TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁነኛ አካል

በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች ማክሰኞ ጥር 28 ቀን ከምሽቱ 2፡30 ገደማ ታጣቂዎች በካምፓሱ ውስጥ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል ሰላም ወዳለበት ግቢ እንዲቀይርላቸው ጠይቀዋል።

በኮሌጁ የጸጥታ ችግር አለ የሚል መረጃ ደርሶናል እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የኮሌጁ ሁነኛ አካል ፣ " ተማሪዎቹ የነገሯችሁ #እውነት ነው። ችግሩ ተፈጠረ፣ ግቢው ተደበደበ። ተማሪዎች ወጡ " ሲሉ አረጋግጠዋል።

በተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፤ " ተማሪዎች ላይ የደረሰ #ጉዳት የለም። ከግቢው ገቡ፣ ከዚያ ተኩስ ተጀመረ፣ ከዚያ #ቦምብ አፈነዱ፣ ጥይት ተተኮሰ " ሲሉ አስረድተው፣ " ‘ተማሪዎች መውጣት አለባችሁ የሚል ነገር ተናገሩ እነርሱ (ታጣቂዎቹ) " ብለዋል።

ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን ከግቢ መውጣት እንዳለባቸው ይህን ካላደረጉ ግን በቀጥይ እርምጃ እንደሚወስዱ እንዳስጠነቀቁ ገልጸዋል።

የሴቶች ብሎክ 1 እና 3 ሕንጻ የተወሰነ በታጣቂዎች መመታቱን የገለፁ ሲሆን " ተማሪ ግን #አልጎዱም  " ብለዋል።

" ተማሪዎች ላይ ታርጌት አላደረጉም ሕንጻውን ነው የደበደቡት። ቦምቡ ደግሞ ከተማሪዎች ወደ ካፌ መሄጃ በኩል እዚያው ከግቢው ውስጥ ፈንድቷል። የፈነዳበት ቦታ ይታወቃል " ሲሉ አክለዋል።

ተኩስ የከፈቱት ታጣቂዎች ፍላጎታቸው ምንድን ነው ? ለሚለው ጥያቄ እኚሁ ግለሰብ " ‘ዩኒቨርሲቲ በቃችሁ፣ ከመጀመሪያውስ ለምን መጣችሁ?’ እያሉ ሲናገሩ ነበር " ያሉ ሲሆን " ‘አሁንም ግቢውን ለቃችሁ ውጡ። ዛሬ አንጎዳችሁም። ቀጣይ ግን ስንመጣ ብናገኛችሁ ቀጥታ እርምጃ እንወስዳለን’ የሚል እንድምታ ነበር ብለዋል።

በግቢው አጠቃላይ ከ1,500 እስከ 2,000 ተማሪ የሚገኝበት ሲሆን ከትላንት ጠዋት ጀምሮ #አብዛኞቹ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል።

" ወደ ቤት የሚሄዱ አሉ (ምክንያቱም በጣም ጭንቅ ነበር በተለይ ሴቶች፣ ሌሊትም #ሲያለቅሱ ነበር) ዘመድ ጋ ወደ ከተማ የሚጠጉም አሉ። #ሆቴል ይዘው ያደሩ ልጆችም አሉ። ቤተሰብ ሩቅ የሆነባቸው፣ ገንዘብ የሌላቸው ተማሪዎች አሉ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለው በጭንቀት " ሲሉ የሁኔታውን አሳሳቢነት አስረድተዋል።

ታጣቂዎቹ ወደ ካምፓሱ ሲገቡ ጥበቃዎች አልነበሩም ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ ፣ " የእኛ ካምፓስ አዲስ ስለሆነ አጥር የለውም። በዙሪያው ጥበቃዎች አሉ። ግን ጥበቃዎች በኮማንድ ፓስቱ ምክንያት መሣሪያ አይዙም። መሣሪያ ቢይዙም የመጣው ኃይል በጣም ብዙ ነው " ብለዋል።

የተማሪዎቹ ፍላጎትስ ምንድነው ? ለሚለው ጥያቄም፣ " ተማሪዎች መማር ይፈልጋሉ። ምክንያቱም በኮሮና ጊዜ፣ በጦርነት ምክንያት አማራ ክልል ላይ ብዙ ታሹ። አብዛኛው ተማሪ መማር ይፈልጋል፣ ግን ደግሞ ከሕይወት የሚበልጥ ነገር የለም " የሚል ምላሽ ተሰጥተዋል።

የካምፓሱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ ረቡዕ ጥር 29 ቀን 2016 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ እንደነበራቸው፣ በዚህም " በጥበቃ (በመከላከያ) ተጠብቀው ይማሩ ወይስ ሌላ ግቢ እናመቻችላቸው ? " በሚለው ጉዳይ እንደተወያዩና ውሳኔው ግን እንዳልታወቀ ተመላክቷል።

መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia