TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ወደ ጦርነትና የእርስ በርስ #ግጭት የሚሄድ ነገር ይኖራል ብለው እንደማያስቡ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም #ብርሃኑ_ጁላ ተናገሩ፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኦነግ በሬ እያረደ በተቀበለው ህዝብ ላይ ዘረፋና #ግድያ ፈጽሟል” ጄኔራል #ብርሃኑ_ጁላ

• ሠራዊቱ ከትግራይ እንዳይወጣ የሞከሩት ህዝቡና የክልሉ መንግሥት አይደሉም

• መከላከያን ከኃላፊነቱ ውጪ የክልሎችና የፖለቲካ ሥራን የማሠራት ፍላጎት አለ

• በሠራዊቱ ላይ ጥላቻ በመንዛት አገርን ለማፍረስ የሚሠሩ አሉ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል #ብርሃኑ_ጁላ

‹‹በውትድርና ዘመኔ በራስ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ #ጥቃት ተፈጽሞ #ያየሁት በምዕራብ ወለጋ ነው››

‹‹ለረጅም ዓመታት በውትድርና አገልግያለሁ፣ እንዲህ ዓይነት #ጭካኔ በወለጋ ከተፈጸመው በስተቀር አይቼ #አላውቅም፤››

‹‹በምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን ጭካኔ በቅርቡ #በቪዲዮ ምሥል ጭምር #ታዩታላችሁ፤››

‹‹የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ #ወለጋ ሲገባ ያገኘነው #ጉድ ዘግናኝ ነው፤››

https://telegra.ph/በውትድርና-ዘመኔ-በራስ-ሕዝብ-ላይ-ጭካኔ-የተሞላበት-ዘግናኝ-ጥቃት-ተፈጽሞ-ያየሁት-በምዕራብ-ወለጋ-ነው-01-09-2
Audio
"ታጣቂዎች "መከላከያ ሰራዊት" ላይ ተኩስ ከፍተዋል" የመከላከያ ሰራዊት
.
.
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት በተባለ ቀበሌ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት በተተኮሰ ጥይት 27 ሰዎች መመታታቸውንና ከእነዚህ ውስጥ ሰባት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን የዓይን እማኝ መሆናቸውን የተናገሩ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለፁ። ግድያውንም በመቃወም ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የሆስፒታል ምንጮች ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ነግረውናል። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ በበኩላቸው በአካባቢው በመንገድ ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያን አጅቦ በመውጣት ላይ በነበረ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የታጠቁ ሰዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር‼️

በጎንደር በተከሰተው ግጭት ዙሪያ የሚወጡ #የተምታቱ መረጃዎች ለውጡን የሚጎዱ መሆናቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጡት የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ምክትል ኤታ ማጆር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ እንደተናገሩት በጎንደር በተከሰተው ግጭት ዙሪያ የተምታቱ መግለጫዎች እየወጡ ነው፡፡

ስለ ክስተቱ ተገቢው የማጣራት ስራ ሊሰራ ይገባል፡፡ ተገቢው #የማጣራት ስራ ሳይሰራ መከላከያው ህዝብን ገድሏል ተብሎ እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎችና በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች ተገቢነት የጎደላቸው ናቸው፤ የተጀመረውን ለውጥም የሚጎዳ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ‼️

በምዕራብ ኦሮሚያ ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መከሰቱን እና አሁን ግን #በቁጥጥር_ሥር እየዋለ መሆኑን የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም አስታወቁ። ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ በተጠቀሰው አካባቢ ተስፋ ሰንቆ ከውጭ የገቡ አካላትን የተቀበለው ሕዝብ መልሶ ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጉን አመልክተዋል። አሁን እየተወሰደ ባለው #ጠንካራ_እርምጃ አማካኝትም የተዘጉ መንገዶች እና አደጋ ላይ የወደቁ የመንግሥት የመዋቅር ሥፍራዎች መከፈታቸውንም ዘርዝረዋል።

ከተማዎቹን እየዞሩ ያተራምሱ ነበር ያሏቸው አባ ቶርቤ በሚል መጠሪያ የሚታወቁ ኃይሎችም በመንግስት ቁጥጥር ሥር መግባታቸውንም ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ገልጸዋል።

«አሁን #ትጥቅ_ማስፈታት ጀምረናል፤ እነዚያ የተዘጉ ከተሞች ነጻ አውጥተናቸዋል። የተዘጉ መንገዶች ተከፍተዋል፤ ሰዎች እንደተዘረፉ አውቃለሁ፤ ሸሽተው አዲስ አበባ የገቡ እንዳሉ አውቃለሁ፤ አባ ቶርቤ የሚባል በየከተማው እየዞረ ነፍስ የሚገድል ፤ የሚያስፈራራ ይሄን ለቅመነዋል።» ብለዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ከሰሞኑ በተከሰተው ወቅታዊ ሁኔታ መከላከያ ሰው አልገደለም ያሉት ጀነራሉ ክስተቱ #እንዲጣራ መወሰኑን፤ ድርጊቱ ተፈፅሞም ከሆነ መከላከያ ይቅርታ እንደሚጠይቅ #ካሳም እንደሚከፍል አመልክተዋል። ባለሥልጣኑ በተለያዩ አካባቢዎች ስለደረሰዉ ጉዳት ምንም አይነት አሃዛዊ መረጃ መስጠት እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አገር መከላከያ ሰራዊት‼️

#በዳውድ_ኢብሳ የሚመራው #ሸኔ የተሰኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ በምእራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች እየፈጸመ ያለው ፀረ-ህዝብና ፀረ ሰላም ተግባር ህዝቡ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን #ማስወገዱን የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ አስታወቁ።

ቡድኑን #ትጥቅ_የማስፈታት ስራም አጠናክሮ እያከናወነ መሆኑንም ጀነራሉ ተናገረዋል። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማካሄድ ከመንግስት ጋር #ተስማምቶ ወደ አገር የተመለሰው የዳውድ ኢብሳው ኦነግ የገባውን ቃል ኪዳን #በማፍረስ ህዝብና አገርን በሚጎዳ ተግባር በመሰማራቱ እርምጃው እየተወሰደበት መሆኑን ነው ጀነራሉ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት።

በአሁኑ ወቅት ቡድኑ አፈግፍጎ ወደ ጫካ #እየሸሸ ቢሆንም ሰራዊቱ ህግ የማስከበር ስራውን ከአካባቢው ህዝብና የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አክለው ገልጸዋል።

እርምጃው የሚወሰደው በኦነግ ታጣቂዎች የተለያየ ህገ ወጥ አርምጃና ግፍ የተማረረው ህዝብ #ባቀረበው_ጥያቄ መሰረት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ አንድም ሰላማዊ ሰው እንዲሞት አልፈልግም" ብ/ጄ #ብርሃኑ_ጁላ
.
.
.
ሰሞኑን ሰባተኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን ተከብሯል። በበዓሉ የማጠቃለያ ዝግጅት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ "የመከላከያ ሠራዊቱ ለጠላቶች የፍርሃት፤ ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ የኩራት ምንጭ ነው" ሲሉ ለሠራዊቱ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ነገር ግን በተለያዩ ጊዜያት ሠራዊቱ በተሰማራባቸው አካባቢዎች ከሚከሰቱ የሰላማዊ ሰዎች ጉዳቶች ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል። የቅርቡን ለመጥቀስ በአማራ ክልል፣ በምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት ቀበሌ፣ ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ተተኮሰ በተባለ ጥይት በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና ግድያውን በመቃወም የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞ ማሰማቱ የሚታወስ ነው።

ከቀናት በፊት (ማክሰኞ የካቲት 5/2011) በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ፣ ሂዲሎላ በምትባል ከተማ አምስት ግለሰቦች ተገድለው፤ ሌሎች ሁለት ዜጎች ደግሞ ቆስለዋል። ከሟቾቹ ሁለቱ ከሠርጋቸው እየተመለሱ የነበሩ #ሙሽሮች ናቸው። የተቀሩት ሦስቱ ደግሞ አጃቢዎቻቸው። የአካባቢው ነዋሪዎችም ግድያው #በመከላከያ_ሠራዊት እንደተፈጸመ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ #በዳኔ_ሊበን፣ መከላከያ በቅርቡ ወደ ከተማዋ መግባቱን ገልጸው ስለክስተቱ በስፍራው የሚገኘውን የመከላከያ ኃይል ጠይቀው "ተኩስ #ተከፍቶብን ምላሽ ስንሰጥ ነው አደጋው የደረሰው" የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

በዚህና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የመከላከያ ሠራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም የሆኑትን ብርጋዴየር ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ቢቢሲ ረቡዕ እለት አነጋግሯቸው ነበር።

ቢቢሲ፡ በቦረና ዞን ሰሞኑን ስለተከሰተው ነገር የሚያውቁት ነገር አለ?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ የትናንትናና የዛሬ መረጃ የለኝም ከቢሮ ውጭ ስለሆንኩ። ነገር ግን መከላከያ በፊት በአንዳንድ ቦታዎች ስህተት ይሰራ ነበር። ያ አስተሳሰብ አሁንም አለ። በተጨባጭ ግን ያን ችግር ቀርፈን ነው እየሰራን ያለነው። ሆኖም ሰላምን የሚያደፈርሱ፣ የሕግን የበላይነት የሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ ሕጋዊ ስለሆነ ለእሱ መልስ የለኝም። ነገር ግን ሕዝቡ ላይ መከላከያ ችግር እያደረሰ ነው የሚባል ነገር ካለ መከላከያ ተጠያቂ ይሆናል።

ቢቢሲ፡ የሕዝቡ ቅሬታ ተጨባጭ አይደለም እያሉኝ ነው?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ ችግሩ መከላከያ ሰው ገደለ ከተባለ ሚዲያ ያንን ወስዶ ይዘግባል። ቦታ ላይ ሄዶ አጣርቶ፣ እውነት የቱ ጋ ነው ያለው ብሎ አይፈትሽም። አንተ እንደሚባለው መከላከያ ወጥቶ ሌላ ተልእኮ የሌለው ሰላማዊ ሰው ላይ እርምጃ ይወስዳል ብዬ በፍጹም አላምንም። ምናልባት እርምጃ ወስዶም ከሆነ እዚያ አካባቢ አንድ የሆነ ችግር አለ ማለት ነው።

ቢቢሲ፡ መከላከያ ምንም ስህትት አይሰራም ነው የሚሉኝ?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ ለምሳሌ አንዳንድ ኃይሎች አንዳንዴ ደፈጣ ያደርጉና መከላከያ ላይ እርምጃ ይወስዳሉ። በዚህ ጊዜ መከላከያ ራሱን ለመከላከል ምላሽ ሲሰጥ በተኩስ ልውውጥ አንድም ሰው አይጎዳም ልልህ አልችልም።

ቢቢሲ፡ እርስዎ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በመከላከያ በተፈጸመ ስህተት ተጠያቂ የሆነ የሠራዊቱ አባል አለ?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ ምንም ስህተት አልተሰራም። የተሰራ ስህተትም አላየንም። እኛ የምናውቀው መንግሥትም ሆነ ክልሎች እንዲሁም በእኛም ደረጃ የተገደለ ሰላማዊ ሰው የምናውቀው የለም። እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ አንድም ሰላማዊ ሰው እንዲሞት አልፈልግም። እኔ የማዘው ወታደርም ይሄንኑ ነው ተግባራዊ የሚያደርገው። እንዲህ የሚያደርግ ወታደር ካለም በሕግ ነው የምጠይቀው። በመከላከያ ላይ የሚደረግ ስም ማጥፋት ነው እንጂ መከላከያ ሕዝቡን እየጠበቀ ከሕዝብ ጋር እጅ ለእጅ ሆኖ ነው ሥራውን እየሰራ ያለው።

ቢቢሲ፡ ሪፎርም ተደርጓል በመከላከያ ይባላል። ምንድነው በተጨባጭ የተቀየረው?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ በተጨባጭ የተቀየረው የመከላከያ አደረጃጀት ነው። በመከላከያ ውስጥ ከላይኛው አመራር ጀምሮ እስከ ታችኛው ድረስ የኢትዮጵን ብሔር ብሔረሰቦች በሚመስል መልኩ ተደራጅቷል። ከዚህ ውጭ አመለካከት ነው የተቀየረው። ወታደሩ የአንድ ብሔር ወይም የአንድ ክልል ወታደር ሳይሆን የአገር ሠራዊት እንደሆነ እንዲረዱ በማድረግ የአመለካከት ለውጥ መጥቷል።

ከዚህ በፊት የነበሩ አንዳንድ ችግሮች እንዲስተካከሉ፣ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሰረት ብቻ እንዲንቀሳቀስ፣ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጎ እንዲሰራ፣ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን የመሳሰሉ ዓይነት ሥራዎችን ሠርተናል። የቀረን ነገር የለም ማለት ግን አይቻልም።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኢትዮጵያ #የጥፋት ኃይሎች በስፋት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን የምዕራብ ኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በወሰደው #እርምጃ ማረጋጋት እንደተቻለ የኢፌዴሪ መከላከያ ምክትል ኢታማጆር ሹም ጀኔራል #ብርሃኑ_ጁላ ተናገሩ ። ዛሬ የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በአሶሳ ከተማ ገምገማ አካሂዷል። በግምገማው ወቅት ህብረተሰቡ ከነበረበት የሥጋት ስሜት ወጥቶ በአካባቢው #ሠላማዊ በሆነ መንገድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተገልጿል፤ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ይገባል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia