TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#መምህራን በወላይታ ዞን መምህራን በፖሊስ እየታሠሩ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል። እስሩ የተፈፀመ ያለድ መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል። ፖሊስ መምህራኑን የሚያስረው " አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል፤ የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል " በሚል መሆኑን…
#Update

🔵 “ መምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን ” - የወላይታ ዞን መምህራን

🔴 “ ከ10,500 በላይ መምህራን ደመወዝ አልተፈጸመላቸውም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን ያልተከፈላቸውን ደመወዝ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታ ለማስገባት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ “ በፓሊስ መታሰራቸው ” ተሰምቶ ነበር።

የደመወዝ ቅሬታቸው ባለመፈታቱ የመብት ጥያቄ ለማንሳት ባደረጉት ፒቲሽን የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ነበር ፓሊስ “ አመጽ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል። የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል ” በሚል ያሰራቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የታሰሩት መምህራን ተፈቱ ? የደመወዝ ቅሬታችሁስ መፍትሄ አገኘ ? ሲል ዛሬ ቅሬታ ያላቸው መምህራንን ጠይቋል።

ምን መለሱ ?

ምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። ሦስቱም መምህራን ተፈትተዋል። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን። 

‘ መንግስትን ከሕዝብ አጣልታችኋል ’ የሚለው ክስ በፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም መረጃ የላቸውም። ከዚያ ጋር ተያይዞ ነው ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸው።

የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።

አሁንም ደመወዝ እንዲከፈለን እንፈልጋለን።

መምህራን ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ሥራ ስለሚሰሩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በትክክል እንዲተገብሩ ደመወዝ መከፈል አለበት።

የሐምሌ ደመወዝ እስካሁን አልተከፈለም። ለመምህራንና ለጤና ባለሙያ 40 በመቶ፣ ለፓሊስ 20 በመቶ እንጂ ከዚህ ውጪ ደመወዝ አልተከፈለም።

አሁን እንደገና አጠቃላይ የትምህርት ባለሙያም ወደታች ወርዶ ‘የሐምሌን ደመወዝ እንከፍላለን’ በማለት አመራርም በአጠቃላይ ተረባርቦ መምህራን ወደ ስራ አስገብተዋል።

ፍርድ ቤትም ገና የራሱን ቀጠሮ እየሰጠ ነው የሐምሌ ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት
” ብለዋል።

ደመወዛቸው በወቅቱ አለመፈጸሙ ትልቅ ጥፋት ሆኖ እያለ ይህንኑ ቅሬታ መምህራን ታስረው መቆዬታቸው ግፍ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም በዚሁ ቅሬታ ላይ ምን እየሰሩ እንደሆነ የክልሉና የዞኑን መምህራን ማኀበር ጠይቋል።

የክልሉ መምህራን ማኀበር የመምህራንን መታሰር በተመለከተ እስካሁን ሪፓርት እንዳልተደረገለት/ቅሬታ ያደረሰው አካል እንደሌለ ገልጾ፣ በይበልጥ የዞኑ መምህራን ማኀበር እንዲጠየቅ አሳስቧል።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የወላይታ ዞን መምህራን ማኀበር ሊቀ መንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ፣ “ በቅርቡ ታስረዋል ስለተባሉት መምህራን ለኛ ኦፊሻሊ የቀረበልን ምንም መረጃ የለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

“ ያመለከተልን አካል የለም። ከውጪ ወሬ ነው እየሰማን ያለነው። ወደ አክሽን እንዳንገባ የመጣልን መረጃ የለም ” ያሉት ሊቀመንበሯ፣ “ እንነጋገርበት ወደኛ መምጣት ይችላሉ ” ብለዋል።

የደመወዝ ክፍያን ቅሬታ በተመለከተም በሰጡን ምላሽም፣ ከ10 ሺህ 500 በላይ መምህራን ደመመወዝ እንዳልተፈጸመላቸው ገልጸው፣ ማኀበሩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

የክፍያ አለመፈጸምን በተለመከተ ምላሽ እንዲሰጡ ከዚህ ቀደም የጠየቅናቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጎደና፣ “ አራት ወረዳዎች ላይ መሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው። የሐምሌ ወር ክፍያ ላልተፈጸመላቸውም ወረዳዎች ገቢ ሰብስበው እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው ” ብለው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ማብራሪያ ሰጥቷል።

ቢሮው እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከአውድ ውጪ በተተረጎመ መንገድ እንደሆነ ጠቁሟል።

" የ1997 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው የተሳሳተ መረጃ ትክክል ባልሆነ መልኩ  ከአውድ ውጪ ተተርጉሞ የቀረበ ነው " ብሏል።

ቢሮው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?

