TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የሟቾች ቁጥር 100 ደርሷል፤ ኢንተርኔት በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞችም ተዘግቷል! በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድና አከባቢዋ 6 ቀናትን ባስቆጠረው ታቀውሞ የሞቱት ሰዎች 100 ደርሰዋል። በኢራቅ የተለያዩ ክፍሎች የሀገሪቱን መንግስት በመቃውም ተቃውሞ ከተቀሳቀሰ ስድስት ቀናትን አስቆጥሯል። በዚህ ታቃውሞ በርከት ብለው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ወጣቶች ሲሆኑ  ሙስናን ፣ ስራ አጥነትን እና ዝቅተኛ መንግስት አገልግሎትን…
#BAGHDAD

ላለፉት 6 ቀናት በኢራቅ በነበረው ተቃውሞ #ከ100 በላይ ሰዎች ሞተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ ታስረዋል። ባግዳድ ላይ ላለፉት ቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ተመልሷል። የማህበራዊ ሚዲያዎችን ግን ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው፤ ያም ቢሆን በርካታ ያልታዩ ቪድዮዎች እየወጡ ናቸው። የኢራቅ ጋዜጠኞች ደግሞ ስለጉዳዩ እንዳይዘግቡ እና የዓለም ህዝብ እንዳይሰማው ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

•አክሱም ዩኒቨርሲቲ
•ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
•ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ(የመግቢያ ጌዜ ተራዝሟል)
•ባህር ዳር የምዝገባ ቦታ አሳውቋል
•ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
•ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
•አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የአዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ይፋ ተደርጓል!

ሌሎች በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን በTIKVAH-MAGAZINE ማግኘት ትችላላችሁ። ትክክለኛው ገፃችን ከ77,000 በላይ ቤተሰብ ያለበት ብቻ ነው!

@tikvahethmagazine የቲክቫህ ኢትዮጵያ ገፅ ነው!

Join TIKVAH-MAGAZINE👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
Addis - global fashion provides only orginal products. We offer quality service and commited to deliver comfort to our clients.
Free delivery is available.

Call us : 0923 29 52 32
Subscribe us on our telegram chanel :
Join👇
https://t.iss.one/addisglobalfashion upgrade your class!

☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ! #ETHIOPIA☀️
🔖እናስተዋዉቅዎ!

Homeቤት interior design ለመኖርያ ቤት ለአፓርትመንት ለሆቴል ለ ኦፊስ እንዲሁም ለተለያዩ ሱቆች የ ኢንቴሪየር ዲዛይን አገልግሎት እንሰጣለን ይደውሉልን በስራችን ይረካሉ!
ለበለጠ መረጃ📱
0912637328
0931180968
Facebook page :https://www.facebook.com/Home-ቤት-Interior-Design-Works-187333958428843/
አድራሻ : መገናኛ ቤቴሌሄም ፕላዛ 5ኛ ፎቅ ቤሮ ቁጥር 526

☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
#ETHIOPIA☀️
በቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ዙሪያ አዲስ አበባ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው!

በአማራ ክልል መንግሥት አስተባባሪነት የተዘጋጄና በቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጉዳይ የሚመክር ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው በውይይ መክፈቻ ላይ ባሰሙት ንግግር ‹‹በቅማንት ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን አለመረጋጋት ከኮሚቴው ጋር በመሆን ሌላ ዓይነት መልክ እንዲይዝ በተቀናጀ መልኩ እየሠሩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት እየሠራ ነው›› ብለዋል፡፡

ጉዳዩን የመገናኛ ብዙኃን ባልተገባ መልኩ የአንድ ወገንን ሐሳብ ብቻ በመያዝ ማቀጣጠላቸው ተገቢ እንዳልሆነና ሊታረሙ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ጥያቄውን ለመመለስ የክልሉ መንግሥት ኃላፊነቱን ተወጥቷል፤ ቀሪ ጥያቁዎችም ካሉ በሠላማዊ መንግድ ለማስናገድ እየሠራ ነው›› ብለዋል አቶ ጌትነት በንግግራቸው፡፡

ለውይይቱ መነሻ ሁለት ጽሑፎች እየቀረቡ ነው፡፡ ‹‹የቅማንት ጥያቄ ከየት ወደዬት፡- እስከ ፖለቲካ ፓርቲ ምሥረታ›› በሚል ርዕስ የሦስተኛ ዲጊሪ ተማሪ በሆኑት አቶ ቹቹ አለባቸው እና ‹‹የቅማንት ጥያቄና የክልሉ መንግሥት ምላሽ›› የሚል ርዕስ የያዘ ጭብጥ ደግሞ በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሕግ አማካሪ አቶ መርሐጽድቅ መኮንን አማካኝነት እንደሚቀርቡም ታውቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከተንቀሳቃሽ ስልኮች ገበያ ውስጥ 98 በመቶው በኮንትሮባንድ መያዙ ተረጋገጠ!

ከሦስት ዓመት በፊት 65 በመቶ ደርሶ የነበረው ሕጋዊው የተንቀሳቃሽ ስልክ ምርቶች የገበያ ድርሻ በያዝነው ዓመት ወደ ሁለት በመቶ በመውረድ 98 በመቶ የሚሆነውን የገበያውን ድርሻ ለኮንትሮባንድ ንግድ ሰንሰለት ማስረካቡ በጥናት ተረጋገጠ።

በሃገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጪ ሃገር በሕጋዊው የንግድ ስርአት የሚመጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ግብር በማይከፍሉ እና በሕገወጥ መልኩ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ስልኮች ገበያውን የተነጠቁ ሲሆን ይህም አንዳንድ አምራቾች ኢንዱስትሪአቸውን ዘግተው እንዲወጡ ምክንያት እንደሆነም የኢትዮጵያ ስልክ ገጣጣሚዎች ማህበር ፕሬዘደንት አስማማው አማረ (ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Happening Now

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አዘጋጅነት ከመስከረም 27- 28/2012 የሚቆይ "አገራዊ ምርጫና የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና" በሚል ርዕስ አለማቀፍ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የኤ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሣህለወርቅ ዘውዴ ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ፣ የአሜሪካ አምባሳደር ሚካኤል ራይን ፣የፓለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ የሲቪል ማህበራትና የሚዲያ ባለሞያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ ጉዳይ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል፡፡

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ አደርጓል፡፡ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ድረስም ክስ እንዲመሠርት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

የ20 ዩኒቨርሲቲዎች የአዲስ ተማሪዎችን የመግቢያ ቀን የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ etv ይፋ አድርጓል። መረጃውን እና ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በ @tikvahethmagazine ማግኘት ትችላላችሁ!

Join TIKVAH-MAGAZINE👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#BAHIRDAR

"የባህር ዳር ነዋሪ ነኝ ፍርድ ቤት አካባቢ ዛሬ የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ቀጠሮ ነበር። ትንሽ ቆይቶ የተቃውሞ ድምፅ ሰማን፤ እስረኞች ይፈቱ የሚል። እናም ልንወጣ ስንል አስለቃሽ ጭስ ተተኮሰ እናም መውጣት አልቻልንም። እስከ ቤታችን ድረስ አይናችን እየተቃጠለ፤ አፋችንም ታፍኖ ነበር የደረስነው።" DAGI/TIKVAH-ETH/

POHTO: ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopua
#AddisAbeba

‹ሀገራዊ ምርጫና የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና› በሚል ርዕስ ዙሪያ ዓለማቀፍ ውይይት አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፤ ዓለም አቀፍ የዉይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳኅለወርቅ ዘዉዴ ‹‹በምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ቢወዳደሩም፣ ዋነኛ የምርጫ ተዋናዮች ሕዝቡ ነዉ። በተያዘዉ ዓመት የሚካሄደዉ ምርጫ የሀገራችንን መፃኢ ዕድል የሚወስን መሆኑን አውቀን፣ በንቃት ልንሳተፍ ይገባል›› ብለዋል።

ስኬታማ ምርጫን ለማከናወን ደግሞ መልካም ተሞክሮ ካላቸዉ ሀገራት ልምድ መቅሰምና ችግሮች ቢኖሩም እንኳ በውይይት መፍታት እንደሚገባ ተናረዋል። ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማከናወን በቅድሚያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛና ከገዥዉ ፖርቲ ውግንና ነፃ መሆን ስለሚገባዉ፣ ይህንን ለማድረግ መንግሥት ልዩ ልዩ ጥረቶችን ማድረጉንም ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ አስታውቀዋል

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Mekelle

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር ጋር ተወያይተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በትናትናው እለት ጉብኝት አድርገዋል።

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልም በትናነትናው እለት አምባሳደር ማይክል ራይነርን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በውይይታቸውም በንግድ እና ኢንቨስትመንት የትብብር መስኮች ላይ የተወያዩ ሲሆን፥ በፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ኢኮኖሚ ዙሪያም ምክክር ማድረጋቸው ነው የተነገረው።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በማኅበራት ተደራጅተው ከቀረጥ ነፃ የገቡ በሥራ ላይ የሚገኙ ባለ ሜትር ክፍያ ታክሲዎች የክፍያ ተመን ወጥነት ያለው ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እየተጠናቀቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደገለጹት ቀደም ሲል የተቀመጠው ክፍያ ተመን ወጥነት ባለው መልኩ እየተተገበረ ባለመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥናት መደረጉን ተናግረዋል።

አያይዘውም ተመኑ ዝቅተኛ ነው በሚል የተወሰኑ ማኅበራት በድርድር ወደ መስራት መግባታቸውን እና ይህንን ለማስተካከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል። ምክትል ሥራ አስኪያጁ ጥናቱ ሲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት እንደሚደረግ እና ጉዳዩን አስመልክቶ በቀጣይ ጊዜያት ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ብለዋል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvagethiopia
በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ከተማ የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪና የሞት አደጋ አደረሰ!

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ከተማ የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪና ከጥንቃቄ ጉድለት ቅዳሜ ዕለት በአንድ ሰው ላይ የሞት አደጋ ማድረሱን የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ማስቆም ዳይሬክቶሬት የመረጃ ትንተና ባለሙያ መክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ ገልጸዋል፡፡

አደጋው የደረሰው ሁለት የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪናዎች በተከታታይ ቆመው ከነበሩበት የአንደኛው መኪና ረዳት መኪናውን ሲያንቀሳቅስ በፈጠረው ስህተት የሌላኛውን ኤፍ ኤስ አር መኪና መስተዋት በመወልወል ላይ በነበረው ረዳት ላይ አሰቃቂ አደጋ በማድረሱ የረዳቱ ህይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ መክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ አስረድተዋ፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን የሞት አደጋ ጨምሮ በደቡብ ክልል ከባለፈው መሰከረም 22/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአራቱ ቀናት ብቻ 13 ያህል የትራፊክ አደጋ መድረሳቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከ13 አደጋዎች 5ቱ የሞት 6ቱ ከባድ የአካል ጉዳትና ሁለት ቀላል የአካል ጉዳት ያስከተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡ የአብዛኘው የአደጋ መንስኤዎች ለእግረኛ ቅድሚያ ያለመስጠት፣ የአሽካርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለትና ፍጥነት ናቸው፡፡ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ በማድረግ ፍጥነታቸውን ገድበው ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ምክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ከችጉንጉኒያ ወረርሽ ስጋት ለመታደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በከተማው ለወራት በዘለቀውና ከ35 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ያጠቃው ወረርሽኙ ከእረፍት እየተመለሱ ባሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ላይም ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

የቺኩንጉኒያን ወረርሽኝን ለመከላከል በተማሪዎች አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች መድሃኒት መረጨቱን የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በድሬ ዳዋ ከአንድ ቤት ከ2-4 ሰዎች በወረርሽኙ እንደተያዘ የተገለጸ ሲሆን መንግስት ጉዳዩን በአጽኖት እንዲመለከተው የህክምና ባለሞያዎች እየጠየቁ ነው፡፡

ከድሬ ዳዋ የጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የድሬ የበጎ ፍቃድ የህክምና ባለሞያዎች ማህበር ወረርሽኙን ለመግታት የህክምና ዘመቻ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Via Ahadu TV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በህገ-ወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ!

በህገ-ወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በአገልግሎትና በመሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት በአቅርቦት ችግር ሳይሆን የህገወጥ ደላሎች ጣላቃ ግብነት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ የዋጋ ንረቱ በተለይም በደሃው ማህበረሰብ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና እያሰደረ ነው ብለዋል፡፡

ጥቂቶች አላስፈላጊ ንዋይ በመሰብሰብ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲፈጠር አድርጓልም ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በህገ- ወጥ ደላሎች አማካኝነት አየር በአየር በመኪና ላይ ህገወጥ ግብይት ሲያካሂዱ የተገኙ 59 መኪኖች አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 52 መኪኖች ጤፍና ሌሎች እህሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጠቁማዋል፡፡

የቁጥጥርና እርምጃ የመውሰድ ስራ በሁሉም የሀገሪቷ ክልሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡ ደላሎችን ከግብይት ሰንሰለት ውጪ በማድረግና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር አምራቾችና ተጠቃሚዎች በቀጥታ የሚገናኙበትን አግባብ ለመፍጠር ሚኒስቴር መ/ቤቱ የረጅም ጊዜ እቅድ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡- የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግብፅ በህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ላይ ያነሳችው አቋም የኢትዮጵያን ቀይ መስመር የሚያልፍ ነው!

ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ዙሪያ ያነሳችው አቋም የኢትዮጵያን ቀይ መስመር የሚያልፍ በመሆኑ ከመግባባት ላይ መድረስ እየተቻለ አይደለም አለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴር።

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበርያ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት በግድቡ ሁለንተናዊ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ አካላት ጋር በዛሬው እለት የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የግድቡ ግንባታ ያለበትን ደራጃ እና የታችኛው ተፋሰስ አገራት የሶስትዮሽ ውይይት ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-08

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE በጣሊያን የባህር ጠረፍ ሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው ከነበሩ መካከል የ13 ሴቶችን አካል የጣሊያን የባህር ጠባቂዎች ማውጣታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ በድረ ገጹ አስነብቧል። ለስደተኞቹ ሞት በከፍተኛ አየር ጠባይ ለውጥ የተሳፈሩባት ጀልባ በደቡባዊ የሲሲሊ ደሴት ላምፔዱሳ ጠረፍ  አካባቢ መስመጧን ተከትሎ እንደሆነ የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ከተረፉት አንዷ ለሲ ጂ ቴኤን እንደተናገረችው በአደጋው  እህቷንና  ሌላ የስምንት ወር የእህቷን ልጅ እንዳጣች በሃዘን በተሰበር ልብ ተናግራለች፡፡

Via CGTN/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስቴር የተቋቋመበትን ዓላማና ግብ ለኅብረተሰቡ በቀላሉ ለማድረስ የሚያስችለውን አዲስ መለያ ዓርማና መሪ መልዕክት ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ይፋ አድርጓል።
@tsegsbwolde @tikvahethiopia