TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AI

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች የእርቃን ምስሎች ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው።

በደቡባዊ ስፔን ውስጥ የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎች ከእነርሱ እውቅና ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወሩ በኋላ ድንጋጤ ውስጥ ገብታለች ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

እርቃን ምስሎቹ የተሰሩት ሙሉ ልብስ ለብሰው የተነሱትን የታዳጊዎቹን ፎቶ በመጠቀም ነው።

በርካታ ምስሎቹ የተወሰዱትም ከታዳጊዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ነው።

ምስሎቹ ከተወሰዱ በኋላም አንድ ግለሰብ እርቃኑን ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምናባዊ ምስል የሚፈጥር መተግበሪያ በመጠቀም የታዳጊዎቹ ምስል እርቃን እንዲቀር ተደርጓል።

እስካሁን ዕድሜያቸው በ11 እና በ17 ዓመት መካከል የሚገኙ 20 ታዳጊ ሴቶች፣ የዚህ ድርጊት ሰለባ መሆናቸውን በመግለጽ በደቡብ ምዕራብ ግዛቷ ባዳጆዝ ውስጥ በምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ እና አቅራቢያው ሪፖርት አድርገዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩት ሐሰተኛ የእርቃን ምስሎች በታዳጊ ሴቶቹ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል።

የተወሰኑ ታዳጊዎች ከቤታቸው ለመውጣት እንደተሳቀቁ ተነግሯል።

ይህ ጉዳይ ወደ አደባባይ የወጣው ከታዳጊዎቹ ሴቶች መካከል የአንዷ እናት በሆነችው የማሕጸን ሐኪም ማሪያም አል አዲብ ምክንያት ነው።

አዲብ ማኅበራዊ ሚዲያዋን በመጠቀም ባወጣችው መልዕክት ምክንያት ጉዳዩ የስፔን ሕዝብ መነጋጋሪያ መሆን ችሏል።

አዲብ ታዳጊ ሴቶችንና ወላጆችን ለማረጋጋት ስትል በማኅበራዊ ሚዲያ ባጋራችው ቪዲዮ " የወጡት የAI ምስሎች የተፈጠሩት በበጋ ወቅት ቢሆንም ጉዳዩ ወደ አደባባይ የወጣው በቅርብ ቀናት ነው " ብላለች።

" ምን ያህል ሕጻናት ምስሎቹ እንደነበራቸው አናውቅም። ምስሎቹ የወሲብ ፊልም በሚጫንባቸው ገጾች ላይ ተጭነው እንደሆነም አናውቅም ነበር። ይህ ሁሉ ስጋት ነበረብን " ብላለች።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎችን ባማውጣት የተጠረጠሩ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 14 የሚደርስ ነው።

ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመረ ሲሆን ምስሎቹን በመፍጠር ሒደት ውስጥ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ #ዋትስአፕ እና #ቴሌግራም በማጋራት ተሳትፈዋል ያላቸውን ቢያንስ አስራ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ወንዶችን መለየቱን አስታውቋል።

መርማሪዎች ታዳጊ ወንዶቹ ሐሰተኛ ምስሎችን በመጠቀም ታዳጊ ሴቶቹን #በማስፈራራት ማግኘት የፈለጉት ነገር ስለመኖሩ ለማወቅ ምርመራ እያካሄዱ ነው።

#BBC

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

(ለተማሪዎች እና ለወላጆች)

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወር የሚቆይ የAI ሰመር ካምፕ የስልጠና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ መሳተፍ የሚችሉት የመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ናቸው።

ተማሪዎቹ ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ለተከታታይ 2 ወራት ለሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያተኩርባቸው ፦
➡️ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➡️ ሮቦቲክስ፣
➡️ ፕሮግራሚንግ፣
➡️ ማሽን ለርኒንግ
➡️ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ (IoT) እንደሆኑ ተገልጿል።

በስልጠናው መሳተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች ፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

በተጨማሪ እውቀትና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ፦

👉 www.aii.et/ethiopian-ai-summer-camp-2024-application-form-trainer-for-summer-camp/

👉 forms.gle/P2vAoZuWT7JgYQtT6 ላይ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

#AI #ETHIOPIA

@tikvahethiopia