" ከተማ አስተዳደሩ የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ለማስተላለፍ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2011 መሰረት ክፍል 3 አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 እና 2 መሰረት ብቁ እና ንቁ ማለትም ' የቤት ፈላጊዎች በገቡት ግዴታ መሰረት የቁጠባ መጠን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትክክል ተቀማጭ ማድረጋቸውን ከእጣ በፊት ያረጋግጣል ' ይላል።

ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢዎች በወቅቱ በመረጃ ቋት ውስጥ ንቁ እና ብቁ  የነበሩ ተመዝጋቢዎችን ከተማ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አስተናግዶ ያጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በወቅቱ ብቁ ያልነበሩትን የ1997 ተመዝጋቢዎች እና ሌሎች የ2005 እጣ ያልደረሳቸው የቤት ፈላጊዎች እየተተገበሩ ባሉ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች እያስተናገደ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በወቅቱ ብቁ እና ንቁ  ያልነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች ከየትኛውም የቤት ልማት መርሃ ግብር ውጪ እንደተደረጉ ተደርጎ የተሰራጨው የሀሰት መረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ እና ይህንን ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን ከተማ አስተዳደሩ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

ከተማ አስተዳደሩ ተመዝግበው የሚጠባበቁትን ሆነ ሌሎች የከተማችዋን የቤት ፈላጊዎች ቤት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ አዳዲስ የቤት ልማት አማራጮችን በመቀየስ እየተገበረ ይገኛል " ብሏል።


NB. ቢሮው ስለ 1997 ተመዝጋቢዎች የትኛው ሚዲያ ከአውድ ውጭ የተተረጎመ ሀሰተኛ መረጃ እንዳሰራጨ በግልጽ ያለው ነገር የለም ነገር ግን መረጃውን የሚያሰራጩትን በህግ እጠይቃለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministrationBureau

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ከለሊቱ 6:04 ላይ አፋር ክልል፣ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድረስ ተሰምቷል። በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። አርብ ምሽት 3:55 ላይ እንዲሁም ለሊት በዚህ ሰዓት የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር። በአዋሽ የሚገኝ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " አላህ ክፉን ሁሉ…
#Update #Earthquake

በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።

ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አግተዋቸው 300,000 ብር እየጠየቁ ነው " - ቤተሰቦች በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ሰዎች ለሕክምና ብለው በወጡበት በታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ የታገቱት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ የሕክምና አገልግሎት በመዘጋቱ አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ነቀምት ሄደው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።…
#Update

በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ሰዎች  ለሕክምና ብለው በወጡበት በታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋች ቤተሰቦች ከቀናት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

" አግተዋቸው 300,000 ብር እየጠየቁ ነው " ነበር ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ታጋቾቹ እንደተለቀቁ ከቤተረቦቻቸውና ከታጋቾች አንደበት ማረጋገጥ ተችሏል።

ከታጋቾቹ መካከል አንዱ እንደሆኑ የገለጹና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ፤ " ሰው ተደብድቦብን ለሞት ደረሰና ወደ ነቀምት ሆስፒታል ሪፈር አፅፈን ወደ ነቀምት ተጓዝን። እዛ እስከምንደርስ ምንም ችግር አልደረሰብንም ነበር " ብለዋል።

ሕክምናውን ጨርሰው እየተመለሱ  በነበረበት ወቅት ኣጋቾች ከጫካ ወጥተው መታወቂያ ከጠየቁ በኃላ ማገታቸውን ጠቁመዋል።

" የአማራ ተወላጅ ወደዛ መሄድ ስለማይችል ከእኛ ጋር አንድ የኦሮሞ ተወላጅ አብረን ይዘን ሄደን ነበር። እርሱን 'ና ውረድ ለምን ለአማራ ተወላጅ ብለህ አብረህ የሄድህ? ' ብለው ወደጫካ ወስደው በጣም ደበደቡት፤ አሰቃዩት " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

" እኛ ላይ ዛቻ አደረሱብን እንጂ አልደበደቡንም። ከዚያ ገንዘቡ ሲላክ ለቀቁን " ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

ያገታችሁ ማነው በሚን ለቀረበ ጥያቄ  በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ መሆኑን ገልጸዋል።

" ሌሊቱን በጫካ ውስጥ ሲያዞሩን ነው ያደሩት የእግር ጉዞ አለው። እኔ ደግሞ ኦፕራሲዮን ነኝ። ያገተን ታጣቂ ‘ መናኸሪያ ላይ መታወቂያ የጠየቃችሁ ፓሊስ የለም ወይ ? ’ አለኝ። አዎ ጠይቆናል አልኩት። ‘ እርሱ ነው እንደመጣችሁ የነገረኝ አለኝ ’። ሌላ የማውቀው ነገር የለም " ሲሉ መልሰዋል።

እኚሁ ታግተው የነበሩ ግለሰብ፣ " እኛ ተሰቃዬንም፤ ገንዘብ ከፈልንም ተለቀናል። ለወደፊት ግን ማንኛውም ሰው መብቱ ተጠብቆ በማንነቱ የሚደርስበት ጉዳት ይቁምልን " ሲሉ ተማጽነዋል።

ታጋቾች ከእገታ እንዲለቀቁ ከወዳጅ ዘመድ እርዳታ ጠይቀው ለአጋቾቹ ገንዘብ እንደላኩ የገለጹልን አንድ ስማቸው እንዲነሳ ያልፈለጉ የታጋች ቤተሰብ ፥ " ወንድሞቻችን ከነቀምት ከህክምና እየተመለሱ ኪረሙ ወረዳ ለመድረስ 5 ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው ታግተው ነበር " ብለዋል።

" ምንድን ነው ችግሩ ? ብለን ስንጠይቅ የተፈለገው 300 ሺሕ ብር ላኩ ተባልን፡፡ ብሩን ላክን " ነው ያሉት።

ለአጋቾቹ በምን መልኩ ነው ገንዘቡን የላካችሁት ? ተብሎ ለቀረበላቸው የቲክቫህ ጥያቄ ፥“በአካውንት እንላክላችሁ አልናቸው 'አይቻልም በእጃችን ነው፣ በአንዲት መኪና ሰዎች ይመጣሉ ለእነርሱ ስጡ ያኔ ሰዎቹን እንለቃለን' አሉ፡፡ ከወረዳው የተላከችው መኪና መጣች 300 ሺሕ ብር ላክን፡፡ ሰዎቹ ተለቀቁ። መኪናይቱ ከወረዳ የመጣች ናት " ብለዋል።

አጋቾቹ  ፥ ከታጋቾቹ ጋር አብሮ የሄደውን ግለሰብ ' ለምን አብረህ ሄድክ? በሚል'እንገለዋለን' በሚል ዛቻ አንለቅም ብለው  ሲያስፈራሩ እንዳይገድሉት ተማፅኖ ሲቀርብ '100 ሺሕ ብር ጨምሩ' በማለታቸው ብሩ ተጨምሮ እርሱም ከእገታ መለቀቁን ጠቁመዋል።

በአሙሩ፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋና በሌሎችም " ቦታዎች ሰዎች ታግተው ብር ተጠይቆባቸው ብሩ ከተላከ በኋም በአጋቾች ተገድለዋል። እኛ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ብሩን ከፍለን ተለቀውልናል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ እገታው ከተፈጸመበት ቦታ በቅርብ ርቀት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እንደነበሩ የታጋች ቤተሰብ አስረድተዋል።

ሌላኛው የታጋች ቤተሰብ ደግሞ ፥ " ከዘመድ ወዳጅ አሰባስበን 400 ሺሕ ብር ከፍለን ታጋቾቹ ተለቀዋል፡፡ ሴቶች፣ የሶስት ቀን ሕፃናት ሁሉ ተገድለዋሌ፡፡ ግን እስከ መቼ ድረስ ነው ፍትህ የማይሰጠን? " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአካባቢውንና የክልሉን የጸጥታ አካላት ምላሽ ለማካተት ጥረት ቢያደርግም ባለስልጣናቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው " -የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ከክፍያ ጋር በተያያዘ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ዘግተው ስለወጡና ስራ ስላቆሙ ጤና ባለሞያዎች በተመለከተ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል። " እኔ እንደ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ ይከፈላቸው ብዬ እየጠየኩ ነው በዕለቱም ይህንን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር…
#Update

" ጥያቄያችን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " - ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሙያዎች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መግለጻችን ይታወሳል።

የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ማለትም 12/02/17 እስከ 18/02/17 ድረስ ስራ ሳይገቡ ቆይተው ማክሰኞ በ19/02/2017 ዓ.ም ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር የወረዳው ባለሥልጣናት በተገኙበት በተደረገ ውይይት ሽማግሌዎች ከወረዳው ሃላፊዎች ጋር ለማደራደር በመስማማታቸው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።

ይሁን እንጂ ከስብሰባው ማብቃት በኋላ " አድማውን አስተባብራቹሃል " በሚል 14 የሚሆኑ ባለሞያዎች ለእስር ተዳርገዋል።

በተለያየ ቀናት ለእስር የተዳረጉት እነዚህ ባለሞያዎች ከ 2 እስከ 6 ቀናት ለሚሆን ጊዜ ታስረው በዋስ ከእስር ተፈተው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለእስር ከተዳረጉት ባለሞያዎች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሯል።

ባለሙያዎቹ  " ጥያቄያችን ፓለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " ብለውናል።

" የጠየቅነው የሰራንበትን ክፍያ ሆኖ ሳለ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ' ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳ አድርጋቹሃል፣ ሰዎችን ወደ ሥራ እንዳይጋቡ አስፈራርታቹሃል ' የሚል ክስ ተነቦልናል " ነው ያሉት።

በተጨማሪም ባለሞያዎች ወደ ሆስፒታል ሲመለሱ ከአሁን በኋላ ተመሳሳይ የሆነ የስራ ማቆም አድማ ውስጥ ቢገቡ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርሙ ተደርጓል ብከዋክ።

ሰራተኞቹ ከተመለሱ በኋላ BPR የተሰኘ በየስምንት ሰዓቱ በሺፍት የሚቀያየሩበት አሰራር እንዲዘረጋ መደረጉን ተናግረዋል።

በአዲሱ አሰራር መሰረት ጠዋት 12 ሰዓት ወደ ስራ የገባ ሰራተኛ 8 ሰዓት ከስራ የሚወጣ ሲሆን 8 ሰዓት የገባው ምሽት 4 ሰዓት ከስራ ይወጣል።

ይሁን እንጂ ይህ አሰራር " ሆስፒታሉ ለሰራተኞች ሰርቪስ የሌለው በመሆኑ እና በምሽት ሺፍት ከስራ ስንወጣ እና ስንገባ ለጅብ እየተጋለጥን ነው " በሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

" ይህ አይነቱ አሰራር የተዘረጋው የወረዳው አስተዳደር ለመቀጣጫ እንዲሆን በሚል ነው " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማስቀረት የተደረገ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ጉዳዩ በዋናነት የሚመለከታቸውን የአንጋጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የሆስፒታሉ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ማርቆስ ማሞን ቅሬታውን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ለማናገር ተደጋጋሚ የሆነ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ አቶ ተሰማ አበራ አዲሱ  አሰራር ለአደጋ አጋልጦናል የሚለውን የሆስፒታሉን ባለሞያዎች ቅሬታ አይቀበሉም።

" የትርፍ ሰዓት ስራ ሲሰሩ ያልነበረ ጅብ ዛሬ ከየት መጣ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ አይነቱ አሰራር ያልነበረና አዲስ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ብለዋል።

አክለውም " ይህን ጭቅጭቅ የሚያመጣው ወረዳው የመክፈል አቅም የሌለው በመሆኑ ነው በቀጣይም መጋጨት የለብንም " በማለት አሰራሩ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለሞያዎቹ የሰሩበት ገንዘባቸው ሳይከፈላቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል መቼ ክፍያቸው ይፈጸማል ስንል በድጋሚ ላነሳንላቸው ጥያቄም "አሁንም እየተነጋገርን ነው ከወረዳ መንግሥት ጋር የገንዘብ ክፍተት ስላጋጠመ እንጂ መከፈል እንዳለበት ተግባብተናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል። ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ…
#Update

" ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል " - ቢሮው

ሰኞ ዕለት በመርካቶ ያሉ ነጋዴዎች " ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው የመጣነው " ያሉ ሰዎች ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ በሚል እቃችንን ወርሰውብናል ብለዋል።

በዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በእለቱ በመርካቶ ያሉ በርከት ያሉ ሱቆች ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ፥ የተባለው ችግር በመርካቶ እንደተፈጠረ አምኖ ነገር ግን የነጋዴዎችን እቃ ወርሰዋል የተባሉት ግለሰቦች ከገቢዎች ቢሮም ይሁን ከየትኛውም የመንግስት አካል ያልተወከሉ ህገ ወጦች ናቸው ሲል ማመልከቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

የታክስ ኢንቴሌጀንስና ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ነጋሽ " እኛ ምንም አይነት ንብረት የመውረስ መብት የለንም መወረስ ካለበትም ይህንን የሚሰራው የጉምሩክ ኮሚሽን ነው " ብለዋል፡፡

" ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል፤ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ደግሞ ገንዘብ ተቀብለው ተሰውረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ነጋዴዎቹ ለፀጥታ አካላት መረጃዎችን በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " መንግስት ከመርካቶ ገበያ የነጋዴዎችን እቃ መውረስ ጀመረ " ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ግን ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ውዥምብሩ የተፈጠረው በዚህ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ከዚህ ቀደም ይሰራ እንደነበረው ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይፈፀም ለማድረግ ያለመ የቁጥጥር ስራ እነደሆነ ኃላፊው ጠቁመዋል።

ከህዳር 1 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዘመቻ መልክ ነው እየተሰራ ያለው።

ከዚህም በተጨማሪ ቢሮው በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመርካቶን የንግድ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች " ያለ እጅ መንሻ " የማይሰሩ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሎ ሁሉንም የመርካቶ ተቆጣጣሪዎችን በማንሳት በአዲስ መተካቱንም ተናግሯል።

ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘን ማንኛውም ሰው 100 ሺህ ብር እንደሚቀጣም አሳውቋል።

ቢሮው መርካቶን ጨምሮ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ያሉ አምራቾች፣ አስመጪዎችና ቸርቻሪዎች የትኛውንም ግብይት በደረሰኝ እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ ማለቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ገልጿል።

ነጋዴዎች ምን ይላሉ ?

በመርካቶ ያለው ችግር ውስብስብ ያለና ከላይ ጀምሮ መጥራት ያለበት ነው።

በተለይ ደግሞ የገቢዎች ተቆጣጣሪ የሚባሉት ያለ ገንዘብ ያለ ሙስና አይሰሩም።

ሆን ብለውም የማስጨነቅ ስራ በመስራት ከነጋዴው ገንዘብ የመቀበልን ተግባራ ስራቸው ያደረጉ እንዳሉ ይገልጻሉ።

ያለ ደረሰኝ ግብይት ተደረገ ተብሎም የገንዘብ ድርድር የሚያደርጉ ተቆጣጣሪዎችም አሉ።

ደረሰኝን በተመለከተ ቸርቻሪው ላይ ጣትን ከመቀሰር ከላይ ጀምሮ ያለውን ነገር ማጥራት እንደሚገባ ነጋዴዎች ጠቁመዋል።

#AddisAbaba #Merkato

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ሲጠበቁ የነበሩ ሁለት መመሪያዎች ፍትህ ሚኒስቴር ማጽደቁ ተሰምቷል።

መመሪያዎቹ " የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያ " እና "ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ድርጅቶች ቁጥጥር መመሪያ  "  ናቸው።

ሁለቱን መመሪያዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  በትላንትናው ዕለት መዝግቦ አጽድቋቸዋል።

የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያን በሚመለከት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተልህኩ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሰነደ ሙዓለ ነዋይን በሚመለከት ከዚህ ቀደም የተማከለ እና ሂደቱን የሚቆጣጠር ህግ እና ተቆጣጣሪ አካል ያልነበረ በመሆኑ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ማውጣት እና ግብይት በርካታ ችግሮች እንደነበሩበት ገልጸዋል።

በዚህ መሃል ለህዝብ የሚቀርቡ መረጃዎች ምንነት ፣ ለሚቀርቡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስዱ ሰዎች ማንነት፣ ሃላፊነት እና ግዴታቸው ምን ድረስ ነው፣ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ከወጣ በኋላ በዛ መንገድ የሚገኘው ገንዘብ ለምን ዓላማ እንደሚውል፣ አውጪዎች የሚኖርባቸው ተግባር እና ሃላፊነት ምንድነው የሚለውን ማወቅ ላይ ከዚህ ቀደም በነበሩ ህጎች ያለተዳሰሱ ስለነበር ገበያው በርካታ ችግሮች እንደነበሩበት ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም የካፒታል ገበያ አዋጅን መሰረት በማድረግ አዲሱ መመሪያ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

መመሪያው በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ለሽያጭ የሚቀርብበትን እና የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ግብይት የሚገዛበት ዝርዝር የያዘ የህግ ማዕቀፍ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከአሁን በኋላ ሁሉም ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ቀርበው መጽደቅ አለባቸው።

በዚህ ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላት የምዝገባ ሰነዳቸውን ለባለሥልጣኑ አቅርበው ማጸደቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የምዝገባ ሂደቱም ዝርዝር ሂደቶችን የያዘ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከሰነደ ሙዓለ ነዋይ ጋር የተያያዙ ማስታወቂያዎች የሚተላለፉት ይዘታቸው እና ለህዝብ ይፋ የሚደረጉበት መንገድ ባለሥልጣኑ ተመልክቶ ሲያጸድቀው ብቻ ይሆናል።

መመሪያው ካካተታቸው እና ከዘረዘራቸው ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ :-

1. የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ምዝገባ

2. ለኢንቨስተሮች መቅረብ ስላለበት የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ይዘት እና የአቀራረብ መንገድ ሂደት እንዲሁም ተያይዞ ስለሚመጣ ሃላፊነት።

3. ስለ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ማስታወቂያ ይዘት እና አቀራረብ እንዲሁም ስለሚያስፈልገው ፍቃድ።

4. የሰነድ ሙዓለ ነዋይ ሽያጭ እና ድልድል
አጠቃቀሙ እና ስራ ላይ ስለሚውልበት አካሄድ እና ሁኔታ።

5. አንድ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ አውጪ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ለህዝብ ሽጦ እንደ ህዝብ ኩባንያ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ በቀጣይነት ስለሚኖርበት ሃላፊነት እና የዚህ የህግ ጥሰቶች በቀጣይነት ስለሚያስከትሉት አስተዳደራዊ እርምጃዎች ይገኙበታል።

በዚህ መሰረት ከዚህ በኋላ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ካልተመዘገቡ ወይም በአዋጁ እና በመመሪያው ከዚህ ምዝገባ ነጻ ካልተደረጉ በቀር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሽያጭ መቅረብ አይችሉም።

በተጨማሪም ማንኛውም ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለህዝብ ለማቅረብ የሚፈልግ ኩባንያ ሰነዶችን ለህዝብ ከማቅረቡ በፊት ዝርዝር መረጃዎችን ያካተተ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ለባለሥልጣኑ ማቅረብ እና ማጸደቅ የሚጠበቅበት ሲሆን ይህንን ከማድረጉ በፊት ማስታወቂያ ማሰራትም ሆነ ከኢንቨስተሮች ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችልም።

መመሪያው በባለሥልጣኑ ገጽ ላይ ከተጫነበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

በመመሪያው የመሸጋገሪያ ድንጋጌ መሰረትም አሁን ላይ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን እያቀረቡ ያሉ ኩባንያዎች እና አስቀድመው ተሽጠው በአክስዮን ባለድርሻዎች እጅ ላይ የሚገኙ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን በሚመለከት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ መመዝገብ እንዳለባቸው አስቀምጧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በራስ ገዟ ሶማሌላድ ዛሬ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ህዝቡ ከጥዋት አንስቶ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ ድምጹን እየሰጠ ይገኛል። በምርጫው የአሁን ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ከአብዲራህማን ኢሮ እንዲሁም ከፋይሰል አሊ ዋርቤ ጋር ይፎካከራሉ። ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ተገንጥላ እራሷን እንደ ነጻ ሀገር የምትቆጥር ናት። ላለፉት በርካታ አመታት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ምንም ግንኙነት…
#UPDATE

አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " የሶማሌላድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን አሸነፉ።

የዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንዲሁም ፋይሰል አሊ ዋርቤ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

የኢሮ ፓርቲ ምርጫውን 63.92 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው። የተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ ፤ ኩልሚዬ ፓርቲ 34.81% ነው ያገኘው።

ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ተገንጥላ እራሷን እንደ ነጻ ሀገር የምትቆጥር ናት። ላለፉት በርካታ አመታት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ምንም ግንኙነት የላትም።

የራሷን መሪ / ፕሬዜዳንቶችን በምርጫ ስትመርጥ ኖራለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት🚨 " የጤና ተቋሙ ሳይፈርስ ከላይ ያሉ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ ቢያደርጉ መልካም ነው "  - ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በክልሉ ተፈጥሮ ከነበረው ጦርነት በፊት ለመድሃኒትና ለላብራቶሪ ግብዓቶች ይመደብለት የነበረው በጀት ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ነበር። በሆስፒታሉ የመድኃኒት እና የላብራቶሪ መመርመሪያ ግብዓቶች እጥረት ስለማጋጠሙ…
#Update

" መስሪያ ቤቱ መድኃኒት ለመግዛት ገንዘብ እያጠረው ነው " -የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት

የዓይደር ኮምፕረንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ካጋጠመው የመድኃኒትና የህክምና ግብዓቶች እጥረት ጋር በተያያዘ በሆስፒታሉ እና በታካሚዎች ዘንድ በርካታ ችግሮችን እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን ተቋሙ ባሉበት ተደራራቢ እዳዎች ምክንያት ችግሩን መቅረፍ ተስኖታል።

ሆስፒታሉ ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር ባለበት ከፍተኛ ያልተከፈለ እዳ ምክንያት ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።

በተቋሙ አጋጥሟል ለተባለ የመድኃኒቶች እጥረት ምክንያትም ያለው ውስን በጀት እና ያለበት ውዝፍ ተጠቃሽ ናቸው።

ካሉበት ችግሮች በተጨማሪ አንዳንድ መድኃኒቶች በመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩልም እያጡ መሆኑን ሆስፒታሉ ለቲክቫህ አሳውቋል። 

ሆስፒታሉ ላቀረበው ቅሬታ እና ስላልተከፈለው ከፍተኛ እዳ የአገልግሎቱን የመቀሌ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ገብረማርያምን አነጋግረናል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/TikvahEthiopia-11-19

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray 🔴 " ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ 🟠 " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት 🔵 " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል። የጊዚያዊ…
#Update

የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ወንጀል ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ ገፁ በሰጠው ማብራርያ ፤ " ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 :00 ሰዓት አካባቢ ከአክሱም ወደ መቐለ ከተማ በመኪና በመጓዝ ላይ የነበሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ የሚያጣራ ቡድን ተቋቁመዋል " ብሏል።

አጣሪ ቡድኑ ከፓሊስ እና ከፍትህ አካላት የተወጣጣ እንደሆነ ገልጿል።

የግድያ ሙከራ ወንጀሉ ተፈፅሟል ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፆች ከተሰራጨበት ደቂቃ ጀምሮ ጥብቅ የማጣራት ስራ መጀመሩ አብራርቷል።

ኮሚሽኑ የማጣራት ሂደቱ እንዲሳካ የህብረተሰቡን ትብብር ጠይቋል። የማጣራት ሂደቱ የሚጎዱ በማህበራዊ ሚድያ የሚነዙ ሁለት ፅንፍ የያዙ አሉባልታዎች እንዲቆሙ አሳስቧል።

የሚደርስበትን የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

የግድያ ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የማይቅነጣል ወረዳ ሲሆን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ማለታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia