TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአፋር ክልል በ9ሺህ 371 ሄክታር መሬት ላይ የነበረው ሰብልና እጽዋት ከበረሀ አንበጣ መንጋ ጥቃት ነጻ መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። በክልሉ ያለው ዝናባማ የአየር ጠባይና የግንዛቤ ማነስ የአንበጣ መንጋውን የመቆጣጣር ሂደት አዳጋች ያደረገው መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በትላንትናው ዕለት አዲሱን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ "መለስ ዜናዊ ካምፓስ" ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። አዲሱ ካምፓስ ተማሪዎችን ለመቀበል በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን በመግለፅ የተማሪዎች መግቢያ/የምዝገባ ጊዜ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnitedStates

Congratulations on the Awarding of the Nobel Peace Prize to Prime Minister Abiy

MICHAEL R. POMPEO, SECRETARY OF STATE

https://www.state.gov/congratulations-on-the-awarding-of-the-nobel-peace-prize-to-prime-minister-abiy/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Al Jazeera News

Arrests Come One Day After Prime Minister Awarded Nobel Peace Prize! #BilleneSeyoum said she is not aware of the arrest.

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ማግኘትን በማስመልከት በዛሬው እለት በተለያዩ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። ሰልፎቹ አዳማ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ መቱ፣ ዱከም እና ገላንን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ተካሂደዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደጀን ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ተከፍቷል። ደጀን ከተማ ላይ ቆመው የነበሩ መንገደኞች በተለይም አዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ እንደሆነ ግልፀውልናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA

የቅንጅት ለዲሞክራሲና ለነፃነት የተባለ ፓርቲ ትላንት በድሬዳዋ ከተማ የምስረታ ጉባኤውን አካሂዷል። ዋና መቀመጫውን ጅግጅጋ ያደረገው ፓርቲው በሱማሌ ክልል ብቻ ሳይሆን  በመላው ሀገሪቱ ነፃነትና እኩልነት እንዲሰፍን ይስራል ሲሉ የመስራች ኮሚቴ አባላት ተናግረዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት በማሸነፋቻው በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ዱከም፣ ገላን፣ ሻሸመኔ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ሱሉልታ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጅማ፣ መቱ፣ በደሌ፣ ባቱ፣አዳማ፣ ጉጂ ዞን፣ ቦረና ዞን፣ እኔ ሌሎች በርካታ ከተሞች የደስታ ሰልፎች እየተደረጉ ናቸው።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Arbaminch

ከጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤትና ከውጭ ሃገር የመጡ የቴክኒክ አባላት በአርባምንጭ ከተማ ለሚገነባው ስመጥርና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴልና ሪዞርት ግንባታ ጅማሮ የሚሆን የቦታ መረጣና ቅኝት ስራዎችን አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ ለህዝብ እንደራሴ አባላት በአፍሪካ ሲሼልስ ከሚገኘው ግዙፉ ሆቴልና ሪዞርት በመቀጠል በአርባምንጭ ከተማ ስለሚገነባው ሆቴልና ሪዞርት ገለፃ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-13

ምንጭ፦ የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢትዮጵያ መንግስት ምን እንደሚጠብቅ አልገባንም!" አቶ ጋአስ አህመድ

በትላንትናው ዕለት ከጅቡቲ የመጡ ወታደሮች "ኦብኖ" በሚባል አካባቢ ጥቃት ፈፅመው የ16 ሰዎችን ህይወት ማጥፋታቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH በላኩት የድምፅ መልዕክት ገልፀዋል። አቶ ጋአስ እንደሚሉት ወታደሮቹ የመጡት ከጅቡቲ ነው፤ ከባድ መሳሪያም የታጠቁ ነበሩ፤ ስልጠናም የወሰዱ ናቸው። እነዚህ ወታደሮች የሲቪል ልብስ በመልበስ ነው ጥቃት የፈፀሙት ያሉት አቶ ጋአስ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ምን እንደሚጠብቅ አልገባንም ሲሉ ተናግረዋል። መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ካልቻለ የዜጎችን ህይወት መታደግ አይቻልም፤ የአፋር ህዝብ ከሚደርስበት ጥቃት የራሱን ቤተሰብ እና ንብረት በራሱ አቅም እየተከላከለ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል። በጅቡቲ መንግስት የሚታገዙ ወታደሮችና ታጣቂዎች በጣም ብዙ ህይወት እያጠፉና ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ፤ ይህ ጉዳይ እጅግ በጣም አሳዝኝ ነው መንግስት አስፈላጊውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ሲሉ አቶ ጋአስ አህመድ አሳስበዋል።

----------

በጉዳዩ ላይ ምላሽ መስጠት የምትፈልጉና ተጨማሪ መረጃ ያላችሁ የመንግስት አካላት በ @tsegabwolde ወይም በ @tsegabtikvah ላይ የድምፅ መልዕክት ማስቀመጥ ትችላላችሁ!

TIKVAH ETH FAMILY

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ላለፉት 2 ቀናት ዝግ ሆኖ የቆየው አዲስ አበባ ከተማን ከባህርዳር ከተማ የሚያገናኘው መንገድ ዛሬ ተከፍቷል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እንኳን ደስ አላችሁ! ለማለት ይወዳል። የህክምና ኮሌጁ የ3ኛው የጣና ሽልማትን በጤና መረጃ ዘርፍ አሸንፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

የኢሬቻ በዓል ቡራዩ በሚገኘው መልካ አቴቴ እየተከበረ ይገኛል፡፡ በመልካ አቴቴ የኢሬቻ በዓል ላይ የጋሞ አባቶችና ሌሎች የጋሞ ብሔረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አልማ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ በለሳ ወረዳ በአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) ድጋፍ የተገነቡ ትምህርት ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-13-2

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ ከተማ ፍልውሃ አካባቢ 2 የፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የፌደራል ፖሊስ ኮምንኬሽን ለሸገር ተናግሯል። 4 አባላት መቁሰላቸውንም ተሰምቷል። ምክንያቱም ምን እንደሆነ የተጠየቃት የስራ ሀላፊ የአንድ አባል ቀልድ መሳይ ብሽሽቅ እንደሆነ ተናግረዋል። በተጀመረውም ብሽሽቅ አንደኛው አባል 2 ጓደኞቹን በእጁ በያዘው መሳሪያ ተኩሶ መግደሉን የፌደራል ፖሊስ ለሸገር ራድዮ ተናግረዋል። ህይወት ያጠፋው አባልም እንደቆሰለ እና ጉዳዩ በምርመራ እንደሆነ ታውቋል። ሸገር የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ፍልውሀ አካባቢ ምን ያደርጉ እንደነበር ጠይቋል። የኮሚንኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ጄላን አባሎቹ በአካባቢው የሚኖሩበት ቦታ አለ በጥበቃም የተሰየሙ ነበሩ የሚል መልስ ሰጥተዋል።

Via ሸገር ኤፍ ኤም ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች ተደርገዋል፦ ዱከም፣ ገላን፣ ሻሸመኔ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ሱሉልታ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጅማ፣ መቱ፣ በደሌ፣ ባቱ፣አዳማ፣ ጅማ ዞን /ጌራ/፣ ድሬዳዋ፣ ቢሾፍታ፣ ሰበታ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሀረር፣ጭሮ፣አሶሳ/ቤኒሻንጉል ጉምዝ/ ደንገሃቡር/ሱማሌ ክልል/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቢሾፍቱ በልምምድ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ በመነሳት በልምምድ ላይ እያለ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ኡኬ ደንካካ በተሰኘ ቦታ መከስከሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ያሚ ለዶቸ ቨለ አረጋግጠዋል። በአደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉንም አቶ…
#RIP

ሻለቃ ሰበሪ ቶፊቅ🕯ሻምበል ኃየሎም ተስፋይ!

#BISHOFTU

በአደጋው በደረደበት ወቅት ኢንስትራክተር አብራሪ ሻለቃ ሰብሪ ቶፊቅ ከተዋጊ ጄቱ ተስፈንጥሮ የወጣ ቢሆንም፣ ፓራሹቱ ሊዘረጋለት ባለመቻሉ ሕይወቱ እንዳለፈ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ሌላው በአደጋው ሕይወቱን ያጣው ሠልጣኝ አብራሪ ሻምበል ኃየሎም ተስፋይ ነው፡፡

ሻለቃ ሰብሪ በ1999 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ አየር ኃይል የበረራ ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማዕረግ እንደተመረቀና አየር ኃይሉን ከአሥር ዓመት በላይ እንዳገለገለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ድሬዳዋ ተወልዶ ያደገው ሻለቃ ሰብሪ በጂማ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ተማሪ የነበረ ቢሆንም፣ ለበረራ በነበረው ፍቅር የምሕንድስና ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አየር ኃይል የበረራ ትምህርት ቤት እንደገባ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በትምህርቱም በከፍተኛ ውጤት ያስመዘግብ እንደነበር ገልጸው፣ ሲመረቅ ከክፍሉ በአንደኛ ደረጃ እንዳጠናቀቀ ተናግረዋል፡፡ ሻለቃ ሰብሪ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበር፡፡

ሱኮይ 27 ተዋጊ አውሮፕላኖች የተገዙት በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ነበር!

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

ዛሬ ማለዳ የካቢኔ አባላት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል። ለአመራሩ እንዲሁም ለተገኘው ስኬት ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ የወርቅ ሀብል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያበረከቱ ሲሆን "እውነት ፍቅር ያሸንፋል" የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበታል።

#PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያዊቷ ለ16 ዓመታት ተይዞ የነበረውን የሴቶች ማራቶን ሪከርድ ሰበረች!

ዛሬ በተካሄደው ቺካጎ ማራቶን ኬንያዊቷ ብርጊድ ኮስጊ በ 2003 ፓውላ ራድ ክሊፍ ያስመዘገበችውን የሴቶች የማራቶን ሪከርድ 2:14:04 በመግባት ከ 16 ዓመታት በውኋላ ሪከርዱን መስበር ችላለች።

@tikvahethsport @GoitomH @kidusyoftahe