TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"መደመር" የጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ መፅሃፍ በአዲስ አበባ ከተማ በሚሊኒያም አዳራሽ እየተመረቀ ይገኛል።

PHOTO: OBANI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Medemer የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በሚሊንየም አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው "መደመር" መፅሃፍ ምርቃት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀሳብ ማዕድ!

#ማዳመጥ #መረዳት #መናገር #መግባባት

በዓለማቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አዘጋጅነት የሚካሄደው ሁለተኛው የአክቲቪስቶች የውይይት መድረክ በቀነኒሳ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የሚዲያ ባለሞያዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በውይይቱ መጀመሪያ ላይ አዘጋጁ እንደተናገረው ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችና አክቲቪስቶችን አቀራርቦ ማወያየት የዝግጅቱ ዋነኛ ዓላማ ነው፡፡ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር አደረ አብደላ እንደገለጹት በአክቲቪስቶች መካከል በመደማመጥ ላይ ያተኮረ ሁሉም ሃሳቡን በእኩል ማካፈልና ከተቻለ የጋራ መግባባትን መፍጠር ካልሆነም ልዩነቶችን አቻችሎ ለሀገር ደህንነትና ሰላም በጋራ መቆም ይኖረባቸዋል ብለዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሌሎች እንዲያደምጡን ብቻ ሳይሆን እኛም ሌሎችን ማድመጥ የምንችልበትን መድረክ ማመቻቸት የዚህ ዓላማ ዋነኛው ዓለማ ነው በማለት አክለው ገልጸዋል፡፡ ፕሮግራሙ አካታች ለማድረግ ጥረት የተደረገ ሲሆን በዚህ ውይይት 12 አክቲቪስቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በመድረኩ የሚነሱ ሃሳቦችን እየተከታተልን እናሳውቃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Medemer #worabe

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በዶ/ር አብይ የተፃፈው የመደመር መፅሀፍ የምረቃ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው።

PHOTO: ABDURE/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Medemer #HAWASSA

በአሁኑ ሰዓት በዶ/ር አብይ አህመድ የተጻፈው የመደመር እሳቤ መጽሐፍ በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን አስተባባሪነት በሚሊንየም አዳራሽ በተዘጋጀው መድረክ በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳውና የሰላም ሚኒስትሪ ወ/ሮ ሙፌርያት እንድሁም የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተመረቀ ይገኛል።

PHOTO: ደግ ሰው/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
IDA'AMUU

የዶክተር አብይ አህመድ "መደመር" መፅሃፍ በቦረና ዞን፣ ያቤሎ እየተመረቀ ይገኛል።

PHOTO: Eb isa/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ''መደመር'' መጽሐፍ ምረቃ በአርባምንጭ!

PHOTO: ብርሽ ዘውዴ/TIKVAH-FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MEDEMER

በሀላባ ዞን የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ "መደመር" የተሰኘ መፅሐፍ በዛሬው እለት በደማቅ ስነ-ስረዓት ተመርቋል። መጽሐፉን የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ እና የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ (የክልሉ ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንዲሁም የደኢህዴን ማዕከላዊ ጽ/ቤት ከተማ ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ታምራት ከሀላባ አባቶች ጋር በጋራ በመሆን በይፋ ያስመረቁ ሲሆን በመድረኩ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶችና በርካታ የህብረተሰ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

PHOTO: MEHIR/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀሳብ ማዕድ!

አክቲቪስቶች ለሀገራዊ ጥቅም ምን አስተዋጽኦ ማድረግ እንችላለን?

አቤል ዋቤላ፦

"አክቲቪስቶች አንድ ላይ ብንሆን የፖለቲካ ስለልጣንን መግራት እንችላለን፡፡ ይህም ማለት አንድ ስልጣን ላይ ያለ ሰው ስልጣኑን ሲጠቀም ሁሉም አክቲቪስት በጋራ በመተባበር መኮነንና ስልጣንን በአግባቡ እንዲጠቀም ማስቻል ላይ በጋራ መስራት እንችላለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉት ክፍተቶች ሁሉም አክቲቪስቶች ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡ በዚህ መተባበር እንችላለን፡፡"

ታምራት ነገራ፦

"አሁን ያለው ስርዓት ሰዎች የመጨረሻውን ጥግ ይዘው እንዲቆሙና በዛ ትርፋማ እንደሚሆኑ ማሰባቸው ነው፡፡ ብሔራዊ መግባባት የሚባል ነገር የለም ሁሉም ስርዓት ጽንፈኛ የሚያደርግ ነገር ነው ያለው፡፡ ከዛም በላይ ስርዓትና ህግ ማስጠበቅ ወደ ማይቻልበት ሁኔታ እየሄድን ስለሆነ ሰዎች ስለ ጋራ መግባባት ሲያስቡ ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው የሚችል ነገር ሳይሆን ስለጎጥ ሲታሰብ ነው ተጠቃሚ እየሆነ ያለው ስለዚህ ስርዓቱ በራሱ ሀገራዊ ተግባቦት እንዲሆን አያስችልም፡፡"

ፍጹም፦

"አዲስ አበባን እንደ ኢትዮጵያ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ ወጣ ብለን ማህበረሰቡን እንመልከት ለጋራ ምንቆምበት ነገር ብንቆም መግባባት ይፈጠራል፡፡"

ዶ/ር እንዳለማው፦

"እኩልነት ምንድነው የሰውዓዊ ክብር ምንድነው በነዚህ ነገሮች ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብንሰብክበት ግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት ቢቻል ቢያንስ በዚህ ላይ በጋራ መስራት እንችላለን፡፡"
የቀጠለ...

ኪያ፦

"ሶሻል ሚዲያው ላይ ላለው አክቲቪስት የፖለቲካ ታሪካችን ውጤት ነው ብዬ ነው ማስበው፡፡ ምን አስተዋጽዖ ማድረግ ችላሉ ለሚለው ግን ብዙ ማድረግ ይችላሉ ባይ ነኝ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸውን ለመልካም ዓላማ መጠቀም ይችላሉ፡፡ የአክቲቪስቶች ስራ ሙሉ ሰዓት መቃወም ብቻ አይመስለኝም ሀገራዊ ስራዎች ላይ ሰላም ላይ መስራት ይቻላል።"

አሁን ላይ የሚታየው የሚዲያና የአክቲቪዝም መደበላለቅ እንዴት ትመለከቱታላችሁ፦

• ሚዲያና አክቲቪዝም መለያየት ያለባቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ከአክቲቪዚሙ ይልቅ ለፖለቲካ አቋም ያላቸው አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች በዝተዋል በግሌ ይሄ መሆን አለበት ብዬ አላምንም (ታምራት )

• ፐብሊክ ሚዲያው ነጻ መሆን አለበት፡፡ የመንግስት የአቋም መግለጫ ሙሉውን የሚያነብ ሚዲያ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስብሰባ እንኳን ሳይጠቅስ ያልፋል፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ (ዶ/ር እንዳለማው)

• አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ሚዲያ ኖሮ አያውቅም፡፡ አሁን ላይ የሀሰት ዜናዎችን እያሰራጩ ያሉት የመንግስት ሚዲያዎች ናቸው፡፡ አሁንም ቢሆን ሶሻል ሚዲያውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም አለብን በሚለው ላይ ተስፋ ይታየኛል፡፡ (ኤቤል)

• በተለይ ዋና ዋና አክቲቪስቶች ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ከሁሉም ክፍል ያሉ ህዝባችንን እንወክላለን ያሉ ተሰብስበው በፈቃደኝነት ተሰብስበው ለራሳቸው ህግ ቢያወጡ ጥሩ ነው፡፡ በተረፈ ግን እንደ ሀገር ያለንበትን ጉዳይ አልተረዳነውም ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ እያገናዘብን እንቀሳቀስ እንጂ በዲሞክራሲና በፕሬስ ሚዲያ ሩቅ የደረሱ ሀገሮችን እንደ ምሳሌ እየጠቀስን መነቃቀፍ የትም አያደርሰንም። (ኪያ)

• ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ብሔርና እንደ ፖለቲካ የተመሰረተ ሚዲያ እንጂ ነጻ ሚዲያ የለም፡፡ አሁን ላይ ስለ ሚዲያ ማውራት አንችልም። (አልበርቱ ቢጠና)

#ቲክቫህ
#HARAR

በሀረር ከተማ በነበረው የ"መደመር" መፅሃፍ ምርቃ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተገኝተው ነበር።

PHOTO: Ablity/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia