TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GAMBELA

ከጋምቤላ ከተማ 38 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ዛሬ በቁጥጥር ሥር ዋሉ። የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቶው አኮት እንደገለጹት መሣሪያዎቹ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በክልሉ ጸጥታ ኃይል፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት ለሦስት ቀናት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ነው።

የጦር መሣሪያዎቹና ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት  ከአንድ ግለሰብ ቤት ኮድ 3 ሠሌዳ ቁጥር ቁጥር አዲስ አበባ 55966 በሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር ነው። በክልሉ እየተስፋፋ ያለውን ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር ለመግታት የክልሉና የፌዴራል ጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት ላይ  መሆናቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኡቲያንግ ኡቻን እንተናገሩት ክልሉ ድንበር ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር መበራከቱን ተናግረዋል። ችግርን ለመካለካል በሚደረገው ጥረት ሕዝቡና  ጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ጥረት አመስግነው፣ በቀጣይም ቁጥጥሩ ይጠናከራል ብለዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዩጋንዳ አቻው ተሸነፈ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ከዩጋንዳ አቻው ጋር በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፏል። በመጀመሪያው አጋማሽ በተቆጠረበት አንድ ግብ ነው የኢትዮጵያ የወንዶች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የተሸነፈው።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ከጅግጅጋ እስከ ሀረሙከሌ መገንጠያ 104 ኪ.ሜ የሚረዝመው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ የግንባታ ስራ ጥቅምት 02/ 2012 ዓ.ም በይፋ ተጀመረ፡፡ የመንገዱ ግንባታ በብር 1,551,507,344.53 (አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ አምሳ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ አርባ አራት) የሚፈጅ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የግንባታ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነዉ። ቻይና ሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮረፖሬሽን (China Civil Engineering Construction Corporation (CCECC) ጨረታዉን አሸንፎ ወደ ስራ የገባዉ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራዉን የሚያከናዉን ኤስ.ጂ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ኃ.የተ.የግ.ማ. (S G Consulting Engineers PLC) ነዉ፡፡

Via ERA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SRIYA

ቱርክ በሰሜን ሶሪያ እየፈፀመች በሚገኘው ጥቃት ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ከአይ ኤስ አባላት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ከካምፕ ማምለጣቸውን የኩርድ አመራሮች ገለፁ፡፡ የአይ ኤስ አባላት የቅርብ ሰዎች የሆኑ እስረኞች ቱርክ ጥቃት እየፈፀመችበት በሚገኘው አከባቢ የሚገኘውን ኢን ኢሳ የስደተኞች መጠለያ መግቢያ ጥቃት እንደፈፀሙበት ተነግሯል፡፡ መረጃዎችን የሚከታተሉ ተቋማ 100 የሚሆኑ የአይ ኤስ አባላት የቅርብ ሰዎች ማምለጣቸውን የሚገልፁ ቢሆንም የኩርድ ሃላፊዎች ግን ከ800 በላይ የሚሆኑ የውጭ ዜግነት ያላቸውና ከአይ ኤስ አባላት የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች አምልጠዋል ነው የሚሉት፡፡

Via BBC/FBC/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ዛሬ በአዲስ አበባ ሊደረግ ታስቦ ከነበረ ሰልፍ ጋር በተያያዘ በትላንትናው ዕለት የታሰሩ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች መለቀቃቸው ለመስማት ተችሏል።

በተጨማሪ ደግሞ ቢቢሲ የሰራውን ዘገባ ይህንን በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ETH-10-13-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EGYPT #ETHIOPIA

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገውን ድርድር እንደገና ለማስጀመር ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቅርቡ እንደሚገናኙ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት በአገራቸው ቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ ጋር በሩሲያ እንደሚገናኙ አስታውቀዋል።

አል-ሲሲ ከጠቅላይ ምኒስትሩ ጋር የሚገናኙበትን ትክክለኛ ቀን ባይገልጹም ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ ጥቅምት 12 ቀን በሶቺ ከተማ የሚካሔደውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በተባባሪ ሊቀ-መንበርነት ይመራሉ። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር ላይ ያደረጓቸው ድርድሮች ያለ ውጤት ተበትነዋል።

ባለፈው መስከረም በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የድርድሩ ፈቅ አለማለት ለቀጣናው መረጋጋት ሥጋት ሆኗል ያሉት ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ከፍትኃዊ እና ሚዛናዊ ስምምነት ለመድረስ ዓለም አቀፍ አሸማጋዮች ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ «የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ኢትዮጵያ እና ሱዳን የማይቀበሉት እና ተገቢ ያልሆነ» በማለት ውድቅ አድርጋለች።

Via DW
PHOTO: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

የአፋር TIKVAH-ETH ቤተሰቦቻችን፦

በትናንትናው እለት የጁቡቲ ሠርጎ ገብ ታጣቂዎች በአፋር ክልል የአፋምቦ ወረዳ ነዋሪዎች በተኙበት ጨለማን ተገን በማድረግ ጥቃት አድርሰዋል። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ዛሬ ጥዋት የአፋር አርብቶ አደሮች መልሶ በማጥቃት በከፈቱት ተኩስ ከታጣቂዎቹ በርካታ የፈረንሳይ ጦር መሳሪያ መማረክ እንደቻሉ ስለሁኔታው የሚከታተሉ የአፋር አክቲቪስቶች ገልፀዋል። በጥቃቱ ከሞቱ ታጣቂዎች በርካታ የሠነድ ማስረጃዎችን ማግኘት እንደቻሉም ተነግሯል። በአፋር የሚገኙ TIKVAH-ETH ቤተሰቦቻችን አሁን የአፋርን ህዝብ እየገደለ እና እያጠቃ የሚገኘው ከጎረቤት አገራት የሚገቡ ሠርጎ ገቦች ናቸው፤ አሁንም ድምፃችን ይሰማ ብለዋል።

TIKVAH ETH FAMILY

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ቱኒዚያኖች አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ድምፅ እየሰጡ ነው ፤በመጨረሻው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወደ ፖለቲካው አዲስ የገቡ ተፎካካሪዎች ናቸውም ተብሏል፡፡ የንግድ ሰው የሆኑት ካቢል ካሩይ እና በጡረታ የተገለሉት የቀለም ሰው ካኢስ ሰይድ ለፕሬዝዳንትነት እየተወዳደሩ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#WolaitaSodo

ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ በወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ነዋሪ ወጣቶች ገለጹ፡፡ በከተማው በሁለት ወጣቶች መካከል በግል ጸብ መነሻነት የተከሰተው አለመግባባት እንዳይስፋፋ በእርቅ መፈታቱን የዞኑ ወጣቶች ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በእርቅ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች በሰጡት አስተያየት ስሜታዊነት ግለሰብን ብቻ ሳይሆን ቤተሰብን፣ አከባቢንና ሀገርን ለጉዳት እንደሚዳርግ ገልጸዋል፡፡ ነገሮችን በሰከነ መንፈስና በመቻቻል ማየት ፍርሀት ሳይሆን አርቆ አስተዋይነት መሆኑን አመላክተው አለመግባባትን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህል እንዲሰርጽ ተግተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-13-4

📹16 MB

Via Wolaita Zone Youth League

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIGJIGA

”ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተበረከተው ሽልማት #ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰጠ ትልቅ ክብር ነው” ሲሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ሽልማት በማግኘታቸው ”የእንኳን ደስ አልዎ!” ሰልፍ በጅግጅጋ ስታዲዬም ዛሬ ተካሂዷል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት “ሰዎች 50 ዓመታት ስልጣን ላይ ቆይተው የማያገኙትን ዓለም አቀፍ ሽልማት ክብር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በማግኘታቸው እጅግ ተደስቻለሁ” ብለዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

መደበኛ የክፍያ ጉብኝት ከነገ ሰኞ ይጀምራል!

ከነገ ሰኞ ማለትም ከጥቅምት 3 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር እንዲሁም በቪአይፒ (VIP) 1 ሺህ ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት ይችላል።

የአንድነት ፓርክን ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲኖርበት በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመሁኔታዎች ካላሟሉ ፓርኩን መጎብኘት አይችሉም።

ጎብኚዎች ይዘው መምጣት የሌለባቸው ነገሮች፦

- ስለት
- ተቀጣጣይ ቁሶች
- የጦር መሳሪያዎች
- ምግብ መጠጦች እና ጣፋጭ ነገሮች
- ማስቲካ
- የመዋቢያ ቁሶች
- የግል ካሜራዎች
- ስልኮች ታብሌቶች እና ማንቸውንም የምስልና ድምጽ መቅረጫ መሳሪያዎችን
- ሲጋራ እና አደንዛዥ ዕጾች

በፓርኩ ውስጥ ማድረግ የተከለከሉ ተግባራትና ባህሪያት፦

- መጮህና መረበሽ
- ከአስጎብኚ ውጪና ከተመደቡበት የጉብኝት ቡድን ውጪ መንቀሳቀስ
- በታሪካዊ ህንጻዎቹ ላይ መደገፍ
- ቅርሶችንና እንስሳትን መነካካት
- እንስሳትን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ መቅረብ
- እንስሳትን መመገብ
- እንስሳትን ማስቆጣት (ጠጠር መወርወር፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ ማስፈራራት፣ አላስፈላጊ ድምጽ ማውጣት)
- ከተቀመጡ የቆሻሻ ማስወገጃ እቃ ውጪ ቆሻሻ መጣል
- ሲጋራና ሌሎች አደንዛዥ እጾችን መጠቀም
- የቤት እንስሳትን ይዞ መምጣት
- መንገድ ከተበጀለት ዉጪ መራመድ እና አጥሮችን ከልክ በላይ መጠጋትም ሆነ መደገፍ
- ማንኛዉንም በፓርኩ የሚገኝ የኤሌትሮኒክስ ቁስ ያለፍቃድ መንካት

#አንድነት_ፓርክ
#UnityPark

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አስራ ሁለተኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ አላማችን የብዝኃነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ እንደሚከበር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 3 የተቀመጠውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ትርጓሜ መሰረት በማድረግ የወጣ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 እንዲሁም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ተደንግጓል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኩርዶች የአይኤስ ታጣቂዎችን አስሮ ማቆየት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ አይሆንም አሉ። በሰሜን ሶሪያ በቱርክ ጦር ጥቃት እየተሰነዘረባቸው የሚገኙት ኩርዶች በቱርክ የሚፈጸመው ጥቃት የሚቀጥል ከሆነ የአይኤስ ታጣቂዎችን አስሮ የማቆየቱ ነገር ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ አይሆንም ብለዋል።

በኩርዶች የሚመራው የሶሪያ ዲሞክራቲክ ኃይል በአሁኑ ወቅት በሚቆጣጠራቸው ስፍራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የአይኤስ ወታደሮችን አስሮ ይገኛል። ቱርክ ከቀናት በፊት በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ ወታደራዊ እርምጃ መውሰዷን ተከትሎ በኩርዶች ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ስፍራዎች ከፍተኛ ጉዳቶችን እያስተናገዱ ነው።

ቱርክ እየወሰደች ባለችው ወታደራዊ እርምጃ እስከ አሁን ቢያንስ 50 ሲቪሎች መሞታቸው ተነግሯል። ቱርክ ኩርዶችን አሸባሪ በማለት የምትፈርጅ ሲሆን፤ "ደህንነቱ የተረጋጋጠ ቀጠና" ለመፍጠር ከድንበሯ 30 ኪሎ ሜትሮችን ርቃ ወደ ሶሪያ በመግባት ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደች ትገኛለች።

Via BBC AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ በ7 ወር ውስጥ የሰባት እጥፍ ጭማሪ ማሳየቱ በጥናት ተረጋገጠ!

ከጥር 1/ 2011 እስከ መስከረም 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ በአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶች ላይ ሰባት እጥፍ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያካሔደው ጥናት አረጋገጠ። ጭማሪው ምንም አይነት እሴት ሳይጨመር በፍትኀዊ አሰራር ጉድለት ምክንያት ብቻ በተለይ በከተሞች የተፈጠረ በመሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ እንዳደረገው ሚኒስቴሩ ገልጿል። በቂ ምርት እንዲያቀርቡ ትስስር የተፈጠረላቸው የንግድ ተቋማትና የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፍትኀዊ አሠራርን ተከትለው አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ያመላከተው ጥናቱ፣ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ የተከሰተው በንግድ ሥርዓቱ ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ተቋማት በመበራከታቸው ምክንያት እንደሆነም አመላክቷል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑ ተጠቆመ!

የዜጎችን በተለይም የአገር የወደፊት አለኝታ የሆኑ ወጣቶችን ህይወት በመቅጠፍ የሚታወቀው ኤች.አይ.ቪ./ኤድስ እንደገና በማገርሸት ሥርጭቱ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ። ሰሞኑን በአገራችን ለ32ኛ፣ በዓለም አቀፍ ደግሞ ለ40ኛ ጊዜ በደብረ ብርሃን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የመምህራን ቀን ላይ የቫይረሱን ሥርጭት፣ ያገጠሙ ችግሮች፣ የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች አስመልክቶ በቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ እንደተገለፀው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በአገራችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎችን ህይወት የቀማበት ወቅት እንደነበር አመላክቶ ነገር ግን በተቀናጀና በተጠናከረ ርብርብ ልንቆጣጠረው ችለን እንደነበር አስታውሷል። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ዳግም በማገርሸት ከሚገባው በላይ መስፋፋቱንና ዜጎችን በተለይም ለጋ ወጣቶችን እያጠቃ እንደሚገኝ ጥናቱ አመላክቷል። የጥናቱ አቅራቢ ወይዘሮ ዓለምፀሐይ እንየው እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት የቫይረሱ ሥርዓት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየደረሰ ይገኛል ተብሏል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመሬት መደርመስ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ትናንት ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መደርመስ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡ በአደጋው 5 መኖሪያ ቤቶች አሁንም በአፈር ተሸፍነው የሚገኙ ሲሆን የሰዎችን ህይወት ለማዳን በኤእስካቫተር በመታገዝ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኮንታ ልዩ ወረዳ የህዝብ ግንኙት ሀላፊ አቶ ፋሲካ ሙሉጌታ በተለይ ለኢቢሲ አስታውቀዋል፡፡

ከአፈር በታች በሆኑት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 20 የሚሆኑ ሰዎች እንደሚኖሩ ግምት በመወሰዱ የሟቾች ቁጥር ሊጨር እንደሚችልም ነው አቶ ፋሲካ የገለፁት፡፡ የአካባቢው ተራራማ እና ተዳፋታማ የሆነ የመሬት አቀማመጥ አደጋው ለመድረሱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችልም ሀላፊው ገልፀዋል፡፡

ከመስከረም 24 ጀምሮ በተከታታይ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከ130 በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በሰብል እና በቤት እንስሳት ላይም ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ በቅርቡ ለስምንት ሰአታት ሳያቋርጥ በጣለ ከባድ ዝናብና የውሀ ሙላት ምክንያትም የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ምርጫው የሚካሄድ ከሆነ ሰላም እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን መሥራት ይገባቸዋል፤›› ሜጀር ጄኔራል ዓለም እሸት

ሪፖርተር👇
https://telegra.ph/ETH-10-14

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

የህዳሴው ግድብ የማመንጨት አቅሙ በ1ሺህ300 ሜጋዋ ዋት ቀነሰ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰት ነው ተባለ። የግብጽና የተለያዩ የአገር ወስጥ መገናኛ ብዙሃን ስለ ህዳሴው ግድብ ያወጡት መረጃ ከእውነት የራቀ እንሆነ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።

የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳሉት የግድቡ የማመንጨት አቅም እንዲቀንስ ተደርጓል የሚባለው መረጃ ትክክል አይደለም ብለዋል። የግድቡ የማመንጨት አቅም የሚወሰነው ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን እና ውሀ ከተርባይን ማእከል በሚኖረው ከፍታ ነው ብለዋል አቶ ሞገስ፡፡

የግድቡ ውሀ ከፍታ በጨመረ ቁጥር የተርባኖች የማመንጨት አቅም ከፍ ያደርገዋል እንጂ ተርባይኖች ብዛት የማመንጨት አቅም እንደማይጨምረው ነው ዳይሬክተሩ የነገሩን። አሁን ባለው ሁኔታ የግድቡን የውሀ መጠን የሚቀንስ ስራ ወይም የግድቡን ከፍታ የሚቀንስ ስራ እየተሰራ አይደለም እየተደረገ ያለው የተርባኖች ቁጥር የመቀነስ ስራ ነው ብለዋል፡፡

የተርባይኖች ቁጥር እንዲቀንስ ቢደረግም በማመንጨት አቅሙ ላይ ምንም ተጽእኖ አይኖረውም ምክንያቱም የግድቦች የማመንጨት አቅም የሚወሰነው በተርባይኖች ብዛት ሳይሆን ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡ ከግብጾች አንጻር አሁን የተነሳው ጥያቄ ግድቡ የሚይዘው የውሀ መጠን የግድቡ ከፍታ እንደማይቀንስ ካሁን በፊት የግብጽ ባለሙያዎች እርግጠኛ ነበሩ ስለሆነም ያንን ተከትሎ የተነሳ እንደሆነም ነው አቶ ሞገስ የተናገሩት፡፡ በመሆኑም የህዳሴው ገድብ 6400 ሜጋዋ ዋት እንዲያመነጭ ከዚህ በፊት በታቀደው መሰረት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#attention የአፋር TIKVAH-ETH ቤተሰቦቻችን፦ በትናንትናው እለት የጁቡቲ ሠርጎ ገብ ታጣቂዎች በአፋር ክልል የአፋምቦ ወረዳ ነዋሪዎች በተኙበት ጨለማን ተገን በማድረግ ጥቃት አድርሰዋል። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ዛሬ ጥዋት የአፋር አርብቶ አደሮች መልሶ በማጥቃት በከፈቱት ተኩስ ከታጣቂዎቹ በርካታ የፈረንሳይ ጦር…
"የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት ነው"- የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ወደ አፋር ክልል በመግባት ጉዳት አደረሰ በሚል የሚሰራጨው ወሬ ሐሰት ነው” ሲል የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዥር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተለያዩ የማሕበራዊ ሚዲዎችና አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን “በአፋር ድንበር በኩል የጅቡቲ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጉዳት አደረሰ” በሚል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑም ተገልጿል።

ጅቡቲም ኢትዮጵያን የመውረር ሐሳብ እንደማታራምድና የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጥብቅ መሆኑንም ተናግረዋል። በሁለቱ አገሮች መካከል ለግጭት የሚዳርግ ምንም አይነት ተጨባጭ ምክንያት አለመኖሩን የገለጹት ኮሎኔል ተስፋዬ እየተሰራጨ ያለው መረጃም ትክክል አለመሆኑን አብራርተዋል።

ይሁን እንጂ በአካባቢው አልፎ አልፎ በግጦሽ፣ ውሃና በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰቱ ግጭቶች መኖራቸውን አስታውሰው፤ በክልሉ በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የመከላከያ ሰራዊት በስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦት የነበረውን የቪዛ አገልግሎት መጀመሩን ገለፀ። በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መስከረም 25 ባወጣው ማስታወቂያ የቪዛ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ተቋርጦ የነበረውን የተጓዦች የቪዛ አገልግሎት ረቡዕ መስከረም 28 ቀን መጀመሩን አስታውቋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የቪዛ አገልግሎት ለመስጠት የሚለጠፉ ስቲከሮች በኤምባሲው በማለቃቸው ለሁለት ተከታተይ ቀናት ቪዛ አገልግሎት ለመስጠት ችግር አጋጥሞ እንደነበር የገለፁ ሲሆን፣ የአገልገሎቱ መቋረጥ በተወሰኑ ተገልጋዮች ላይ እንግልት እና ቅሬታ ፈጥሮ ነበር ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ ኢምግሬሽን እና ዜግነት ዋና መምሪያ ስቲከሮችን በመውሰድ ረቡዕ መስከረም 28 ቀን አገልግሎቱ እንዲጀመር ተደርጓል። ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን በርካታ ሰዎች እንደሚጓጓዙ የገለጹት ነቢያት፣ የስቲከሮች ማለቅ ከዛ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"የኢትዮጵያ መንግስት ምን እንደሚጠብቅ አልገባንም!" አቶ ጋአስ አህመድ በትላንትናው ዕለት ከጅቡቲ የመጡ ወታደሮች "ኦብኖ" በሚባል አካባቢ ጥቃት ፈፅመው የ16 ሰዎችን ህይወት ማጥፋታቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH በላኩት የድምፅ መልዕክት ገልፀዋል። አቶ ጋአስ እንደሚሉት ወታደሮቹ የመጡት ከጅቡቲ ነው፤ ከባድ መሳሪያም የታጠቁ ነበሩ፤ ስልጠናም…
🤔ከቀናት በኃላ በአፋር ስለተገደሉ ዜጎች የመንግስት ሚዲያዎች መዘገብ ጀምረዋል!

#EBC

በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ሜጉ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች በፈፀሙት ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ መሆኑን የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ኡመድ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

በጥቃቱ እስካሁን 16 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከእነዚህም መካከል 3ቱ ህፃናት እና 4ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል። ጥቃቱ በተሸከርካሪ የታገዘ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘት እንደተቻለም ነው ም/ል ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን አስታውቋል፡፡

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዦር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia