TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትን #በህግ_ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ዶ/ር እሸቱ ከበደ

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆችም መረጃዎችን ከተቋሙ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉም ጠይቀዋል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia