#MEDEMER በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተፃፈው “መደመር” መፅሃፍ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከ30 በላይ ከተሞች ነው ዛሬ የሚመረቀው። መጽሀፉ ከሚመረቅባቸው ከተሞች መካከል በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ እና ሀረር ከተሞች ይገኙበታል። በአዲስ አበባ የመፅሃፉ ምረቃ በሚከናወንበት ሚሌኒየም አዳራሽ እንግዶች በመግባት ላይ ይገኛሉ። መጽሃፉ በአንድ ሚሊዮን ቅጅ በአማርኛ፣ እንግሊዝኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎች በኢትዮጵያና አሜሪካ አገር ነው የታተመው። ከመጽሃፉ የሚገኘው ገቢ ሙሉ ለሙሉ በአገሪቱ ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል መሆኑም ታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Medemer የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በሚሊንየም አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው "መደመር" መፅሃፍ ምርቃት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Medemer #worabe
በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በዶ/ር አብይ የተፃፈው የመደመር መፅሀፍ የምረቃ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው።
PHOTO: ABDURE/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በዶ/ር አብይ የተፃፈው የመደመር መፅሀፍ የምረቃ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው።
PHOTO: ABDURE/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Medemer #HAWASSA
በአሁኑ ሰዓት በዶ/ር አብይ አህመድ የተጻፈው የመደመር እሳቤ መጽሐፍ በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን አስተባባሪነት በሚሊንየም አዳራሽ በተዘጋጀው መድረክ በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳውና የሰላም ሚኒስትሪ ወ/ሮ ሙፌርያት እንድሁም የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተመረቀ ይገኛል።
PHOTO: ደግ ሰው/TIKVAH FAMILY/

#MEDEMER
በሀላባ ዞን የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ "መደመር" የተሰኘ መፅሐፍ በዛሬው እለት በደማቅ ስነ-ስረዓት ተመርቋል። መጽሐፉን የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ እና የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ (የክልሉ ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንዲሁም የደኢህዴን ማዕከላዊ ጽ/ቤት ከተማ ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ታምራት ከሀላባ አባቶች ጋር በጋራ በመሆን በይፋ ያስመረቁ ሲሆን በመድረኩ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶችና በርካታ የህብረተሰ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
PHOTO: MEHIR/TIKVAH FAMILY/