TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የ10ኛ ክፍል ውጤት #ዛሬ ይፋ ይደረጋል። የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዛሬ 10 ሰዓት ውጤቱን በተመለከተ መግለጫ ይሰጣል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ #ዛሬ በመዲናዋ ግዙፍ ሰልፍ ሊኖር ይችላል ብሎ ኤምባሲውን ዘግቷል። ኤምባሲው መረጃውን ከየት እንዳመጣው ይፋ አላደረገም። ነገር ግን ከተማይቱ የወትሮው ሰላማዊ እና መደበኛ እንቅስቃሴዋ ላይ ትገኛለች።

📌የአንድ ትልቅ ሀገር ኤምባሲ በምን ምክንያት ይህን መረጃ ይፋ እንዳደረገ እና ኤምባሲውን ሊዘጋ እንደቻለ የሁሉም ጥያቄ ነው። በመዲናይቱም ምን እየሆነ እንዳለ? ምን እንደተፈጠረ?? የሚጠይቁ ብዙዎች ናቸው። አሜሪካስ ይህን አይነት መረጃ ማን ሰጣት??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢህአፓ⬆️

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮች ከ40 አመታት በላይ የውጪ አገር ቆይታ በኋላ #ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በውጪ ያሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር ግንባታ ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይህን ጥሪ ተከትሎ ነው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ከደርግ ዘመን ጊዜ ጀምሮ ከነበራቸው የብዙ አመት የውጪ ቆይታ በኋላ ዛሬ ወደ አገር ቤት የገቡት።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ በላይነህ ንጋቱ፣ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሃመድ ጀሚል እና ኢንጂነር ሰለሞን ገብረስላሴን የያዘ ከፍተኛ አመራር አባላት ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ተቀብለዋቸዋል።

ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ንጋቱ እንዳሉት፤ ፓርቲው በአገሪቱ አሁን የተጀመረውን ለውጥ መሰረት እንዲይዝ የሚችለውን ያደርጋል።

በተፈጠረው እድል ህጋዊ ሆኖ ለመንቀሳቀስ ፓርቲው ዝግጁ መሆኑን የገለፁት ሊቀመንበሩ ከአሁኑ የለውጥ አመራር ጎን በመሆን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር #በትጋት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ሚናቸውን በአግባቡ ለመወጣትም ከቀድሞ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ከወጣቱ ጋር የጋራ ምክክር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

የህግ የበላይነት እንዲከበርና ዴሞክራሲ የበለጠ እንዲሰፋ ፓርቲያቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር #ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የፓርቲው አመራሮች ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥና ሻማ የማብራት ስርዓት ያከናውናሉ ተብሏል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከግንቦት 7 ጋር መለያየቱን አሳወቀ፡፡ድርጅቱ ከግንቦት 7 ጋር መለያየቱን አስመልክቶ #ዛሬ በባሕር ዳር መግለጫ እየሰጠ ነው፡፡

©AMMA
@Tsegabwolde @tikahethiopia
#update የቴክኒክ እና ሙያ መግቢያ⬆️

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ በ2011 ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ #ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው #ዛሬ እንዳስታወቀው በየዓመቱ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል የሥራ ገበያውን መሰረት በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መስፈርት ተመርኩዞ የመቁረጫ ነጥቡን ይፋ እንዳደረገ አመልክቷል፡፡

በዚህም መሰረት በ2010 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል 725 ሺህ 652 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመደበኛው ዘርፍ እንደሚገቡ ኤጀንሲው አመልክቷል፡፡

ከዚህም ውስጥ 230 ሺህ 828 ሴቶች ናቸው፡፡ በመምህራን ኮሌጅ እንዲሁም በፖሊስና መከላከያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡት ቁጥር በዚህ መግለጫ አለመካተቱም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• ከንግዲህ ትኩረታችን ወጣቱን የስራ ባለቤት ማድረግ ነው

• ፊታችንን ወደ ስራ ለማዞር የማብሰሪያው ዕለት ነው #ዛሬ

• የልማት እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ማድረግ የመንግስት ዋነኛው ስራ ነው

• የኢንዱስትሪ ልማት ሲስፋፋ ቦታው ለትራንስፖርት ምቹ መሆኑ ይታያል፤ አዳማን የሚያህል ምቹ ስፍራ የለም፤ የባቡር መስመር፣ ፈጣን መንገድ፣ ወደፊት በቅርብ ርቀት የሚሰራው ትልቁ የአየር ማረፊያ

• የአዳማ ወጣትና ነዋሪ ላለፉት ጊዜያት በተካሄደው ትግሉ ካለአንዳች ጥፋት ተቃውሞውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልፅ የቆየ ነው

• የባለሀብቶች ዋነኛው ጥያቄ መንገድ አለ ወይ ሳይሆን ሰላም አለ ወይ በመሆኑ ሰላማችሁን መጠበቃችሁን አትዘንጉ

• በተለመደው መንገድ በኦሮሞ ባህል ባለሀብቱን የመሳብ የማቀፍ ስራችሁን ቀጥሉ

• ከወራት ትግል በኋላ ወጣቱ አሁን ፊቱን በሙሉ ልብ ወደ ስራ ደወ ልማት ወደ እድገት ማዞር ይኖርበታል፡፡ የትግል ሱስ ያለበት የለምና፡፡

• ዶ/ር አርከበ ሰርቶ የሚያሳይ ብቃት ያለው ከፖለቲካ ሻጥር ራሱን አውጥቶ በስራ የተጠመደ ክቡር ሰው ነው

• ቀበቶአችሆን አጥብቃችሁ ለሚጠብቀን ቀጣይ ስራ ተዘጋጁ

• ዶ/ር መሰለ ኃይሌ በታላቅ ጥረት ውጤት እንድናመጣ እያገዘን ያለ በመሆኑ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል

• አዳማ የሰላም የፍቅር አብሮ የመኖር አብነት በመሆኑ ባለሀብቶች ወደ አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፊታችሁን እንድታዞሩ እመክራችኋለሁ

• ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ ተግባራት ላይ ብትሰማሩ መንግስት ከፍተኛ እገዛ ያደርግላችኋል

• የኢትዮጵያ እውነተኛ የተሃድሶ በርግጥም ከፊታችን እየመጣ ነው

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤጀንሲው ተማሪዎችንና የተማሪ ወላጆችን ይቅርታ ጠየቀ!

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ/የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት #ዛሬ ይፋ ይደረጋል ቢባልም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በገጠመው ችግር ምክንያት ለ2 ቀናት #ማራዘሙን አስታውቋል፡፡ ኤጀንሲው ውጤቱን ከ2 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ተናግረዋል፡፡ ለተፈጠረው መዘግየትም ዳይሬክተሩ ለተፈታኞች እና ለተፈታኝ ወላጆች ይቀርታ ጠይቀዋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የመን

ትናንት - ራሱን የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት (southern transitional council) ብሎ የሚጠራው የየመን ተገንጣይ ቡድን በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ድጋፍ ኤደንን ተቆጣጠረ -- #ዛሬ-በሳዑዲ አረቢያ ትዕዛዝ እና ዛቻ ጥሎ መውጣት ጀመረ።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሐሺ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ!

#የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት #ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የተጠባባቂና የምክትል ከንቲባ ሹመት አፀደቀ። ምክር ቤቱ  አቶ አብዲፈታህ ኢብራሂምን ተጠባባቂ ከንቲባ፣ አቶ ሐሺ አብዱላሂ ደግሞ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟቸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር #ዛሬ በይፋ ተመስርቷል። ማህበሩ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመረጃ ነጻነትና የመደራጀት መብቶች እንዲከበሩ የህግ፣ የፖሊሲና የማዕቀፎች እንዲሁም የአፈጻጸም ማሻሻያዎች እንዲስፋፉ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዛሬ

በአለማቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አዘጋጅነት የሚካሄደው ሁለተኛው የአክቲቪስቶች የውይይት መድረክ ዛሬ ይካሄዳል፡፡ በዚህ መድረክ የሚነሱ ሀሳቦችን ለእናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መደመር_መጽሐፍ
#በድሬዳዋ
#ዛሬ_ይመረቃል

በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈው ‘’መደመር ’’ መጽሐፍ ዛሬ ጥቅምት 8 በኢትዮጵያና በአሜሪካ በሚገኙ 20 ከተሞች የሚመረቅ ሲሆን ድሬዳዋም የዚህው መረዓ ግብር አንዱ አካል ነች። በመደመር መጽሐፍ በአማርኛ ፣ ኦሮምኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተፃፈ እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ቅጂዎችም የታተመ ሲሆን ይህ መጽሐፉ 300 ብር ዋጋ የተቆረጠለት እና ከሽያጩ የሚገኘው ገቢም በአገሪቷ ላሉ ትምህርት ቤት ግንባታ ይውላል ተብሏል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመጽሐፉ ይዘት ዙሪያ ማብራሪያና ትንተና ይሰጥበታልም ተብሎ ይጠበቃል።

PHOTO: #ተርቢኖስ_ዘደብረ_ሃይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ሁለተኛው ዙር ሙሌት #ዛሬ_ለሊት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተሰምቷል።

የውሀው መጠን ግንባታው የደረሰበት ከፍታ ላይ ደርሶ ዛሬ ለሊት ሞልቶ ይፈሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው "የሪፖርተር ጋዜጣ ድረገፅ" ሲሆን መረጃውን ከፕሮጀክቱ ስፍራ ማግኘቱን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia #SW ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ። የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ። ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው። በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን…
" አልሸባብ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል " - ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው

የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት እርምጃ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በሶማሌ ክልል በ5 ትናንሽ የጠረፍ አካባቢዎች ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራ በጸጥታ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሉ ተቆርጠው የቀሩትን የሽብር ቡድኑ አባላትን የማጽዳት ዘመቻ ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ባለፉት ቀን ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡ በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ጠቁመዋል፡፡

ነገር ግን የሽብር ቡድኑ #ዛሬ_ሌሊት ላይ የተበታተነ ኃይሉን በማሰባሰብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት አካባቢ ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም መሞከሮ ነበር።

ሆኖም የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ዳግም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራዎችን ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ነው ያብራሩት፡፡

እስካሁን ባለው መረጃም ከ150 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውንና የሽብር ቡድኑ ለአጥፍቶ መጥፋት ያዘጋጃቸው ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንደተማረኩ አመልክተዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል። የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል። የማረቆ፣ ቀቤና፣…
የደቡብ ክልል ዕጣፋንታ ምን ይሆን ?

መንግስት ክልሉ በክላስተር ተከፍሎ በአጎራባች ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አንድ ላይ በመሆን ሁለት አዲስ ክልል እንዲመሰርቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይህን አቅጣጫ ከተትሎም የዞን እና ልዩ ወረዳ ም/ቤቶች በየም/ቤቶቻቸው በመሰባሰብ በቀረቡላቸው የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ውሳኔ አሳልፈዋል፤ ውሳኔያቸውንም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አስገብተዋል።

አዎ! በመንግስት አቅጣጫ መሰረት በአንድ ላይ ሆነን በአዲስ 2 ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ያፀደቁ አጠቃላይ 10 ዞኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

ከእነዚህ መካከል ግን በብቸኝነት የጉራጌ ዞን " ክላስተር አልደግፍም ፤ የህዝቡም ፍላጎት አይደለም ፤ እኛ የምንፈልገው በክልል መደራጀት ነው ፤ ይህም በህጋዊ መንገድ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል " ሲል የክላስተር አደረጃጀትን በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህ በኃላ ግን በዛው በዞኑ ውስጥ ያሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በዞናቸው ም/ ቤት በአብላጫ ድምፅ የተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉ በመግለፅ " ክላስተር እንደግፋለን " የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

ውሳኔ ያሳለፉ (ትላንት) የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች ሲሆኑ #ዛሬ ደግሞ የቡኢ ከተማ፣ የደቡብ ሶዶ ወረዳ እና የሶዶ ወረዳ ምክር ቤቶች "ክላስተር እንደግፋለን " በሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

" ፌዴሬሽን ም/ቤት ስብሰባ ይቀመጣል "

የፌዴሬሽን ም/ቤት በ " ደቡብ ክልል " አደረጃጀት ጉዳይ ላይ ነሃሴ 12 #አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ እና ከክልሉ ጋር ተያይዞ የሚወስናቸው ውሳኔዎች እንደሚኖሩ የም/ቤቱን ህዝብ ግንኙነት ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ከ90 በመቶ በላይ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ እስካሁን ባለው አፈፃፀም ይህ ነው የሚባል ችግር እንዳልገጠመና አብዛኛው / ከ90 በመቶ በላይ ተፈታኝ ተማሪ / ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቱን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ይህን የተነገሩት ትላንትና ምሽት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተፈታኝ ተማሪዎችን እና እየቀረበላቸው ያለውን መስተንግዶ በአካል ተገኝተው በተመለከቱበት ወቅት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃላቸው ነው።

ከ90 በመቶ በላይ ተማሪ ወደ መፈተኛ ተቋሙ መግባቱን የተገለፁት ሚኒስትሩ ሙስሊሞች እና የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አማኞች #ዛሬ እሁድ ጥዋት እንደሚገቡ ፤ ከዚህ በኃላ ሁሉም ተማሪ ገብቶ #እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል፤ ነገ ሰኞ ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ " ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። " ያሉ ሲሆን " ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው። " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተማሪዎች የተሰጣቸውን መመሪያ አክብረው ፤ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ እንዲሁም በምንም ነገር እንዳይሸበሩ አደራ ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ለተፈታኞቹ " የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ " ሲሉ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አምባሳደር ማይክ ሐመር ኬንያ ይገኛሉ። የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ተነጋግረዋል። ፕሬዜዳንት ሩቶ ከአሜሪካው አምባሳደር ሐመር ጋር ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ " ሰላምና መረጋጋት ለአገሮች ልማትና ብልፅግና የግድ አስፈላጊ ነው " ያሉ ሲሆን ኬንያ ፤ አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም…
#Update

አምባሳደር ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው አምባሳደር ማይክ ሐመር በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር #ዛሬ ውይይት አካሂደዋል።

አቶ ደመቀ መኮን በውይይቱ ወቅት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆኑን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር በበኩላቸው፤ አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " በውይይቱ ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ተስማምተዋል " ሲል አሳውቋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ከቀናት በፊት #ኬንያ እንደነበሩና ከኬንያው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

አሜሪካ አምባሳደር ሐመርን ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም እና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ ወደ ኬንያ ፣ #ደቡብ_አፍሪካ ፣ ኢትዮጵያ እንደላከች ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።

Photo Credit : Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ነገ የሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ... የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የተናገሩት ፦ " በእጣው ብቁ የሚሆኑት የ20/80 (ስቱዲዮ ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን የ84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ።…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት ዕጣ #ዛሬ_ከሰዓት ይወጣል።

ይኸው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሚጠብቀው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ይተላለፋል ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ/Addis TV የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በቀጥታ ስርጭት እንደሚያስተለልፈው ቀደም ብሎ አሳውቋል።

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፃ ፤ ዛሬ ዕጣ የሚወጣባቸው በ20/80 18,930 ቤቶች እና በ40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25, 791 ቤቶች ሲሆኑ ከፍተኛ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የባለ ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት #ተጨማሪ 300 (ሶስት መቶ) ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባርና ለአዲሰ ተመዝጋቢዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዝርዝር የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ  ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል። የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ? #የመንግስት_ግዥ_ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት…
" በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው " - የፍትህ ሚኒስቴር

ትላንት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የፓርላማ አባሉ ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

የቀድሞው የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጫላ ዋታ፤ #ዛሬ_ረቡዕ ረፋድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፍትሕ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትን ዋቢ በማድረግ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ዘግቧል።

ዶ/ር ጫላ በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት #በሙስና_ወንጀል_ተጠርጥረው መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ ለድረገፁ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ማስታወሻ ፦ ዶ/ር ጫላ ዋታ የተጠረጠሩባቸው የሙስና ጉዳዮች ምንድናቸው ? እሳቸውስ ትላንት ለህ/ተ/ም/ቤት ምን አሉ ? መለስ ብለው በዚህ ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/77517

@tikvahethiopia