TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሁሉም ውስጡ #ስጋና #ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ #አንድ ነው አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ #አዳም
.
.
ሰውነት ይከበር!
ሰውነት ይቅደም!
#ETHOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከልዩነታች ይልቅ #አንድነታችን እጅግ እንደሚገዝፍ በቅዱሳን መፃህፍትም ሆነ በሳይንስ ተረጋግጦ ሳለ ይበልጥ #ልዩነታችን ላይ ማተኮራችን ምክንያቱ ምን ይሆን 🔅ሶስት ማዕዘን
.
.
ሁላችንንም #አንድ የሚያደርገን ከኢትዮጵያዊነታችን፤ የአንድ ብሄር ተወላጅ ከመሆናችን በላይ #ሰው መሆናችን ነው። ስለሰውነት በቅጡ #መረዳት ካልቻልን መጪው ጊዜ ይከፋብናል። ሁላችንም ስለሰው ክቡርነት እንነጋገር፤ ማንም ሰው በብሄሩ፣ በዘሩ፣ በሀይማኖቱ ሳይሆን ሰው በመሆኑ ብቻ #ሊከበር ይገባዋል!!

ለ30 ደቂቃ በዚህ ጉዳይ ተነጋገሩ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቀለ...

"የሐገር መሠረት ቤተሰብ ነው፡፡ አያትና ቅድመ አያቶቻችን በአንድነት ና በፍቅር ሆነው የኢትዮጵያን እና የጥቁር ህዝቦችን #ነፃነት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው አቀዳጁን፤ እኛ ታዲያ ልጆቻችንን እሕት ወንድሞቻችንን ከቤት እስከ ጎረቤት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ድሮም #አንድ አድርጎ ያስተሳሰረን ውድ ፍቅራችንን ፣ #እሴቶቻችን መንገርና በተግባር ማሳየት ያቅተናል? እኛ የተሳሳተ አስተሳሰብ እንጂ #የሰው_ጠላት_የለንም፤ ሰው በሰውነቱ እኩል ነው ፤ የሃሳብ ልዩነቶቻችንን በሰከነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እየቻልን ጥላቻንና በቀልን በመዝራት ሞትን፣ ውድመትንና መከራን ስለምን እናጭዳለን?? እኛኮ ውድ የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጆች ነን፤ እኛኮ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት አርማ ኩራታቸው ነን፤ አባቶቻችን በታላቅ መስዋዕትነት የገነቡትንና ያወረሱንን ድንቅ ታሪካችንን በመገዳደልና በመዘራረፍ ለአለም ሕዝብ #መሳለቂያ መሆን #ያሳፍራል፤ ተው ወገን ይህም ያልፍና ቀጣይ ትውልድ ይታዘበናል...የአገራችን ሰላም በእጃችን ነው አንድም ለማፍረስ አንድም ሰላማችንን ለማስቀጠል፡፡ አሸናፊ ግርማ ከመቖለ ዩኒቨርሲቲ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

(አቶ አዲሱ አረጋ)

ሰሞኑን በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን ለማስከበር በተደረገ እንቅስቃሴ በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና የመሰረተ ልማት መገንቢያ ቦታዎች ላይ የተገነቡ እና ከከተማዉ የመሬት አጠቃቃም ፕላን ጋር የሚቃረኑ 347 ቤቶች እና በአጥር የተከለሉ ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ይታወቃል። የተወሰደዉን እርምጃ ተከትሎ ሰፊ #ቅሬታ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

ህገ ወጥነት መከላከል #ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ ባይሆንም በአፈጻጸሙ ሂደት የተፈጠሩ #ግድፈቶች እና #ስህተቶች ካሉ ለይቶ ማረም አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ግብረ ሀይል ተደራጅቶ ወደ አካባቢዉ እንዲሰማራ ክቡር ፕረዚዳንት #ለማ_መገርሳ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ግብረሃይሉ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ወደማጣራት ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ ሪፖርት መሰረትህገወጥ ግንባታን በማፍረስ ሂደት የተፈጸሙ ስህተቶች ካሉ ህግን ተከትለዉ የሚታረሙ ይሆናል።

ህገ ወጥ ግንባታ የፈረሰባቸዉ የደሃ ደሃ የሆኑ ወገኖቻችን ያለ #መጠለያ እንዳይቀሩ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ መሰረት ህግና ስርኣትን በተከተለ መንገድ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

የተወሰደዉ ዕርምጃ #አንድ_ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት አስመስሎ በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ሚዲያዎች እየቀረበ ያለዉ ዘገባ #ሀሰት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

#Addisu_Arega_Kitessa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ተስፋዎች👆

#ሰውነት ያስተሳሰራቸው፤ #ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች #የተሰባሰቡ፤ ሀገራችንን ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ለማውጣት በየዩኒቨርሲቲው እየተጓዙ የሚገኙት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #ኑ ኢትዮጵያን #ከጥላቻ አላቀን #ታላቅ እናድርጋት የሚል #ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ: የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት #ለእንግዶቹ ያደረገው #የእራት እና #የምሳ ግብዣ #WKU

Photo: @Dura_pic

ደማችን #አንድ ነው!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁሉም ውስጡ #ስጋና #ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ #አንድ ነው አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ #አዳም
.
.
ሰውነት ይከበር!
ሰውነት ይቅደም!
#ETHOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሁላችንም አንድ እንሁን፣ #ሰላም እናስፍን፣ ከእንደዚህ አይነቱና አላህ ከማይወደው ተግባር እንራቅ፣ እስላም ክርስቲያኑ ሁሉ በአንድ ሆነን አገራችንን እናልማ፣ ሰላም እንፍጠር፣ ከመተላለቅ እንዳን። እባካችሁ ሁላችንም ለአላህ ብለን ከዚህ ተግባር እንቆጠብ...ሰላም ማጣታችን ያሳዝናል። ፍቅር ማጣታችን ያሳዝናል። ኡለማዎችንን ማስለቀሳችን ያሳዝናል። አንድነት ማጣታችን ያሳዝናል። አሁን #አንድ_ሆነን_ቆራጥ ሆነን ልንነሳ ይገባል። አንድ እንሁን፤ የከተማውም የገጠሩም እስላም እና ክርስቲያኑም አንድ እንሁን። አንድ ሆነን ቆራጥ ሆነን እንነሳ። እውነቱም ይታወቃል፤ ውሸቱም ይታወቃል። ለእውነት እንድትሰሩ አሳስባለሁ። አደራም እላለሁ። አሚን።” ሀጂ ኡመር ሙፍቲ (ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ፕሬዚዳንት )

#share #ሼር

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

አንድ መራጭ ለክልል ምክር ቤት መቀመጫ ምን ያህል እጩዎችን መምረጥ ይችላል?

ለክልል ወይም ለከተማ ም/ቤት መቀመጫ አንድ መራጭ መምረጥ የሚችለው የእጩዎች ብዛት እንደየምርጫ ክልሉ ይለያያል።

አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 1 እጩ፣ እንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 3 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ላይ 9 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 14 እጩዎች ወይም ሌላ ቁጥር ያለው የመቀመጫ ብዛት ሊኖራቸው ይችላል።

ብዛቱ የሚወሰነው የምርጫ ክልሉ በክልል ምክር ቤቱ ባለው የመቀመጫ ቁጥር ብዛት ነው።

በመሆኑም አንድ መራጭ በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ መምረጥ የሚችለው የዕጩዎች ብዛት በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ከላይ ተፅፎ ይገኛል።

በዚህም መሰረት አስፈጻሚዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጡ ለመራጩ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ እስከ ስንት እጩ መምረጥ እንደሚችል ያስረዳሉ።

ሆኖም ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አንድ ዕጩ ብቻ የሚመረጥ ይሆናል። ስለዚህም ከዚህ ቁጥር ገደብ በላይ ምልክት የተደረገባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አይኖራቸውም።

ስለሆነም ድምፅዎን ሲሰጡ በወይን ጠጁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወረቀት #አንድ በክልል ምክር ቤት ወረቀት ደግሞ ወረቀቱ ላይ በተጻፈው እና ምርጫ አስፈጻሚው በሚነግርዎ ቁጥር መሰረት መሆኑን አይርሱ። ከተፈቀደው የእጬ ቁጥር በላይ ምልክት አያድርጉ።

#ሼር #Share

(የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አንድ_ሚሊዮን_ዳያስፖራ ወደ ሀገር እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ሰሜን አሜሪካና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በራሱ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚፈለገውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትኬት ቅናሽ እንዲሁም ተጨማሪ የሻንጣ የኪሎ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና አየር መንገዱ የማይበርበትም ሥፍራ ቢኖር፣ ገበያውን ለማምጣት እንደሚሰራ ከአየር መንገዱ መስማቱል ሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚ ቀደምም ሆነ ወደፊትም ለልዩ ልዩ በዓልና ተመሳሳይ ወቅቶች የተለየ ቅናሽ እንዲሁም አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በሌላ አጭር መረጃ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ''ቢዝነስ ትራቭለርስ '' መጽሄት የሚያዘጋጀውን “የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች የአፍሪካ ምርጥ” አሸናፊ ሆኗል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ሊያገኝ የቻለው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያያዘ እየወሰዳቸው ያሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች ፣ ከጉዞ ትኬት ጋር በተገናኘ የሚሰጠው ፈጣን ምላሽ እንዲሁም በወረርሽኙ ወቅት ለተከሰቱ የጉዞ መስተጓጐሎች ለሰጠው የተቀላጠፈ የጉዞ ማስተካከያ አገልግሎት እና ተያያዥ መስፈርቶች በቢዝነስ መንገደኞች በመመረጡ ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ 6710 ከA/B/C/D ወደ " OK " መቀየሩን አሳውቆናል።

በኢትዮ ቴሌኮም ድጋፍ ለልብ ሕሙማንን የሚለገስበት 6710 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ከዚህ በፊት ከ1 ብር እስከ 100 ብር ድጋፍ የሚደረግበት A/B/C/D አማራጭ ወደ “OK” ተቀይሯል።

አሁን ላይ አንድ ጊዜ ብቻ " OK " ብሎ ወደ 6710 በመላክ እና በመመዝገብ በቀን አንድ ብር ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡

#6710_OK📨
#አንድ_ብር_ለአንድ_ልብ!💖

ይህንን መልዕክት በማጋራት ለብዙሃን ያድርሱ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጋምቤላ ክልል ፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጠዋት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸው ይታወሳል። ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ…
#Gambella

በጋምቤላ በዚህ ሳምንት ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ንፁሃን ዜጎች ላይ ከማዋከብ አንስቶ እስከ ግድያ የደረሰ ከዚህም በተጨማሪ የዝርፊያ ድርጊት መፈፀሙ መጠቆሙ ይታወሳል።

ክልሉ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ንፁሃን ሰለባ እንዳይሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረገ መሆኑን መግለፁ አይዘነጋም።

በከተማው አንድ ወጣት እጁን ወደ ኃላ ታስሮ የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ እና ባለሰቡ አካላት በጥይት ሲደብደብ የሚያሳይ ቪድዮ መሰራጨቱ በርካቶችን አስዝኖም አቆጥቶም ነበር ፤ ይህን ተከትሎ ክልሉ በሰጠው መግለጫ ይህንን ጉዳይ በግልፅ አፍረጥርጦ ባይናገርም ከህግ ውጪ የሆነ ድርጊት የፈፀሙና የስነ- ምግባር ጉድለት ያለባቸው የፀጥታ አካላት እንዳሉ አረጋግጦ ህጋዊ እርምጃ መዉሰድ መጀመሩን አስታውቆ ነበር።

ትላንት ሪፖርተር ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ ደግሞ ክልሉ አንድ ወጣት በጥይት የመደብደቡን ክስተት አረጋግጦ ፤ ከሕግ ውጪ ግድያ በፈጸሙ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ዕርምጃ ተወስዷል ብሏል።

የጋምቤላ ክልል ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡጉት አዲንግ " የኦነግ ሸኔና የጋምቤላ ነፃ አውጪ ቡድን አባላት ለይቶ ሕጋዊ ዕርምጃ የመውሰዱ ጥረት ፈታኝ ነበር " ያሉ ሲሆን " በዚህ የተነሳ ጥንቃቄ ሳያደርጉ ወይም በእልህና በቁጣ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ዕርምጃ የወሰዱ የፀጥታ አስከባሪዎች ነበሩ " ብለዋል።

#አንድ የልዩ ኃይልና #አንድ የመደበኛ ፖሊስን ጨምሮ ሁለት የፀጥታ አስከባሪዎች በሕገወጥ ግድያ ተጠርጥረው ተይዘዋል ሲሉ አሳውቀዋል።

ጥቃት የከፈቱት ታጣቂዎች ሲቭልም የለበሱ ስለነበሩ እንዲሁም አንዳንዶቹ የትጥቅ ልብሳቸው ቀይረው ከህብረተሰቡ ጋር መቀላቀላቸው ሁኔታዎች ፈታኝ አድርጎት እንደነበርም ለጋዜጣው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለግል_መገልገያ_እንዲውሉ_ወደ_አገር_የሚገቡ_ወይም_ከአገር_የሚወጡ_ዕቃዎችን_ለመወሰን_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር.PDF
ለግል መገልገያ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው የሚገቡ ዕቃዎች የትኞቹ ናቸው ?

- ሲጋራ | መለኪያ ➤ ግራም |  የሚፈቀደው መጠን ➤ 200

- ሲጋር | መለኪያ ➤ በቁጥር |  የሚፈቀደው መጠን ➤ 20

- ብትን ትንባሆ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 250

- የአልኮል መጠጥ | መለኪያ ➤ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 2

- ለስላሳ ሽቶ | መለኪያ ➤ ሚሊ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 500

- ሽቶ | መለኪያ ➤ ሚሊ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 500

- #ሞባይል | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 2 (#ሁለት)

- #ላፕቶፕ | መለኪያ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን 1 (#አንድ)

- #የፎቶግራፍ_ካሜራ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- #ዊልቸር | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- #የእጅ_ሰዓት | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- የፂም ወይም የፀጉር መላጫ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- የፀጉር ማድረቂያ | መለኪያ ➤ በቁጥር |  የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- የፀጉር መተኮሻ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- መንገደኛው የሚጠቀምባቸው መድሃኒቶች እና የህክምና በቁጥር መገልገያዎች | መለኪያ ➤በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ ለአንድ ሰው በሚያስፈልግ መመጠን

- በጉዞ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውሉ እና ለቤተሰብ የሚያገለግሉ ፣ ልብሦች፣ ጫማዎች፣ እና የፅዳት እቃዎች | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ ለአንድ ቤተሰብ ከሚያስፈልገው ያልበለጠ

የተሻሻለው የግል መገልገያ እቃዎች - የጉምሩክ መመሪያ https://t.iss.one/tikvahethiopia/73728

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢትዮጵያ ከፍላዋለች ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል " - ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ

በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እህት የሆነችው ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ አሁን ላይ በስደት #በካናዳ_ሀገር የምትገኝ ሲሆን የወንድሟን ህልፈት በሰማችበት ወቅት እራሷን ስታ ሆስፒታል እንደነበረች ተናግራለች።

ድምፃዊት ትዕግስት ፤ የወንድሟን ህልፈት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ላሳየው ልዩ ክብር ምስጋናዋን አቅርባለች።

ወንድሟን እስላም ፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው አንድም ሳይለያይ አልቆሶ በክብር መቀበሩን የገለፀችው ትዕግስት ባየችው ነገር እንደተፅናናች ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እየጠፋ ያለው የሰው ህይወት ይቆም ዘንድና ሁሉም ወደ ፍቅር እንዲመለስ እያለቀሰች ተማፅናለች።

ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፦

" ... ወንድሜን ኢትዮጵያ ከፍላዋለች። እግዚአብሔር ይመስገን የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት አክብሮታል።

እንደ ንጉስ በክብር ተቀብሯል።

ፌንት አድርጌ ሆስፒታል ነበርኩኝ ፤ ወንድሜ ለኔ ልጄ ነው ፤ የስደት ጓዴ ነው፤ ሁሉ ነገሬ ነው። የጀግና ሞት ነው የሞተው፤ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው።

የማስተላልፈው መልዕክት ፤ ወንድሜ እንዲሁ እንደ ንጉስ እንደተቀበረ  ፤ #ኢትዮጵያን እንዳለ እንደዘፈነ ፤ ኢትዮጵያን እንደወደደ የክብር ሞት ነው የሞተው የኢትዮጵያ ህዝብም ብድሩን መልሶለታል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ፤ ኢትዮጵያን ሰላም ያድርጋት።

ነገር ግን አንድ የሚያመኝ ነገር ወንድሜ እንዲህ እንደ ንጉስ ተከብሮ ተቀብሮ እንዲህ አንጀቴ ፣ ልቤ የተቆረጠ ፤ የሚያልቀው ህዝብ ፣ ምንም በማያውቀው ፣ ደጉ ባለሀገሩ ፣ ምስኪኑ የሚጨፈጨፈውስ ... ስለነሱ ነው መልዕክቴ።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደድሯችን #አንድ ልንሆን ይገባል፤ ሞት ሊቆም ይገባል። እኔ ወንድሜ በክብር ተቀብሮ እንደዚህ ያመመኝ ተዋግቶ በማያውቀው ተጋድሎ የሚሞተው ህዝብ ፤ ለእሱ ህዝብ ሞት ሊቆም ይገባል ነው መልዕክቴ።

ወንድሜማ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው ግን እንደዛም ሆኖ አንጀቴ ተቆርጧል። ማዲንጎ ኢትዮጵያን ነው ያሳየው እስላም፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው ሁሉ አልቅሶ ነው የቀበረው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግ ህዝብ ነው።

እባካችሁ ወገኖቼ ፣ ወንድሜ እንዲህ በክብር ተቀብሮ እንኳን አዝኛለሁ አንጀቴ ተቆርጧል፤ እያየች ልጇ የሚገደልባት እናት አባት ፣ እህት ወንድም የሚያልቅው እባካችሁ ... እባካችሁ ሞት ይቁም ኢትዮጵያ ላይ ፤ እግዚአብሔርን አምላክን ፍሩ ፤ ሁላችንም እንፍራ ወደ ፍቅር እንምጣ።

ማዲንጎ ይጠበቃል ዱብእዳ ነው የሆነብኝ፤ ቀኝ እጄ ነው የተቆረጠው ... በሰው ሀገር ፌንት ነው ያደረኩት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ አፅናናኝ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንደዛ ሲሆንለት ሳይ ፣ ህዝቡ እንደዛ ሲወጣ አንድ አደረጋት ፣ #አንድ_ናት_ኢትዮጵያ እያለ ዘፍኖ ቀብሩ ላይ እስላም ፤ ክርስቲያን ሳይል ሁሉም አንድ ሆኖ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ አንድ ሆኖ ነው አልቅሶ የቀበረው እናም ይሄ ህዝብ ፍቅር ነው የሚያስፈልገው ፤ ለእሱ ስንል መታሰቢያነቱ ለወንድሜ ይሁን አንድ ያድርገን እባካችሁ ፤ #ሞት_ይብቃን !! "

(ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፤ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ላይ ለሚሰራጨው " ታዲያስ አዲስ " ለተሰኘው የሬድዮ ዝግጅት ከሰጠችው ቃል የተወሰደ)

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በዝርፊያ ምክንያት ኃይል ተቋርጧል።

ከጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ወደ ጃዊ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች #በሌቦች በመፈታታቸው ኃይል መቋረጡ ተገልጿል።

ይህንን ያሳወቀው የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ነው።

ዝርፊያው የተፈፀመው አይማ ገብርኤል ቀበሌ ጌሾ ወንዝ አካባቢ ነው።

ሦስት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች በሌባ በመፈታታታቸው የወደቁ ሲሆን አንድ ተጨማሪ ምሰሶ በመሳሳብ ጉዳት ደርሶበት ወድቋል።

በዚህ የተነሳ ፦ ለበለስ ስኳር ፕሮጅክት፤ ለጃዊና አካባቢው የሚሰጠው የጃዊ ኤሌትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ ከጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጧል።

የወደቁትን ምሰሶዎች ለመጠገን የቴክኒክ ቡድን በሥፍራው ደርሶ ጥገና የጀመረ ሲሆን ጥገናውን ለማጠናቀቅ እስከ #አንድ_ሳምንት ሊፈጅ ይችላል ተብሏል።

ህብረተሰቡ የደረሰ ጉዳት እስኪጠገን በትዕግስት እንዲጠብቅ ዘራፊዎችን ለፀጥታ አካላት እንዲጠቁም ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethiopia