TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ምርጫ ቦርድ የቀጣዩ ምርጫ ደህንነትን ለማረጋገጥ በራሱ የሚመራ እና 27 አባላት የሚኖሩበት የጋራ የምርጫ የማዘዣ ማዕከል (Joint Election Operation Center - JEOC) በፌደራል ደረጃ ለማቋቋም እቅድ እንዳለው አስታውቋል። በእቅዱ ላይ ምክክር ይደረግበታል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም በምርጫ ጣቢያነት ያገለገሉ ቦታዎችን ለመለየት የጂ.ፒ.ኤስ ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ ይገኛል። በመስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች የተዘጋጀው የምርጫ ጣቢያዎች ካርታ በቅርቡ ለቦርዱ ውሳኔ ይቀርባል ተብሏል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

ምርጫ ቦርድ ባለድርሻ አካላትን በጋበዘበት ኮንፍረንስ ላይ በመጋዘን ውስጥ፣ በካርቶን ታሽገው የተከማቹ፣ በርከት ያሉ የመራጮች የምዝገባ ሰነዶች እና ቁሳቁሶችን ለተሳታፊዎች በቪዲዮ አሳይቷል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2020

የተረጋገጠ፦ ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በአውሮፓውያን የጊዜ አቆጣጠር : Revised key dates for General Elections 2020

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"ነሐሴ መጀመሪያ ላይ ከማድረግ ትንሽ ገፋ ያደረግነው የክረምት ጫናውን ይቀንሳል ብለን ነው"- የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የድምጽ መስጫ ቀኑ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ከነበረው ስለመሻሻሉ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

ለ 50,800 የምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ የመራጮች ምዝገባ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች እንደዚሁም ለስልጠና ብቻ የሚውሉ 4,200 ሰነዶች እና ቁሳቁሶች ተጠናቅቀው ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን በዛሬው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮንፍረንስ ተገልጿል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#Election2012 ምርጫ ቦርድ ባለድርሻ አካላትን በጋበዘበት ኮንፍረንስ ላይ በመጋዘን ውስጥ፣ በካርቶን ታሽገው የተከማቹ፣ በርከት ያሉ የመራጮች የምዝገባ ሰነዶች እና ቁሳቁሶችን ለተሳታፊዎች በቪዲዮ አሳይቷል። #EthiopiaElection @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የምርጫ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች የተከማቹት ከፍተኛ ጥበቃ ባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕቃ ማከማቻ መጋዘን መሆኑን በዛሬው የምርጫ ቦርድ ኮንፍረንስ ላይ ተመልክቷል። ቦርዱ አየር መንገዱን ለዕይታ ባበቃው ቪዲዮ ላይ አመስግኗል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የምርጫ ምዝገባን በተመለከተ ፦ "ሎጀስቲክ ላይ ብዙ ወጪ ሳያስወጣ እንዴት መፈጸም እንደምንችል እያየን ነው። እንዴት እንደምንፈጽመው ገና አልወሰንንም" ብልዋል የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው ኮንፈረንስ።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

"ኤርትራ ለእኛ ድጋፍ አላደረገችም" - ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

በምርጫ ቦርድ ኮንፍረንስ የተሳተፉ የህወሓት ተወካይ፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት በቅርቡ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ የተናገሩትን አንስተው ጥያቄ አቅርበዋል። "ኤርትራ ለእኛ ድጋፍ አላደረገችም" ሲሉ ብርቱካን ሚደቅሳ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምርጫ ዋና የሉዓላዊነት መገለጫ መሆኑን የተናገሩት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ድጋፍ ከሚሰጧቸው አካላት እስካሁን ምንም ዓይነት ተጽእኖ እንዳልደረሰባቸው ለኮንፍረንስ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ለምርጫ 2012 "ሰራዊታችንን በአግባቡ እናሰለጥናለን። የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥሙ እንዴት መከላከል እንደሚቻል በቂ ዝግጅቶች አድርገናል... በከተማም ሆነ በገጠር ሽፍታ ካለ አንቀበልም። ህግ እናስከብራለን" ብለዋል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot