TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ብቻዬን ብቀር እንኳ #ትግሌን እቀጥላለሁ" ጃል መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ
.
.
በመንግሥትና በኦነግ መካከል በሽማግሌዎች አማካይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ በርካታ የግንባሩ አባላት ተሰማርተው ከነበሩባቸው ቦታዎች #በሰላም እየተመለሱ ቢሆንም በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ኃይል አዛዥ ግን ይህንን ለመፈፀም ዝግጁ እንዳልሆነ ገልጿል።

በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተሰማርተው የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጦር አባላት የአባገዳዎችን ጥሪ ተከትለው #ትጥቅ_ፈትተው ወደ ጦር ካምፖች ከመግባታቸው በፊት ወደተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ ማቆያ ስፍራዎች በዚህ ሳምንት እየገቡ እንደሆነ እየተዘገበ ነው።

ሽምግልናውን የመሩትና ስምምነቱ ከፍጻሜ እንዲደርስ ጥረት እያደረጉ ያሉት አባገዳዎች እና የየአካባቢዎቹ ባለስልጣናት ለውሳኔው ተገዢ በመሆን ወደተዘጋጁላቸው ስፍራዎች ከነትጥቃቸው ሲመጡ አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የአባገዳዎችን ጥሪ ተከትሎ ሁሉም የኦነግ ጦር አባላት እየተመለሱ እንዳልሆነ ከተመለሱት የኦነግ ጦር አባላት ተሰምቷል።

ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው የምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባ ወይም በትግል ስሙ በስፋት የሚታወቀው ጓድ መሮ የአባገዳዎችን ጥሪ አለመቀበሉ ነው።

በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የኦነግ ጦር አዛዥ እንደሆነ በስፋት የሚነገርለት ኩምሳ ድሪባ (መሮ) ወይም መሮን ቢቢሲ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ አነጋግሮታል። እንደተባለውም መሮ ባለው ሁኔታ ስምምነቱን ተቀብሎ ለመግባት ዝግጁ እንዳልሆነ ገልጿል።

የአባገዳዎችን ጥሪ ለመቀበል እና እርቅ ለማውረድ ዝግጁ ስለመሆኑ ሲጠየቅም "የእርቅ የተባለው ኮሚቴ እኔን በአካል አግኝተው ለማነጋገር ፍላጎት የላቸውም። ትኩረት ያደረጉት ጦሩን አንድ በአንድ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ላይ ነው" በማለት እሱም እነሱን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ይናገራል።

እንዲያውም "ጦሩን የመበታተን ዓላማ ይዘው ነው እየተንቀሳቀሱ ያሉት" ሲል ይከሳል።

የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ የእርቅ ኮሚቴውን በመደገፍ የኦነግ ጦር ጥሪውን ተቀብሎ ወደተዘጋጀለት ስፍራ እንዲሄድ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። የጦሩ መሪ መሮ የግንባሩ ሊቀመንበር ተገዢ መሆን አለመሆኑን ተጠይቆ ሲመልስ "ሊቀመንበሩ የእርቅ ኮሚቴውን ያሉት፤ 'የኦነግ ጦር የእናንተው ነው። ሂዱና አወያይታችሁ የሚሉትን ስሟቸው' ነው ያሉት" ብሏል።

ጨምሮም እንደተናገረው "እኔ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንወያይ ነው ያልኩት እንጂ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ጥቅም የለውም፤ የኦሮሞ ህዝብ መሰቃየት የለበትም ነው የምለው። እነሱ ግን የጦሩ አባላት የእጅ ስልክ ላይ እየደወሉ አንድ በአንድ ጦሩን የማፍረስ ሥራ ነው እየሰሩ የሚገኙት" ሲል ገልጸወል።

ያለው ችግር ከስር መሰረቱ ምፍትሄ አላገኘም ብሎ የሚያምነው መሮ አሁን እየተደረገ ያለው "በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ሰዎችን አንድ በአንድ የማስኮብለል ሥራ ነው። ከዚህ የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም። 95በመቶ አሁንም እንደታጠቀ ነው የሚገኘው" በማለት ተናግሯል።

"ወደፊት መራራ ትግል ማድረጋችንን እንቀጥላለን" ያለው መሮ "ብቻዬን ብቀር እንኳ #ትግል ማድረጌን እቀጥላለሁ እቅዴም ይሄው ነው" በማለት በትጥቅ ትግሉ እንደሚቀጥል ጠንከር በማለት ተናግሯል።

የቀረበውን የእርቅ ጥሪ ተቀብለው ከገቡት የኦነግ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት የግንባሩ ጦር የሞራል እና ፖለቲካ መምህር የ57 ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ አቶ #ታፈሰ_ኦላና በመሮ በኩል ያሉት ወታደሮች እየተመለሱ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል።

ጨምረውም "መሮ መመለስ አይፈልግም፤ ስልክ እየደወለ #ጸያፍ_ቃል እየተናገረን ነው። 'እጃችሁን ለአባገዳዎች እየሰጣችሁ ሰዎች ከትግላችን ዓላማ ውጪ የሆነ ተግባር እየፈጸማችሁ ነው። ታሪክ ይፋረዳችኋል' እያለ ያስጠነቅቀናል።"

አቶ ታፈሰ እንደሚሉት አሁንም በምዕራብ ኦሮሚያ ትዕዛዝ የሚሰጠው መሮ መሆኑንና "የኦሮሞን ምድር የጦር አውድማ ማድረግ ነው የሚፈልገው። ህዝብ ሰላም እየፈለገ እሱ ግን አሁንም ደም ማፍሰስ የሚፈልግ ከሆነ ተሳስቷል" ብለዋል።

የኦነግ የምዕራብ ኦሮሚያ ጦር አዛዥ መሮ በአባ ገዳዎች የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ የሄዱ የጦሩ አባላት ላይ ይሰነዝራል ስለተባለው ማስፈራሪያን በተመለከተ "የምን ማስፈራራት ነው። መሳሪያ ይዘን እያየናቸው እኮ ነው እየሄዱ ያሉት። ምርጫቸው ነው። ማንም ማንንም አላስፈራራም" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

መሮ ችግሩን ለመፍታትም እንደቅድመ ሁኔታ የሚጠይቀው "በደቡብ ኢትዮጵያ እና በተለያዩ ዞኖች ከሚገኙ አባላቶቻችን ጋር በቅድመ ሁኔታዎች ላይ #ውይይት ማድረግ አለብን" በማለት የሽምግልና ኮሚቴውም እንዲያወያያቸውና "አንድ በአንድ የጦሩን አባላት ማስኮብለል" ያለውን ድርጊት ማስቆም እንዳለባቸው ተናግሯል።

የእርቅ ኮሚቴው ጸኃፊ የሆነውን #ጀዋር_መሐመድ በበኩሉ የኮሚቴው አባላት በተንቀሳቀሱባቸው ስፍራዎች ሁሉ የኦነግ የጦር አመራሮችን ለማግኘት ያደረጉት ጥረት የጦሩ አመራሮች ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ሳይሳካ እንደቀረ ይናገራል።

ጃዋር ''ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ የተጓዙት አቶ በቀለ ገርባ እና አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ያደረጉት ሙከራ #አልተሳካላቸውም። ወደ ደቡብ ኦሮሚያ የሄድኩት ደግሞ እኔ ነበርኩኝ። የኦነግ የምዕራብ ዞን የጦር ኃላፊ ሊያገኘን ፍቃደኛ #አልነበረም።'' ሲል ተናግሯል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia