TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሲቢኢ #ዩኒቨርሲቲዎች #ኦዲት

" ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል፤ ዝውውሩም አይታወቅም ብለው አስበው ነው ያደረጉት " - አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ስለነበረው የመጋቢት 6 ለሊት የገንዘብ ዝውውር እና አጠቃላይ ወጭ ስለተደረገው / አሁን ስለተመለሰው የገንዘብ መጠን ምን አሉ ?

አቶ አቤ ሳኖ ፦

" የተቋረጠውን አገልግሎት ካስጀመርን በኃላ ወደ ግብይቶች ምርመራ ነው የገባነው።

በዛ ያለ ግብይት ያደረጉትን ለይተናቸው የፍትሕ አካላት እንዲያውቁት አድርገናል። በብዛት በዛ ያለ ቁጥር ያለው እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ #በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ነው።

ተማሪዎቹ (የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ) ያሰቡት ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል ብለው ነው። ስለዚህ የሚደረገው ግብይት (ወጭ / ዝውውር) አይታወቅም ብለው ነው ያደረጉት።

አሁን ላይ ግን ግብይቱ እንደሚታወቅ ሲያውቁ የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ ነው ያሉት። አሁንም እንዲመልሱ ነው የምንፈልገው።

የወሰዱትን ገንዘብ ከመለሱ ወደ ክስ አንሄድም። የማይመልሱ ከሆነ ግን የህግ እርምጃ እንወስዳለን።

ዝርዝር ጉዳዩ (ከገንዘብ ዝውውር/ወጭ የተደረገ/የተመለሰ) ኦዲት ተደርጎ ሲያልቅ ይቀርባል።

የኦዲት ሂደቱ ስላላለቀ በዚህ መካከል ሌሎች ነገሮችን ማንሳት ከፋይናንሻል ኦዲት አካሄድ ጋር የሚሄድ ስላልሆነ አንዳንድ የህጋዊ እርምጃዎችም ሊከተሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ ነው። "

@tikvahethiopia