TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትላንት በትራፊክ አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተዘግቦ ነበር፦

• ከሟቾቹ ውስጥ ሦስቱ ጓደኛማቾች ይገኙበታል
• 3ቱም የ3ኛ ዓመት የአርኪዮሎጂ ተማሪዎች ናቸው
• ያቤሎ በሀዘን ተመታለች!
• እንደወጣን አንመለስም! …

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የተከሰተው ከኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል ኮንሶ ከተማ ኮንትሮባንድ ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረ ተሽርካሪ ከከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በደረሰው ከባድ የትራፊክ አደጋ ከ15 ሰዎች በላይ ህይወት አልፏል። ከቦራና ወደ #ወላይታ_ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ሴምስተር ምዝገባ ሲጓዙ የነበሩት የ3ኛ ዓመት የ#አርኪዮሎጂ #archeology ተማሪዎች የሆኑት ተማሪ #መቅደስ_ተሰፋዬ፣ ተማሪ #ትዝታ_ይድነቃቸው እና ተማሪ #ከና_ሚፊታ በመኪና አደጋ ሕይዋታቸው ተነጥቋል፡፡

ከሟቾቹ ውስጥ ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ሦስት ጓደኛሞች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ #ተመራቂ ተማሪዎች ነበሩ::

• (በመንገድ ላይ እየቀረን ነው)

ያገሬ ልጆች እንደወጡ አይመለሱም፤ አንመለስም!

ነፍስ ይማር!

Via Getu Temsegen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WSU የዛሬው እንግዳ ዶክተር ታከለ ናቸው! ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዓት ይከበር። #ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

#StopHateSpeech

•ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
•ቦታው፦ ከፕሬዘዳንት ህንፃ ፊት ለፊት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

የወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ11ኛው ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4000 በላይ ተማሪዎችን በድምቀት አስመርቋል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በመስጠት ሲሳተፉ ለነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ክቡር ዶክተር ዘብዲዮስ ጨማ ላለፉት 40 ዓመታት በወላይታ ባህል፣ ቋንቋ፣ እና በወላይታ ታሪክ ላይ በስፋት ለሰሯቸው ስራዎች የእውቅናና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ሌላኛው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው ኢትዮጵያዊ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገ/ወልድ ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ወልደሰማያት ገ/ወልድ 7ቱን የወላይታ ወረዳዎች በመቆርቆር የሚታወቁ የልማት አርበኛ እንደሆኑ ተነግሮላቸዋል። ህይወታቸውን በሙሉ በወላይታ ውስጥ ሲሰሩ በነበሩ የልማት ስራዎች ላይ ላደረጉት ትልቅ አስተዋፆ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🎂TIKVAH ETHIOPIA~2 ዓመት🎂

#ደብረ_ብርሃን #ወሎ #ጅማ #ሀረማያ #ሀዋሳ #ወልቂጤ #መቐለ #ወልዲያ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #ሆሳዕና/#ዋቸሞ/

📎የሰውልጅ በሰውነቱ የሚከበርበት፤ የግለሰቦች አመለካከት፣ እምነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ የኔ ነው የሚሉት ሁሉ የሚከበርበት፤ ፍቅር፣አንድነትና መተባበር የነገሰበት፣ የሰው ልጅ ሁሉ መሰብሰቢያ የሆነች ከጥላቻ የራቀች ሀገር እንገነባለን!! ተባብረን እንሰራለን፤ ለመጭው ትውልድ ኢትዮጵያን እናወርሳለን!!

እኛ ስንኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ ኢትዮጵያ ስትኖር እኛም እንኖራለን!

#ድፍን_ሁለት_ዓመት_በፍቅር_በመተባበር!

ነገ 6:00 አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት እንገናኝ፤ ከእናታችንም ምርቃት እንቀበል!! ሁላችሁም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ናችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ‹የአረንጓዴ አሻራ› ችግኝ ተከላ ቅድመ-ዝግጅት በስኬት መጠናቀቁ ተሰምቷል። በነገው ዕለት 50ሺህ የሚጠጋ ችግኞችን ለማስተከል እንደታቀደ ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአረንጓዴ አሻራ ቀን በወላይታ ሶዶ ችግኝ ተክለዋል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና አምባሳደር ተሾመ ቶጋን ጨምሮ፥ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞኑ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በሶዶ ከተማ ስምንት ችግኝ መትከያ ቦታዎች የተለዩ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንደኛው በመገኘት ችግኝ ተክለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶዶ ስታዲየም በመገኘት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ

የወላይታ ህዝብ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም የከፈለውን መስዋእትነት አሁንም ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት ለተጀመረው ጥረት ሊጠቀምበት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ከወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ በከተማው ስታዲየም ተገኝቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደማቅ አቀባበል አድርጓል። በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የወላይታ ህዝብ የአገሩን ዳር ድንበር በማስጠበቅ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው ብለዋል። ”ዛሬ እኔ እዚህ የተገኘሁት ሰኔ 16 ቀን በአዲስ አበባ በተሞከረው ጥቃት እኔን ለማዳን ሲል ራሱን በሰዋው ዮሴፍ አያሌው ስም ነው” በማለት ገልፀዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ HIWOT ASSEFA በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 606 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#606 #ወላይታ_ሶዶ #ሊቃ

🗓የሌሎች #ጀግኒቶች ውጤት ይቀጥላል🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH-ETH #የStopHateSpeech ሀገር አቀፍ ዘመቻዎች/በዩኒቨርሲቲ ደረጃ/ና በየተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ የተደረጉ ጉብኝቶችን ለመከታተል #የዩትዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ!

#ሀረማያ #ጅማ #ወልቂጤ #ሀዋሳ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #መቐለ #ዋቻሞ #ወሎ #ደብረብርሃን #ወልዲያ

Watch ""የአንድ እናት ልጆች ነን" በመቐለ ዩኒቨርሲቲ #TIKVAH_ETHIOPIA" on YouTube
https://youtu.be/qjyt56okb3U
እሁድን በበጎ ተግባር!

#አዲስ_አበባ

💫የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ የሙዚቃ ድግስ ነገ እሁድ ነሃሴ 26 በጌትፋም ሆቴል ይደረጋል። መግቢያ: 12 ደብተር - 2 እስክርቢቶ - 2 እርሳስ - 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ - የTIKVAH-ETH የአ/አ ቤተሰቦች እንዳትቀሩ! #onepackforonechild

💫Rotaract Ethiopia በጎ ስራ ላይ የተሰማራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ለአዲሱ አመት #አልባሳት እያሰባሰበ ነው እናተም ተሳተፉ ያላችሁበት መጥተው ይወስዳሉ ደውሉላቸው Rotaract club of Atrons President Yeabsera --- +251922175164. (Or Natnael -@Natysf +251923594536, Sofonias - @SophoDarik +251 92 453 9140

#ወላይታ_ሶዶ

💫"አለን ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ" ላለፉት ሁለት ቀናት ለ800 ተማሪዎች ለትምህርት የሚሆናቸውን ቁሳቁስ እያሰባሰበ ነው። በተጨማሪ የደም ልገሳ እየተደረገ ይገኛል። ነገም ለ3ኛ ቀን ይቀጥላል። ወላይታ ሶዶ ያላችሁ የTIKVAH-ETH ተከታዮችም እሁዳችሁን ከነሱ ጋር ማሳለፍ ትችላላችሁ። ስልክ +251913776084፣ 0926172318

#ሻሸመኔ

💫የሻሸመኔ ወጣቶች ነገ የይደግ በጎ አድራጎት ማእከልን ይጎበኛሉ እንዲሁም ግቢውን ያፀዳሉ። የሻሸመኔ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ኑ እሁድን በመልካም ስራ እናሳልፍ ከሰአት 8:00 ሰአት ላይ CDI እንገናኝ ብለዋችኃል!! ስልክ፦0926940304

#ለኩ
💫በለኩ ከተማ የሚገኙ "እኔም ለወገን" የበጎ አድራጎት ማህበር አባላት የሻይ ቡና ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። የለኩ ቤተሰቦቻችን እሁድን አብራችሁ!0986241726

💫"ነገ በለኩ ፉርቃን የአበባ እና የችግኝ መተከል ስነ ስርአት ስለሚኖረን የቻላችሁ ከጥዋቱ 3 ሰአት በለኩ ፉርቃን ግቢ በመገኘት አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጀመአችን ጥሪውን ያስተላልፋል" ቢላል የለኩ ሙስሊም በጎ አድራጎት ጀመአ

#ድሬዳዋ

💫"የድሬዳዋ ስካውት ካውንስል አባላት ነን በከተማችን የሚገኙ መንገዶች በግራና በቀኝ ያሉ ጠርዞችን ነጭ እና ጥቁር ቀለም በመቀባት ለመንገዱ ውበት እንዲሁም በምሽት ለአሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲታይ በማድረግ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አንፃር የበኩላችንን እየተወጣን ነው ። ስራው ገና አልተጠናቀቀም ነገም እለተ ሰንበት ይቀጥላል።"

#ወሊሶ

💫ወገኔን ለማስተማር እሮጣለሁ በከተማችን ቅን ወጣቶች የተቋቋመው የ" we are one" የበጎ አድራጎት ማህበር ባሳለፍነው አመት "ወገኔን ለማስተማር እኔም እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ታላቅ የእሩጫ ዉድድር ማሰናዳቱ የሚታወስ ነዉ። በዘንድሮ አመትም በተመሳሳይ መሪ ቃል በአይነቱ ልዩ በሆነ ሩጫ ዝግጅቱን አጠናቆ እርሶን እየጠበቀ ይገኛል ታድያ እርሶም የሩጫ ቲሸርት በመግዛት ከአላማችን ጎን ይሰለፉ። የቲሸርቱ ዋጋ 100 ብር የቲሸርቱ መገኛ ቦታ: ፓስታ ቤት፣የኛ ህንፃ ፣ክርኪስ እናም ሁሉም ቦታ አዙረው በመሸጥ ላይ ከሚገኙ አባላቶች

በሌሎች አካባቢዎች ያሉ እንቅስቃሴዎችን እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!
በዚህ ወር በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠሙ የእሳት አደጋዎች ፦

#ወልቂጤ_ከተማ (ጉራጌ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በኩር ክ/ከተማ አርሴማ መንደር

• የደረሰው ጉዳት - 14 ቤት ሙሉ በሙሉ 6 ቤት በከፊል ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው።

#ቤሮ_ወረዳ (ምዕራብ ኦሞ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ሾላ ቀበሌ

• የደረሰው ጉዳት - 1840 መኖሪያ ቤቶች፣ 547 የንግድ ቤቶች፣ 37 የወርቅ ማህበራት ፣ 109 የወርቅ ማሽን በአጠቃላይ 586 ሚሊዮን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እስካሁን አልታወቀም።

#ሆሳዕና_ከተማ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰው በአንድ የገበያ ማዕከል አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል። በርካታ የኤሌክትሮኒክስ እና አልባሳት ንግድ ድርጅቶች ከነ ንብረታቸው ወድመዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ፖሊስ እያጣራው ነው።

#መካነሠላም_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• በመካነ ሠላም ከተማ በንግድ ቦታ ላይ ድንገት የተከሰተ አደጋ።

• የደረሰው ጉዳት - በሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች፣ በሴቶች የውበት ሳሎን፣ በልብስ ስፌት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሳል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም።

#ወላይታ_ሶዶ_ከተማ (ወላይታ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - መርካቶ ገበያ

• የደረሰው ጉዳት - 1 ቢሊዮን 57 ሚሊዮን 670 ሺህ ብር ወድሟል። 42 ሺህ ገደማ ዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ለቀውስ ተጋልጠዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አንታወቀም፤ በፖሊስ እየተመረመረ ይገኛል።

#ማሻ_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - አዲሱ መናኸሪያ አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 2 ሼዶች በውስጣቸው ካለ ሙሉ ንብረት ጋር ወድመዋል። ሼዶቹ በውስጣቸው ሱቆች፣ ፖስታ ቤት፣ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ይገኙበታል። 1 ሚሊዮን 224 ሺህ 936 ብር የሚገመት ሃብት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም፤ እየተጣራ ነው።

#ዌራ_ወረዳ (ሀላባ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ

• የደረሰው ጉዳት - 11 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እህል የተከመረበት ቦታ ላይ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞባልይ ስልክ ፈንድቶ።

#ምሻ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ኤራ ጌሜዶ፣ ኩናፋ፣ ጉና ማጋቾ ቀበሌዎች

• የደረሰው ጉዳት - 128 ዶሮዎች፣ 243 ኩንታል የተለያየ እህል፣ 18 የንብ ቀፎ ፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች በድምሩ 23 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - የተፈጥሮ እሳት

#ሶሮ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በጃቾ ከተማ

• የደረሰው ጉዳት - ከ250 ሺህ ብር በላይ ወድሟል።

• የአደጋው ምክንያት - የመብራት ኮንታክት

#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

• የአደጋው የደረሰበት ቦታ - ዋናው ግቢ ህንፃ 3

• አደጋው የኤሌክትሪክ መቆጣጣሪያ ላይ የተነሳ ነው።

• የደረሰው ጉዳት - መጠኑ ያልተገለፀ ንብረት ጉዳት ደርሶበታል።

#ቡራዩ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ገብርኤል አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 16 ሱቆች ፣ 3 መኖሪያ ቤቶች፣ 3 ባርና ሬስቶራንቶች ቃጠሎ ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ ግምንቱ 10 ሚሊዮን ብር የሆነ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እየተጣራ ይገኛል።

#ባህር_ዳር_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 3 ጉዶባህር የሚባለው ሰፈር

• የደረሰው ጉዳት - 22 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በገንዘብ 300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - እንጀራ ከሚጋገርበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገሮች የተነሳ ነው።

#ጅግጅጋ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 2 ልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ

• የደረሰው ጉዳት - 7 የምግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ንብረት አደጋ ደርሶበታል ይህም 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ከአንድ ቤት ውስጥ ነው የተነሳው ተብሏል።

#ደብረማርቆስ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ጉልት ገበያ አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - 48 የንግድ ሱቆች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ቅመማቅመም፣ አትክልት እና ፍረፍሬ ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የንብረት ግምት እየተጣራ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም በፖሊስ እየተጣራ ነው።

በዚህ ወር በደረሱት የእሳት አደጋዎች በርካቶች ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረታቸው ፣ ቤታቸው ወድሞባቸው ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

በርካቶች ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ስራ አጥ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

* የአብዛኛዎቹ የእሳት አደጋዎች ትክክለኛ መንስኤ በግልፅ አይታወቅም።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Congratulations !

የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዛሬ ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።

#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ ባካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ስርዐት 5 ሺህ 726 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 448ቱ በ2ኛ ዲግሪ እንዲሁም ሰባቱ በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 31ዱ ሴቶች ናቸው።

#ወራቤ_ዩኒቨርሲቲ

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

#ኦዳቡልቱም_ዩኒቨርሲቲ

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 354 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ባካሄደው 3ኛ ዙር የምረቃ ስነስርዐት የተመረቁ ተማሪዎች፤ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች አስመርቋል።

3ኛ ዙር ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲው አራት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው። ዛሬ ከተመረቁት ተማሪዎች 428ቱ ሴቶች ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

የተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣ ግሬት ኮሌጅና ኤልኤም ኢንተርናሽናል የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

Source : @tikvahuniversity
“ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” - የተሽከርካሪው ባለቤት

“ እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

#ከአዲስ_አበባ ተነስቶ ወደ #ወላይታ_ሶዶ 70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በሻሸመኔ እና ሀዋሳ መካከል ከቶጋ ካምፕ አለፍ ብሎ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ በሚገኝ ቦታ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ ላይ በታጠቁ ኃይሎች እንደተወሰደና እንዳልተመለሰላቸው የተሽከርካሪው ባለቤት፣ ሌላ እማኝና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት በሰጡት ቃል፣ “ ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” ሲሉ ገልጸዋል።

እንዲህ ያደረጉ አካላት ማን እንደሆኑ ሲያስረዱ ፣ “ ደብል ጋቢና በሆነ መኪና (አሮጌ ነገር ነው) እርሱ ላይ ሰዎች ነበሩ፣ 3 ክላሽ 1 ሽጉጥ የያዙ። ‘ኬላ ጥሳችሁ ነው የመጣችሁት አሉ’። ኬላ አልጣስንም ያው ደረሰኙ ቢላቸውም ‘አይ ውረድ ውረድ’ ብለው ሹፌሩን በሰደፍ መቱት ጭንቅላቱ ላይ፣ ጋቢና ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎችንም አስወረዱ እነርሱንም ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው ” ነው ያሉት።

በገመድ አስረው ፣ አፋቸውንም በፕላስተር አስይዘው እንደነበር በኃላም አላሙዲን እርሻ ፊት ለፊት ባለው አቅጣጫ መኪናውን ይዘው እንደሄዱ ተናግረዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት ፤ በሰደፍ ተመቱ የተባሉት ሰዎች ቢለቀቁም ቁስሉ እንዳልተሻላቸው ገልጸዋል።

“ ዱቄቱ 70 ኩንታል ነው። 210 ሺሕ ብር ይገመታል። መኪናው  አዲስ ነው 2022 ሞዴል ቢ 24 ነው። መኪናውን ይመልሱልኝ ” ሲሉ የመኪናው ባለቤት ተማጽነዋል።

ሌላኛው ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አካል በበኩላቸው፣ “ ሹፌሩንና ረዳቱን ደበደቡ። የኤሌክትሪክ ፓል ጋ ሹፌሩን አሰሩ። ከዚያ መኪናውን ይዘው ሄዱ። እስከዛሬ ፋይዳ የለም ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

ተፈፀመ የተባለውን ድርጊት አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ቡኩሉ ፣  70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ የነበረው ተሽከርካሪ በሻሸመኔ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ እንዲቆም ተደርጎ እንደተወሰደ፣ ሰዎቹ ተደብደብዋል መባሉም እውነት ነው እንደሆነ ገልጿል።

አንድ የማኀበሩ ኃላፊ ፤ ሌላም እዚህም ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ከድሬዳዋ ዘይት ጭኖ የቆመ መኪና ሰሞኑን ጠፍቶ እንደነበር፣ መጨረሻም ጭነቱ ተራግፎ ቆሞ እንደተገኘ አስታውሰው፣ " ትክክል ነው የሻሸመኔውም። እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው " ብለዋል።

" ምክያቱም በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስን ወንጀል በወንጀልነት ቆጥሮ በጸጥታ አካል አድኖ የመያዝ ሂደት አናሳ ሆኗል። አይደለም እቃውን የሰውን ሕይወት መጥፋትም በተለይ በመንግሥት ሚዲያዎች ሲዘገብ አናይም " ሲሉ አክለዋል።

" እገታና ዝርፊያ በጣም ተበራክቷል። " ያሉት እኚህ ኃላፊ " ሜዳ ላይ አስቁመው ደብድበው የሚፈልጉትን ይዘው ነው የሚሄዱት " ሲሉ የሁኔታውን አስከፊነት አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ወደ ሻሸመኔ ከተማ ፓሊስ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። #TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia