TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል "

13 የ " ቤቲንግ " ሥራ ድርጅቶች እንዲሁም 109 አንቀሳቃሾቻቸው ከህብረተሰቡ የሚሰበስቡትን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በመጠቀም በጥቁር ገበያ የውጭ ሀገር ምንዛሬ ግዢ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን በተደረገ ክትትል በመረጋገጡ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ተደረገ።

ጉዳያቸውም በህግ እንደሚታይ ተገልጿል።

" ቤቲንግ " በሚል ስያሜ የሚታወቁትና የውርርድ ስራዎችን ላይ የተሰማሩት እነዚህ አካላት #የታክስ_ማጭበርበርን ጨምሮ በህገ-ወጥ የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ግዢ ወንጀል ድርጊት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው #ተረጋግጧል ሲል የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ የ13ቱን የቤቲንግ ስራ ድርጅቶች እና የ109 አንቀሳቃሾቻቸውን ስም ዝርዝር በይፋ አልገለፀም።

በእነዚህና በሌሎችም ዘርፎች በሚንቀሳቀሱ እና መሰል የወንጀል ተግባር ላይ በሚሳተፉ አካላት ላይ ቀጣይነት ያለው ክትትልና ህጋዊ የሆነ እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታወቀው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ታሳታፊ እየሆኑ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine