TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD🇪🇹

" የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ ነው ፤ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ ፥ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌ/ጀኔራል ደስታ " ሠራዊቱ የተሠጠውን ተልኮ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት መፈፀም በመቻሉ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ ግብአቶች በሰላም ተጓጉዘው እንዲደርሱ እና ሰራተኞችም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል " ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ #3ኛውን_የውሃ_ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ሌ/ጀኔራሉ " የግድቡ ግንባታ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ በትኩረት እየሰራ ነው " ብለዋል።

አክለውም " የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ ዕድገታችንን ለማደናቀፍ #ከሱዳን ሰርገው የሚገቡ ኃይሎችን እየተከታተለ ሴራቸውን እያከሽፈው ይገኛል ፤ በቀጣይም ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ሲቪል አመራሮች ጋር ተቀናጅቶ ግዳጁን በአስተማማኝ ለመወጣት ዝግጁነቱ የላቀ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#FDRE_Defense_Force🇪🇹

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia