TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" እጅግ ነውር ተግባር ነው "

ከ2 ዓመት በፊት የቀረበን ሪፖርት በቀጥታ ገልብጦ ያቀረበው የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር” እጅግ ነውር ተግባር” ፈጽሟል ሲል የዉሃ ፣ መስኖ ፣ ቆላማ አከባቢ እና አከባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

ቋሚ ኮሚቴው የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ9 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲያቀርብ በተገኘበት መድረክ ምንም ዓይነት የሪፖርት ማሻሻያ ሳያደርግ በቀጥታ #እየገለበጠ እንደሚያስተላልፍ ደርሼበታለዉ ብሏል።

ዛሬ ቋሚ ኮሚቴው የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።

በዚህም ወቅት ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፖርቶችን በቀጥታ ገልብጦ ከማምጣቱም ባሻገር የተቋሙ የበላይ ሃላፊዎች #የማያዉቁት እና #ያልተገመገመ ሪፖርት ለምክርቤት መላኩ " እጅግ ነዉር ነዉ " ሲል ወቅሷል፡፡

ሪፖርቱ ከ2012 ጀምሮ እስካለንበት 2014 የግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርቶች #በቀጥታ ተገልብጠዉ የተላለፉ ናቸዉ።

ለማሳያነትም ፤ በስነምግባር እና በጸረ ሙስና ብልሹ አሰራሮች ናቸዉ ተብለዉ ከቀረቡት 16 ጥቆማዎች መሀል 13ቱ ተጣርተዉ መልስ የተሰጣቸዉ ሲሆኑ 3 ጥቆማዎች በሂደት ላይ የሚገኙ ናቸዉ " የሚለዉ አፈጻጸም ከ2012 የ9 ወር ሪፖርት ቃል በቃል ምንም ለዉጥ ሳይደረግበት ተገልብጦ የመጣ መሆኑን በግልጽ ያሳያል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ፈትያ አህመድ ገልፀዋል።

ሰብሳቢዋ ይህንን ሀሰት ነዉ የሚል አካል ካለ በርካታ ተጨባጭ የሰነድ ማሳያዎች ማቅረብ እንችላለን ሲሉ ተናግዋል።

በሚኒስቴር ዲዔታ ማዕረግ የሚኒስቴሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ በሪፖርቱ ላይ የቀረበዉ ትችት ትክክል እንደሆነ አምነዋል።

የሪፖርት ጥራትና ወቅታዊነት ጉዳይ ፍጹም ለጥያቄም ቢሆን የሚቀርብ ጉዳይ እንዳልሆነ አንስተዋል። ይህም መስተካከል እንዳለበት እንደሚያምኑ እና የተለያዩ መ/ቤቶች አንድ ላይ መዋሃድ ይህንን ክፍተት መፍጠሩን እንደምክንያት አንስተዋል።

በቀጣይ ይህንን አስተካክለዉ እንደሚቀርቡ ገልጸዉ ቋሚ ኮሚቴዉን ይቅርታ መጠየቃቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia