TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ

" ተጠርጣሪው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል " - ፖሊስ

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ቪዛ እናስጨርሳለን ! " በሚል #ቲክቶክ በተሰኘው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚጓዙ ሰዎች ቪዛ እናስጨርሳለን ! " እያለ በቲክቶክ ሲያጭበረብር የነበረው ይኸው ግለሰብ ከ25 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን  በማጭበርበር ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል።

በቲክቶክ ሀሰተኛ የግለሰቡ ማስታወቂያ የተጭበረበሩት አብዛኞች ወደ #ካናዳ ለመጓዝ ፍላጎት አሳይተው ከተጠርጣሪው ጋር የተገናኙ ናቸው።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ የቪዛ ፕሮሰስ እጨርሳለሁ " ቢልም ተበዳዮችን የተለያየ ቦታ እየቀያየረ እያገኛቸው  ቪዛ እንዳለቀላቸው እየነገረ እና ሌሎች ምክንያቶችን እየሰጠ ከእያንዳንዳቸው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብሏል።

ተጠርጣሪው የማታለል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ የታወቀው " ቪዛ አልቆልሃል " ተብሎ 600 ሺህ ብር የከፈለ አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ ሀገር ለመሄድ አየር መንገድ በተገኘበት ወቅት #ቪዛው_ሃሰተኛ መሆኑ ከተነገረው በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ነው፡፡

አሁን ላይ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ አግባብ ቤቱ ሲበረበር ሀሰተኛ ሰነዶች እና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

#AddisAbabaPoliceCommission

@tikvahethiopia