፈልገዉም፡፡ ሊቀመንበሩ እንደሚሉት #የግድ አደርጋለሁ ካሉ እና ከተሳካላቸዉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸዉ!" -- አቶ ጌታቸው ረዳ

አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ለትግራይ ሚድያ ሃውስ፦

•"ኢህአዴግ የግድ ለውጥ ማድረግ ነበረበት። ቀድመን የተነጋገርንበት ነበር።"

•"ለዉጡ ወደኋላ ተመልሷል ብቻ ሳይሆን መንገዱን ስቶ ለሀገሪቱም አደጋ ጋርጧል።"

•"ትግራዋይነት እንርሳ። አማራነት እንርሳ። ኦሮሞነት እንርሳ። ኢትዮጵያውነት ብቻ ነው የምያዋጣን ብለው የምያምኑ የዋሃን ናቸው።"

•"ህወሓት አይዋሀድም ይሄ ምንም ይቅርታ አያስፈልገዉም፡፡ ሊቀመንበሩ እንደሚሉት የግድ አደርጋለሁ ካሉ እና ከተሳካላቸዉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸዉ።"

•"ትግራይን ለማስተዳደር የሚፈልጉ እና ለመላክ የተዘጋጁ አዲስ አበባ የሚኖሩ ሰዎች አሉ።"

•"ኢትዮጵያ ለዉጭ ጨረታ የቀረበች ሀገር መስላለች።"

•"የትግራይ ህዝብ ጥቅም በእንደዚህ አይነት ሰርከስ መመለስ አይችልም።"

•"ኢትዮጵያን ማዳን ካለብን እዉነት እናዉራ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የምር ለዉጥ ይፈልጋል፡ የመበለቶች ተረት በማዉራት የኢትዮጵያ ችግር ሊፈታ አይችልም።"

•"ሌብነት ኢንስቲቱሽናላይዝ እስከሚመስል ድረስ ከፍተኛ ምዝበራ የሚካሄድበት፥ በደም የተጨማለቁ ሰዎች እንደፈለጉ የሚፈነጩበት ሀገር ነዉ የሆነዉ።"

Via Dimtsi Weyane አማርኛ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል…
20/80 እና 40/60 ውል ፦

የቤት እድለኞች #ውል_ለመዋዋል_ሲመጡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው ?

- እጣው የደረሰው ግለሰብ ውል ለመፈፀም በአካል መቅረብ፤

- በውጭ የሚኖሩ ጉዳያቸውን በውክልና ለማስጨረስ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ (አውታንቲኬት) ሆኖ የመጣ ውክልና ማቅረብ፤

- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- ያላገባ/ች ከሆነ/ች 6 ወር ያላለፈው የምስክር ወረቀት፤

- ያገባ/ች ከሆነ/ች የትዳር አጋር የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ፎቶ 2 ኮፒ፤

- የምዝገባ ማረጋገጫ (print out) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የምዝገባ የምስክር ወረቀት ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የባንክ ምዝገባ ማረጋገጫ ከተመዘገቡበት ባንክ የሚቀርብ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የባንክ የቁጠባ ደብተር ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ (ፎቶ ባለው በኩል)፤

- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- ቅጽ -09 (ከወረዳ ተሞልቶ ታሽጎ የሚላክ) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የጠፋ ሰነድ ካለ የፖሊስ ማስረጃ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- 4×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ 4፤

- ፍቺ ካለ በፍ/ቤት የፀደቀ ፍቺ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- የንብረት ክፍፍል ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- ባለ ዕድለኛው በሞት ከተለየ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- የወራሽነት ማስረጃ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ ባለ እድለኛው ወይም ወኪሉ ይዞ መቅረብ አለባቸው።

የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ የሚመጣ ማንኛውም ባለጉዳይ #እንደማይስተናገድ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጥብቅ አሳስቧል።

#በውጭ_ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊ ከላይ የተጠቀሱትን ማሟላት #የግድ_ሆኖ

• የታደሰ ፓስፖርት ወይም ቢጫ ካርድ (yellow card) የታደሰ፤

• በውክልና ከሆነ የውክልና ወረቀቱ በጀርባው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተም የተረጋገጠ እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል ተብሏል።

ባለዕድለኞች / ወኪላቸው በ60 የስራ ቀናት ውስጥ ካልተዋዋሉ ምን ይፈጠራል ?

ባለእድለኞች ወይም ወኪላቸው ምዝገባ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ #ቤቱን_እንዳልፈለጉት_ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ የከተማው ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአጽንኦት አሳስቧል።

Credit : አዲስ ዘመን ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ ትላንት እሁድ በአዲስ አበባ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ መከልከሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

ፓርቲድ " ክልከላ በእሳት ፈትኖ እንደ ብረት ቢያጠነክረን እንጂ ሸብረክ እንድንል አያደርገንም " ብሏል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በቅድሚያ 6 ኪሎ የሚገኘው በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሥር የሚተዳደረው የስብሰባ ማዕከል አዳራሽ ይሁንታ አግኝተን በመንግሥት ክልከላ ተደርጎብናል፡፡

ቀጥሎም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በኩል አስይዘን ስለነበር ወደዚያ ቀይረን እንዲሁ ለጉባኤው ከ48 ሰዓት በታች ሲቀር በድጋሚ ክልከላ ተደርጎብናል፡፡

#የግድ መደረግ ያለበት በመሆኑ ሦስተኛ አማራጭ ከብዙ ድካም በኋላ የቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሰርግ አዳራሽ ሕጋዊ ሂደቶችን አሟልተን፣ ክፍያ ፈጽመን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን አስገብተንና ትላንት ጠዋት ከሀገራችን 4ቱም ማዕዘናት ከመጡ ከ700 በላይ አባላት ተገኝተው፣ የተጋበዙ የሌሎች ፓርቲዎች አመራሮች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች፣ ተጋባዥ እንግዶች ጋር በመሆን ወደአዳራሽ ስናመራ “ከመንግሥት የመጣ ትዕዛዝ” በሚል ወደውስጥ እንዳንገባ ታግደናል፡፡     
   
በዚህ መሐል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሓላፊ ለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳዩን አስረድተን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም፣ በተዋረድ ካሉ የጸጥታ ተቋማት ሓላፊዎች ጋር ቢደወልም መፍትሔው ሊቀርብ አልቻለም፡፡

ፓርቲያችንም ከ3 (ሦስት) ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገበት ጉባኤ ሳይከናወን አባላትን ለከፍተኛ እንግልት ዳርጎብናል፤ እንደፓርቲም ከፍተኛ የገንዘብ ኪሣራና የሥነልቡና ጉዳት አድርሶብናል፡፡ "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia