TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sport

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን ሆነ።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ለተከታታይ ሁለተኛ አመት ለአስራ ስድስተኛ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን መሆናቸውን ዛሬ አረጋግጠዋል።

አንድ ነጥብ ብቻ ያስፈልጋቸው የነበሩት ፈረሰኞቹ በሀያ ዘጠነኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸናፊ ያደረጉ ሁለት ግቦች ቸርነት ጉግሳ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቶጓዊው የፊት መስመር አጥቂ እስማኤል ኦሮ አጎሮ በሀያ አምስት ጎሎች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢነት እየመራ ይገኛል።

እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከዚህ በተጨማሪም በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ ከፍተኛ የምንጊዜም ሁለተኛ ግብ አስቆጣሪነትን ከጌታነህ ከበደ ጋር መጋራት ችሏል።

የሊጉ #ሪከርድ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እነማን ናቸው ?

1. አቡበከር ናስር :- 2⃣9⃣ ጎሎች

2. ጌታነህ ከበደ :- 2⃣5⃣ ጎሎች

2. እስማኤል ኦሮ አጎሮ :- 2⃣5⃣ ጎሎች

4. ዮርዳኖስ አባይ :- 2⃣4⃣ ጎሎች

ተጨማሪ https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport