#PMOEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሄሰን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25,000 ዩሮ ለመልካም ወጣት አገልግሎት ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ተከትሎ፣ ዛሬ ከሰዓት ዮናታን አክሊሉን አግኝተው ቃል የገቡትን ገንዘብ አስረክበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወርሀ መስከረም ዮናታን አክሊሉ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ለመደገፍ እየሠራ ላለው የላቀ ሥራ እውቅና መስጠታቸው የሚታወስ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

October 18, 2019
#EPRDF
ኢሕአዴግ የውህደት «አጀንዳ ገና በጥናት ውጤቱ ላይ ውሳኔ ያገኘበት ደረጃ ላይ አልደረሰም። የመጨረሻ የውህደት ውሳኔም አሰራሩን ጠብቆ ወደፊት የሚታይ ይሆናል» ብሏል። ግንባሩ በዛሬው ዕለት ሕወሓት ከቀናት በፊት በውኅደት ጉዳይ ላይ ያወጣውን መግለጫ ኮንኗል። ኢሕአዴግ በዛሬው መግለጫው ሕወሓት «በድርጅቱ ስም በሚወጡ መግለጫዎችም ሆኑ አንዳንድ አመራሮች በሚሰጧቸው ማብራሪያዎች የውህደቱን ሃሳብ አዲሱ የለውጥ አመራር በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲል እንዳመጣው አስመስሎ ለህዝብ ማቅረብ የተሳሳተ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም» ብሏል።
Via ጋዜጠኛ እሸት በቀለ

#EPRDF | የኢሕአዴግ መግለጫ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ትናንት ከተጠናቀቀ ከአንድ ቀን በኋላ መውጣቱ በግንባሩ አባል ድርጅቶች ዘንድ ያለውን የኃይል አሰላለፍ በግልፅ ይጠቁማል። ኢሕአዴግ 28 ዓመታት ገደማ የተመራበትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሚያቀነቅኑት የመደመር ጽንሰ ሐሳብ እንደሚተካ ኦዲፒ አስታውቋል። ሕወሓት በአንፃሩ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፈቀቅ የሚል አይመስልም።
Via ጋዜጠኛ እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ጋዜጠኛ እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
October 18, 2019
ከዊንጌት እስከ ጀሞ የሚደርሰውና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊሰራ የታቀደው ፈጣን የአውቶቡስ መንገድ የፊታችን ጥር ወር አጋማሽ ላይ እንደሚጀመር የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
October 18, 2019
#HARAR #SEMERA
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመደመር ፍልስፍና መጽሐፍ በአፋር እና ሐረሪ ክልሎች ደረጃ ነገ በሰመራና ሐረር ከተሞች እንደሚመረቅ ተገልጿል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SOMALI #AFAR
የአፋር ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና የሶማሌ ክልል አቻቸው አቶ ሙስጠፋ መሐመድ ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ ጋር ከተወያዩ በኋላ ሁለቱ ክልሎች የሚዋሰኑባቸውን አካባቢዎች ከፌድራል መንግሥት ጋር በመተባበር ከግጭት ነፃ ለማድረግ መወሰኑን ተናግረዋል። አቶ ሙስጠፋ እንዳሉት «የሕዝብ ጥያቄና የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በሕግ አግባብ እና በሕገ-መንግሥቱ መሰረት እንዲፈቱ» አቅጣጫ ተቀምጧል።
ሁለቱ ርዕሰ-መስተዳድሮች አፋር እና ሶማሌ በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ግጭቶች ያገረሹበትን ምክንያትም ሆነ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ አልተናገሩም። «በዚህ ግጭት ምክንያት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚዳዳቸው ኃይሎች መኖራቸው ግልፅ ነው። ከሰሞኑም ሲታይ የነበረው ይኸው ሁኔታ ነውe። የተለያየ ስያሜ በመስጠት የግጭቱን ገፅታ ለመቀየር የሚደረጉ ነገሮች አሉ። እነዚህ ጠቃሚ አይደሉም» ያሉት አቶ ሙስጠፋ መገናኛ ብዙኃን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። አቶ አወል በበኩላቸው «ለውጪዎቹ መሳሪያ መሆን አያስፈልግም» ሲሉ ተደምጠዋል።
Via DW
Video: FBC

ይህ ግልፅ አቋማችን ነው[TIKVAH-ETHIOPIA]
የሀገራችን ሁኔታ ያሳበናል!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፦
📢በአንድ ሀገር የሚኖሩ የራሳችንን ወገኖች እየሰደብንና እያንቋሽሽን፣ ሀሳባችንን የሚቃረኑትን በሙሉ ጠላት እያደረግን፣ የሰዎችን ማንነት እየነካን፣ የሰዎችን ክብር እየነካን ሀገር እንገነባል፣ "አንዲት ኢትዮጵያ፤ ታላቋ ኢትዮጵያን" የሚሉትን ሀሳብ በፍፁም አንደግፈውም። ሰው በሰውነቱ ብቻ ባልተከበረባት ሀገር ስለየትኛው አንድነት እንደሚወራም ጨርሶ አይገባንም።
📢ሀገር በብሽሽቅ፣ በስድብ፣ በመዘላለፍ፣ በጥላቻ፣ በቂም በቀል፣ በክፋት እንደማይገነባ በፅኑ እናምናለን።
📢በአንድ ሀገር እየኖርን አንዱን ጠላታችን፤ አንዱን ወዳጃችን የሚሉትን አባባል በፍፁም አንቀበለውም። የጠላትነት ስሜት ወደፊት ሀገር #መበተኑ አይቀርም።
📢አንዱን ወገን አግልሎ፣ ሰድቦ፣ አንቋሾ፤ አንዱን ወገን ወዶ፣ ክቦ፣ የሚገነባ ሀገር የለም። ሁሉም ዜጋ በእኩል ሊከበር ሊወደድ ይገባል። የተለየ አመለካከት ያላቸው ወገኖችም እኩል ክብር ሊሰጣቸው ይገባል።
📢ሰዎችን በብሄራቸው መደበል፣ መግፋት፣ አድሎ መፈፀም፣ ክብራቸውን መንካት ለሀገር መተራመስ ትልቁን ድርሻ የሚወስድ በመሆኑ ይህን መሰል ድርጊቶችን እንቃወማቸዋል። አሁንም እንደግመዋለን ሰው በሰውነቱ ተከብሮ ይኑር!
📢የሚያጠፉ ሰዎችን በደቦንና በጅምላ እየሰደብን፣ እያንቋሸሽን፣ እየዘለፍን የምናፈርሰው እንጂ የምንገነባው ሀገር አይኖርም። ሀገራችን ኃላቀር፣ በብዙ ነገሮች የተጎዳን፣ ንቃተ ህሊናችንም ይሄን ያህል ያልዳበር በመሆኑ ችግሮችን መፍታት ያለብን በፍቅር እና በብልሃት መሆኑን እናምናለን። ጥፋት የሚያጠፉ ሰዎችን በፍቅር አስተምረን መመለስ ካልቻልን ለሀገራችን እንዲመሆን እኛም ከተጠያቂነት አንድንም።
📢ከየትኛውም ወገን ይሁኑ የተወሰኑ ሰዎችን በመስደብና በመግፋት፣ ለውጥ ሊመጣ አይችልም። በዚህ ሂደት ሰዎችን እየገፋናቸው ፅንፍ እንዲይዙ ከማድረግ ውጪ ምንም ለውጥ አናመጣም። ስለሆነም ሰዎችን በቀና መልኩ በመመልከት እንደራሳችን ሰዎች ማቅረብ፣ ፍቅር መስጠት ይገባል ብለን እናምናልን። የማንስማማበትንም ሀሳብ በፍቅር መግለፅ ይኖርብናል። የትኛውም ሰው እየሰደብነው፤ ክብሩን እየነካነው፣ እያንቋሽሽነው መልካም ሊያስብ፣ከጥፋቱ ሊማር፣ አብሮን ሊያወራ፣ በጋራ ሊያስብ አይችልም።
📢በሁሉም አቅጣጫ እየተሰዳደብን ሀገራችንን የከፋ ችግር ውስጥ እየከተትናት እንገኛለን፤ በአንድ በኩል በመንግስት በኩል የሚታዩት ሁኔታዎች እያሰጉን ይገኛሉ፤ በሌላ በኩል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከቀን ወደቀን እየጨመረ የመጣው ጎራ ለይቶ መሰዳደብ ነገ መሬት ሲወርድ ሀገራችንን ምን ሊያደርግብን ይሆን ብለን እንሰጋለን። ስለሆነም በዚህ ፈታኝ ወቅት ሁሉም ዜጋ ልዩነቱን ወደጎን ትቶ በፍቅር፣ ተደጋግፎ ይህን ፈታኝ ጊዜ ሊያልፍ ይገባል እንላለን።
📢ከዛና ከዚህ ሆነው/በተልይም በብሄ/ ሲሰዳደቡ የሚውሉ፤ አካላት በዚህ ወቅት ከዚህ ድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ነገ ይህቺ ሀገር ለምትገባባት መከራ እነሱም ተጠያቂ መሆናቸውን ሊውቁት ይገባል።
📢እኛ የዛሬይቱ የኢትዮጵያ ልጆች ዜጎች ያለስጋት፣ ያለፍርሃት የሚኖሩባትን ለሁሉም ተስማሚ የሆነች ሀገር የመገንባት ኃላፊነት አለብን።
ለሁላችንም የምትስማማውን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ፦
•መከባባር፣መዋደድ፣መተሳሰብ ያስፈልጋል።
•ካለፉ ታሪኮች መልካሙን በመውሰድ ማጎልበት፤ ከጥፋቶች በመማር እንዳይደገሙ ተማምኖ መዝጋት ያስፈልጋል!
የቲክቫህ ቤተሰቦች እነማን ናቸው? የቲክቫህ ቤተሰቦች TIKVAH-ETH የቴሌግራም ገፅን የተቀላቀሉ በሙሉ የቤተሰቡ አባላት ናቸው።
ከላይ ያሉት መልዕክቶች የተላለፉት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተስቦቻችን ተውጣጥቶ ነው። እኔም ሀሳብ አለኝ ያምትሉ ሌሎች የቤተስሰባችን አባላት ይህን Bot ተጠቀሙ👉 @TikvahEthiopiaBot
አጠቃቀሙን ለማታውቁን ሊንኩን ኣንዴ ይንኩት(@TikvahEthiopiaBot፤ በመቀጠለም start ይበሉትና መልዕክቶን ፅፈው ይላኩ።

🔖እናስተዋዉቅዎ!
Homeቤት interior design ለመኖርያ ቤት ለአፓርትመንት ለሆቴል ለ ኦፊስ እንዲሁም ለተለያዩ ሱቆች የ ኢንቴሪየር ዲዛይን አገልግሎት እንሰጣለን ይደውሉልን በስራችን ይረካሉ!
ለበለጠ መረጃ📱
0912637328
0931180968
Facebook page :https://www.facebook.com/Home-ቤት-Interior-Design-Works-187333958428843/
አድራሻ : መገናኛ ቤቴሌሄም ፕላዛ 5ኛ ፎቅ ቤሮ ቁጥር 526
☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ! #ETHIOPIA☀️

October 19, 2019
Forwarded from TIKVAH-SPORT
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሽልማታቸውን ተቀበሉ. . .
ከሳምንታት በፊት ምርጡ አለም አቀፉዊ የሩጫ ውድድር በሚል ዘርፍ በአሸናፊነት የተመረጡት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያዎች በትናንትናው ምሽት በለንደን የሽልማቱ አዘጋጅ ከሆኑት ከ Let's do this እጅ ሽልማታቸውን መቀበል ችለዋል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Via Great Ethiopian Run
@tikvahethsport @GoitomH @kidusyoftahe

የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ በተያዘው የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 113 በተለያዩ ቁልፍ የሀገሪቱ ተቋማት እና መሰረተ-ልማቶች ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች እና ሙከራዎች ተከስተዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
October 19, 2019
#ዛሬ
በአለማቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አዘጋጅነት የሚካሄደው ሁለተኛው የአክቲቪስቶች የውይይት መድረክ ዛሬ ይካሄዳል፡፡ በዚህ መድረክ የሚነሱ ሀሳቦችን ለእናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

"አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን"በቤይሩት ነዋሪ ኢትዮጵያውያን
.
.
ባለፉት ሰባት ወራት ለሥራ ወደ ሌባኖስ ካቀኑ #ኢትዮጵያዊያን መካከል ሰላሳ አራቱ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን እንዳጡ በሊባኖስ ያሉ የኢትዮጵያዊያንና ሌሎች የበጎ አድራጎት ማህበራት ይፋ አደረጉ።
ለኢትዮጵያዊያኑ ህይወት መጥፋት በአብዛኛው እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው በአሰሪዎቻቸው በሚፈጸምባቸው አሰቃቂ ግፍና ጥቃት ሳቢያ ራሳቸውን በማጥፋት እንዲሁም ካሉበት ኢሰብዓዊ የስቃይ ኑሮ ለማምለጥ በሚደርጉት ትግልና ጥረት እንደሆነም ተገልጿል።
ይህ ይፋ የሆነው በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እየገጠማቸው ያለውን አስከፊ ችግር በተመለከተ "መንግሥት የኢትዮጵያዊያን ሰራተኞችን ሞትና ስቃይን ለማስቆም" አፋጣኝ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በጠየቁበት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ላይ ነው።
"አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን"
"አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን" በማለት በደብዳቤያቸው ላይ ያሰፈሩት ኢትዮጵያዊያኑ በአገሪቱ ያለው ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለዜጎቹ ደህንነትና መብት እየሰራ ባለመሆኑ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ በአጽንኦት ጠይቀዋል። "በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ስላለው ግፍና ሰቆቃ በይገባኛል ስሜት አገርን ወክሎ በመንቀሳቀስ ረገድ በሌባኖስ ያለው የኢትዮጵያ ቆንስላ ሙሉ ኃላፊነትም ሆነ ግዴታ ቢኖረውም፤ እውነታው ግን ፍጹም ከዚህ የራቀ ነው" በማለት በደብዳቤያቸው ላይ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-19
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ

#MEDEMER በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተፃፈው “መደመር” መፅሃፍ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከ30 በላይ ከተሞች ነው ዛሬ የሚመረቀው። መጽሀፉ ከሚመረቅባቸው ከተሞች መካከል በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ እና ሀረር ከተሞች ይገኙበታል። በአዲስ አበባ የመፅሃፉ ምረቃ በሚከናወንበት ሚሌኒየም አዳራሽ እንግዶች በመግባት ላይ ይገኛሉ። መጽሃፉ በአንድ ሚሊዮን ቅጅ በአማርኛ፣ እንግሊዝኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎች በኢትዮጵያና አሜሪካ አገር ነው የታተመው። ከመጽሃፉ የሚገኘው ገቢ ሙሉ ለሙሉ በአገሪቱ ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል መሆኑም ታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
October 19, 2019
#መደመር_መጽሐፍ
#በድሬዳዋ
#ዛሬ_ይመረቃል
በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈው ‘’መደመር ’’ መጽሐፍ ዛሬ ጥቅምት 8 በኢትዮጵያና በአሜሪካ በሚገኙ 20 ከተሞች የሚመረቅ ሲሆን ድሬዳዋም የዚህው መረዓ ግብር አንዱ አካል ነች። በመደመር መጽሐፍ በአማርኛ ፣ ኦሮምኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተፃፈ እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ቅጂዎችም የታተመ ሲሆን ይህ መጽሐፉ 300 ብር ዋጋ የተቆረጠለት እና ከሽያጩ የሚገኘው ገቢም በአገሪቷ ላሉ ትምህርት ቤት ግንባታ ይውላል ተብሏል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመጽሐፉ ይዘት ዙሪያ ማብራሪያና ትንተና ይሰጥበታልም ተብሎ ይጠበቃል።
PHOTO: #ተርቢኖስ_ዘደብረ_ሃይል

IDA'AMUU
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተፃፈው “መደመር” መፅሃፍ ምረቃ በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተካሄደ ነው። መጽሃፉ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ፣ ጅማ ከተማ፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን ደረጃ ነቀምቴ ከተማ እና በሌሎች ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ባለው የመጽሃፍ ምርቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። እንዲሁም በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው “መደመር” መፅሃፍ ምረቃ ላይም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
Via FBC