TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዋሽ ወይን አክሲዮን ማኅበር በ2 ሚሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሰርቶ አጠናቀቀ!

የአዋሽ ወይን አክሲዮን ማኅበር የምርት አቅሙን በሦስት እጥፍ ያሳድጋል የተባለለትን የማስፋፊያ ፕሮጀክት በ2 ሚሊዮን ዶላር ገንብቶ አጠናቀቀ። በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ በሚገኘው የመጥመቂያ ፋብሪካ የተገነባው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም ፋብሪካው በአመት ሲመርተው የነበረውን የ6 ሚሊየን ሊትር ወደ 30 ሚሊዮን ሊትር የሚያሳድግ ሲሆን ከቻይና፤ ጀርመን እና ጣሊያን በተገኙ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀ መሆኑ ተገጾል። በቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎችን ለመስራት 1 ሚሊየን ዶላር በጀት መያዙን በተጨማሪም ለማህበራዊ ስራዎች ከ 15 ሚሊየን ብር መመደቡን አሳዉቀዋል፡፡የአልኮል መጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ዳንኪራ የተሰኘ አዲስ ምርት ለገበያ አቅርቧል፡፡

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን 950 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የጉደር ፋጦ ወንዝ ላይ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል። ኮርፖሬሽኑ ከውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመስኖ ልማት ኮሚሽን ጋር ተፈራርሞ ሥራ ሊጀምር መሆኑን ነው የገለጸው።

ከአዲስ አበባ በ150 ኪሎ ሜትር ርቆ ኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ልዩ ስሙ መልኬ ዴራ ቀበሌ ውስጥ በፋጦ ወንዝ ላይ የሚገነባው የጉደር ፋጦ ግድብ በሶስት ዓመታት ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን፣ በአካባቢው ላለው ማህበረሰብ እንዲሁም፣ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፆ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ግድቡ፣ 283 ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር ቁመት የሚኖረው ሲሆን፣ 57.7 ሚሊየን ሜትር ኩብ ውሀ ማጠራቀም ይችላል። በወንዙ የቀኝ ጎን በኩል 4 ሺህ 972 ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት አቅም ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስኳር ኮርፖሬሽን ምንም ያወጣሁት የአክሲዮን ሽያጭ የለም አለ!

የኢፌዲሪ ስኳር ኮርፖሬሽን በመንግሥትም ሆነ በኮርፖሬሽኑ በኩል ምንም አይነት ለሽያጭ የወጣ የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የአክስዮን ሽያጭ አለመኖሩን አስታወቀ። ኮርፖሬሽኑ እንዳስታወቀው ‹‹ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር›› የተባለ ኩባንያ በመገናኛ ብዙኃን ከሚያስነግረው ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ በኅብረተሰቡ ዘንድ ኮርፖሬሽኑ አክስዮን እንደሸጠ ተደርጎ ብዥታ በመፈጠሩ እና ይህንም ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች ወደ ኮርፖሬሽኑ በመምጣት አላስፈላጊ ጫና እየተፈጠረበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይህን መግለጫ ለመስጠት እንደተገደደ አስታውቋል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
10ቱ የኤች አይ ቪ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ የሚታይባቸው የኢትዮጵይ ክፍሎች!

ኤች አይቪ ኤድስ ዳግም ተቀስቅሶ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሆንና ሽፋን ማግኘት ከጀመረ ውሎ አድሯል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተካሄደ አገራዊ የኤችአይቪ መከላከል ጉባኤ የቀረበ አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚያስረዳው ታድያ ስርጭቱ በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን አዲስ አበባም ደረጃውን ትከተላለች። ስርጭቱ ዝቅተኛ ሆኖ የጠመዘገበው በሱማሌ ክልል ሲሆን ይህም በመቶኛ 0.2 ነው።

ጥናቱ በተጨማሪ በየዓመቱ 15 ሺህ ሰዎች እንደ አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙና በኤድስ ምክንያ የሚሞቱ ናቸው። በኢትዮጵያም በተለይ ከ2010 ጀምሮ ስርጭቱ መቀነስን እያሳየ እንዳልሆነ ጥናቱ አካትቷል። ጥናቱ በኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት የተሠራውን ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ተኮር ጥናት ዋቢ አድርጎ እንደጠቀሰው፤ ኤችአይቪ በሴተኛ አዳሪዎች ያለው ስርጭት በጣም ከፍተኛ ሲሆን የሥርጭት መጠኑም 23% ነው።

ይህም ሆኖ በድምሩ በኤች አይቪ ምክያጥ የሚከሰት የሞት ቁጥር ቀንሷል። በተለይም እኤአ በ2004 የፀረ-ኤችአይቪ ሕክምና ከመጀመሩ በፊት ደርሶ ከነበረበት 83,000 እአአ በ2017 15,539 በመውረድ በ82 በመቶ መቀነሱ ይጠቀሳል። በጥቅሉም እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2017 በኤድስ ምክንያት የሚከሰት የሞት መጠንን በ57% መቀነስ መቻሉ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በ2030 የተቀመጠውን ግብ መድረስ የሚያስችል ነው።

አሁንም ግን በአዋቂም ሆነ በወጣትነት ዕድሜ ክልል ባለው የማህበረሰብ ክፍል ኤችአይቪን ለመከላከልና አገልግሎቶችን ለመጠቀም የሚያስችል የግንዛቤና የባህሪ ለውጥ ምጣኔ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ በጥናቱ ታይቷል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው። በየዓመቱ የሚካሔደው እና ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ የሚደረገው ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተባባሪ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሔዳል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለ10 ቀናት ሥራ ማቆሙ ተገለጸ!

የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት አስር ቀናት ያህል ሥራ የተቋረጠ ሲሆን አንድ ድርጅት የጄነሬተር ኃይል በመጠቀም ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል።

የፓርኩ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ መሐመድ ሃጂ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ፓርኩ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኘው ከአዋሽ መልካሳ የኃይል ማመንጫ ሲሆን፣ ለፓርኩ ኃይል የሚያቀብለው ትራንስፎርመር በመቃጠሉ ምክንያት ሥራቸው መስተጓጎሉን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሰኞ ነሐሴ 20/2011 አዲስ ትራንስፎርመር ተገዝቶ ወደ አዋሽ መልካሳ መላኩን የነገሩን መሐመድ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ጥገናው ተጠናቆ የኃይሉ ችግር እንደሚቀረፍ ተናግረዋል።

በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ለችግር የተጋለጠው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ አለመሆኑን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኮንን ኃይሉ ገልጸዋል። ብዙዎቹ ፓርኮች ሥራቸውን ባቀዱት መጠን እንዳይሠሩ የኃይል መቆራረጡ እቅፋት እንደሆነባቸውም ኃላፊው ተናግረዋል።

#AddisMaleda

https://telegra.ph/ETH-09-02
#update የተለያዩ 17 የዓለም አገራት ዜግነት ያላቸው 80 የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በ2011 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ በቁጥጥር ሥር መያዛቸውን የፌደራል ፖሊስ የፀረ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ግብረ ኃይል አስታውቋል።

Via #ADDISMALEDA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እና በራስ ዳሽን ተራራ ላይ ብቻ የሚገኘው ብርቅዬው የዱር እንስሳ ዋልያ ከመጥፋት ስጋት በመውጣት ወደ ዘጠኝ መቶ ከፍ አለ። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ ከ 15 ዓመት በፊት የዋልያዎቹ ቁጥር ወደ 150 ማሽቆልቆሉን ተከትሎ በአደጋ መዝገብ ውስጥ እንዲገባ አድርጎ የነበረ ቢሆንም በ2010 ከፍተኛ የሚባል የቁጥር እድገት በመታየቱ በድጋሚ የቋሚ ቅርስ መዝገብ ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ ይታወሳል። ፓርኩ በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበበት ጊዜ አንስቶ በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ የዋልያዎቹን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ተችሏል ሲሉ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለስልጣን የብሔራዊ ፓርኮች መጠለያና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገብረመስቀል ግዛው ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ከተለያየ የዓለም ክፍል የተወጣጡ እና በተባበሩት መንግሥታት መሪነት አዲስ አበባ ላይ ውይይት እያደረጉ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ የአፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence) ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል!"

ሐሰን ጃበር የተባሉ ሊባኖሳዊ የንግድ ሰው በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀናት ትራንዚት በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ታግተው እንደተወሰዱ እና የደረሱበት እንዳልታወቀ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

በዕለቱ ከአፍሪካዊቷ አገር ጋቦን በመነሳት በአዲስ አበባ አድርገው ወደ ሊባኖስ ቤሩት በማምራት ላይ የነበሩት ሐሰን አዲስ አበባ ደርሰው ቀጣዩ ጉዟቸውን ለማድረግ በሚሰናዱበት ወቅት ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ዕገታ እንደተፈፀመባቸው እና ሊሰወሩ እንደቻሉ የተገለፀው። የግለሰቡ ቤተሰቦች ከሊባኖስ ጋዜጣ አል አክበር ጋር ባደረጉት ቆይታ ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ግለሰቡ ከዓመታት በፊት በፈረንጆች 2017 ከሒዝቦላህ ጋር ግንኙነት አለው በሚል በጋቦን የፀጥታ አካላት ምርመራ የተደረገባቸው መሆኑን አውስቷል። ይሁን እንጂ ሐሰን ከሒዝቦላህ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት ሊባኖሳዊው ግለሰብ የት እና በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ነገር የለም። ስለጉዳዩ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የሊባኖስ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኩል የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በጉዳዩ ላይ ግልፅ ምላሽ እስከ መጪው ሰኞ መስከረም 5/2012 ድረስ እንዲሰጥበት አሳስበዋል። ካልሆነ ግን ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የሊባኖስ መንግስት አስጠንቅቋል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መደመር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ”መደመር” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት አዲስ መጽሐፍ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ በአማርኛ እና በኣፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ለገበያ እንደሚውል ተሰምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር ፍልስፍና ይዘው ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ጽፈውታል የተባለው ይህ መጽሐፍ ህትመቱ የተጠናቀቀ ሲሆን ገቢው በገጠር ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ይውላል። በሦስት መቶ ብር ወይም በ 30 የአሜሪካን ዶላር ለገበያ የሚውለው ይህ መጽሐፍ 365 ገፆች ሲኖሩት በ16 ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው።

Via #ADDISMALEDA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2012 ዓመት፣ በስድስት ወራት ውስጥ 7ነጥብ7 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል። ትርፉ ከባለፈው ዓመት 6 ወራት ጋር ሲነፃፀር ተመሳሳይ እንደሆነም ተገልጿል።

#AddisMaleda
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከፍተኛ አመራሮች ትላንት እሁድ አመሻሹ ላይ ከእስር የተፈቱ ሲሆን የቀድሞው የኦነግ ጦር አዛዥ የነበሩት እና አሁን የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አብዲ ረጋሳ ግን እስካሁን ያለመፈታታቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

የፓርቲው ነባር አባል የሆኑት ለሚ ቤኛ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደተናገሩት አመራሮቹ እሁድ ማታ ታስረው ከቆዩበት በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ ከሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ የተፈቱ ሲሆን ‹‹ እንዲሁ ተለቀቁ እንጂ ዋስትናም ጥሩ አልተባሉም›› ሲሉ ተናግረዋል።

‹‹አብዲ እስካሁን ያሉበትን አናውቅም›› ያሉት ለሚ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ግዜ ጀምሮ ቤተሰብም ሆነ ጠበቃ እንዲያገኛቸው ባለመደረጉ ምክኒያት ፓርቲያቸው ስጋት እንደገባውም ገልፀዋል።

‹‹አብዲ መንግስት እና ፓርቲው ባደረገው ድርድር ከኤርትራ በሰላም ለመታገል የተመለሱ ሲሆን የኦነግ ሰራዊት ዋና አዛዥ የነበሩ ናቸው። ስለዚህ የእሳቸውን ጉዳይ በቀላሉ የምናየው አይደለም›› ሲሉ ለሚ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

More https://telegra.ph/OLF-03-02

#AddisMaleda
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthioTelecom

በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን የ4G ኤል.ቲ.ኢ አድፋንስድ አገልግሎት ተጀመረ።

ኢትዮ ቴሌኮም የ4G ኤል.ቲ.ኢ አድፋንስድ አገልግሎት በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን ማስጀመሩን በይፋ አሳውቋል።

ተቋሙ በሪጅኑ ከተሞች ፦
- አምቦ፣
- ሰበታ፣
- ቡራዩ፣
- ወሊሶ እና ሆለታ የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት ተደራሽ የሆነባቸድ ከተሞች ናቸው።

ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ አካባቢ 334 ሺህ ደምበኞች እንዳሉት ያሳወቀ ሲሆን 4G LTE አገልግሎቱ ከመደበኛው የበይነ መረብ 16 እጥፍ ይልቃል።

#AddisMaleda

@tikvahethiopia