TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EMA ከ600 በላይ የሕክምና ባለሙያዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ውይይት ሊያደርጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ገለጸ። የማኀበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለጸገ ማህበረሰብ እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መ/ቤቶች የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎች፣ ከማኀበሩ አባላት ጋር በመሆን ምክክር የሚያደርግበት ዓመታዊ…
#EMA

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ አባል ፤ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዕግስት መኮንንን ጋር ቆይታ  አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት መሰረታዊ የሚባሉ ጥያቄዎችን አንስቷል።

1ኛ. በጤና ተቋማት እየታዩ ያሉና ትኩረት የሚሹ ችግሮች ምንድን ናቸው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" አሁን በስፋት በዋነኝነት እንደተግዳሮት ሆኖ የሚታየው የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት መኖር ነው።

የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት በሚፈለገው ልክ ተቋማት  የሚጠበቅባቸውን ሥራ ለመስራት ትልቅ ተግዳሮት እየሆነ ነው። "

2ኛ. ማህበሩ #የጤና_ባለሙያዎችን ጉዳዮች ተደራሽ ማድረግ አንዱ ዓላማው እንደመሆኑ መጠን በደመወዝ እጥረት የጤና ባለሙያዎች ወደ ውስጥም ሆነ ውጪ አገራት እየፈለሱ (የትግራይ ክልል) መሆኑን በተመለከተ ማኅበሩ እንደማኀበር ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" እርግጥ ነው ይሄ ነገር ማኀበሩ እውቅና የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ከሥራ ማጣት ጋርም ተያይዞ፣ ከተለያዩ ችግሮች አንፃር የባለሙያዎች ፍልሰት እንዳለ እሙን ነው። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ እንደዚህ ነው የሚል ጥናታዊ ፅሑፍ አልሰራንም።

ግን ችግሩ እንዳለ፣ በጥልቀት አትኩሮት መሰጠት እንዳለበትም ለተለያዩ አካላት ግብዓት ስንሰጥ ቆይተናል።

ይሄ አገሪቱም ካለችበት የኢኮኖሚ ጉዳይ፣ ለጤና ሴክተሩ ከሚሰጠው ትኩረት አንፃር እጥረት አለ፣ መድረስ ያለብን ደረጃ ላይ አልደረሰንም። ይህ ባለበት ሁኔታ የመፍለሱ፣ ሥራ የማጣቱ ጉዳይ እየታዬ ስለሆነ እንደ አገር ያለው ችግር ነው ለዚህ የዳረገው። "

3ኛ. የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱ ሕሙማን መጉላላት፣ የቀጠሮ መንዛዛት ስለሚገጥማቸው በወቅቱ መታከም ሲገባቸው ከሕመማቸው ጋር ለመቆየት እንደሚገደዱ ሕሙማን በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" የታካሚዎች መጉላላት፣ በወቅቱ የሚፈለገውን የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት አጠቃላይ የሥርዓት ችግር ቢሆንም፣ ችግሩን ምን አመጣው ? በሚለው ጉዳይ ብዙ ነገሮች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ለምሳሌ፦ የሕክምና መሣሪያዎች ግብዓት እጥረት መኖር፣ ለጤና ሴክተር የሚሰጠው የበጀት እጥረት፣ ከዶላር ጋር ተያይዞ ያለው ችግር በቀጥታ ለዚህ ችግር አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ቁጥሩን ለመግለጽ ለጊዜው ባላስታውሰውም ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

እንደ አጠቃላይ በታካሚዎች፣ በሐኪሞች፣ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ውይይት የማኀበሩ 60ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በዚህ ወር ሲደረግ ይነሳል። ይበልጥ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። "

#TikvahEthiopiaAA

@tikvahethiopia