#አርሲ_ሮቤ
በአርሲ ሮቤ ከተማ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ከደቂቃዎች በፊት በላኩልን መልዕክት ትላንት የተፈጠረው ውጥረት መብረዱን ገልፀዋል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ተልከው እስኪመጡ ከ7 እስከ 12 ሰአት ድረስ ከተማዋ ጥሩ ሁኔታ ውስጥ እንዳልነበረችም አስታውሰዋል። በዛሬው ዕለት ከዞን የተወከሉ የመንግስት ተወካዮች ህዝቡን እያወያዩ ነው ብለዋል። ትላንት መነሻው ባንዲራ ሆኖ ሳለ ወደ ሃይማኖት አለመግባባት ለማዛመት ተሞክሮ ነበር የሚሉት የቤተሰባችን አባላት የደመራው ስነ ስርዓት መንግስት የፖሊስ ኃይል ጨምሮ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እንዲከበር ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ሮቤ ከተማ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በተከሰተው የሰላም ችግር ዙሪያ ከሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት ተካሂዷል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም የተፈጠረው የሰላም ችግር የሃይማኖት አይደለም ብለዋል።
ከዚህ በፊትም ከአሁንም፤ ከዚህ በኃላም እኛ አንድላይ ነው የምንኖረው፤ ስለዚህ እምነትን ምክንያት በማድረግ የፖለቲካ አመለካከትን ሲያንፀባርቁ የነበሩ አካላት በህግ ይጠየቁልን ሲሉ ተናግረዋል።
በስብሰባው ላይ የተገኙት የODP ሃላፊ እንደተናገሩት ከትላንት በስቲያ የተካሄደውና የተፈፀመው ነገር ሆን ተብሎ እንደሆነና፤ በዓሉን የሚያከብሩ ሰዎች ህጋዊ ባንዲራዎችን በመጠቀም በዓሉን ማክበር እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ውጪ ግን ሌሎች ያልተፈቀዱ እና እውቅና የሌላቸው ባንዲራዎችን መጠቀም ተገቢ አይደለም የተከለከለም ነው ሲሉ አሳስበዋል። እምነትን ተገን አድርገው የማህበረሰቡን ሰላም የሚበጠብጡ አካላትን ለህግ እናቀርባለን ብለዋል የODP ተወካዩ። የኦሮሞ ህዝብም ከብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለውን ሰላም እንዲጠብቅም መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።