TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንድማማችነት ከባንዲራ በላይ ነው⬇️

በሀገራችን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እና ትዉልድ መስዋዕትነት የከፈለበትን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እዉን ለማድረግ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ ሂደትም በሀገራችን የዴሞክራሲ ምህዳር ከመጥበቡ የተነሳ የትጥቅ ትግልን ለማራመድ ተገድደዉ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ትግል ለማድረግ የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወደ ሀገር በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

በተፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ላይ የሚገኙትን የፖለቲካ ድርጅቶችንም ሆነ ግለሰቦች ደጋፊዎቻችዉ እና አድናቂዎቻቸዉ የተለያዩ ዓርማዎች፣ #ባንዲራ እና ምልክቶችን በመያዝ አቀባበል እያደረጉ፣ ድጋፋቸዉን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

በነዚህ የአቀባበል እና የድጋፍ ሂደቶች ማንኛዉም ሰዉ የመሰለዉን ዓርማ፣ ባንዲራ ወይም ምልክት ይዞ አቀባበል ወይም ድጋፍ ቢያደርግ የሌላዉን ዜጋ መብት እስካልተጋፋ ድረስ ምንም ችግር የለዉም። ዴሞክራሲያዊ መብትም ነዉ!

#ነገር_ግን አሁን አሁን በድጋፍ እና በአቀባበል ወቅት የሚያዙ ባንዲራዎች እና ምልክቶች #የልዩነት እና የዉዝግብ እልፎም #የግጭት መነሻ እየሆኑ እንደመጡ እያስተዋልን ነዉ። ይህ ሁኔታ ከባንዲራ፣ አርማ እና ምልክቶች ጋር ተያይዞ መግባባት ለመፍጠር ሰፊ ስራ መስራት እንዳለብን ያመላክተናል። ሁኔታዉ በቶሎ መስመር እንዲይዝ ካልተደረገም ለግጭት ነጋዴዎች ቶምቦላ ሎተሪ ይሆንላቸዋል።

ትግላችንም ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለመገንባት ከሚደረግ ወሳኝ ትግል ወደ ዓርማ እና ባንዲራ ፉክክር እና ንትርክ ብሎም ግጭት ዝቅ ሊል ይችላል። እንደዚህ አይነቱ ሂደት ደግሞ ከማንም በላይ የግጭት ነጋዴዎችን የሚጠቅም ይሆናል።

ትግላችን #ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት የሰፈነባት #ዴሞክራሲያዊት ሀገር መገንባት እንደሆነ ሁሉም የለዉጥ ደጋፊ ሊያሰምርበት ይገባል።

በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ልዩነትን ከሚያጎሉና ወደ ግጭት ሊያመሩ ከሚችሉ ጉዳዮች ይልቅ አንድነትን ሊያጠናክሩ #ሰላምና #መተጋገዝን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ማትኮር ወሳኝ ይሆናል። ይህ ካልሆነ ግን በጠንካራ ክንድ ትግሉን ወደ ስኬት ከማንደርደር ይልቅ በባንዲራ፥ በአርማ እና በትናንት ታሪካችን ተፈጥረዉ በነበሩ ድክመቶችንና ትናንሽ የልዩነት ነጥቦች ላይ ንትርክ ዉስጥ ለመግባት ያስገድደናል። እንደዚህ አይነት ጠቃሚ ያልሆነ ዉዝግብ አንድነታችንን ይፈታተናል። ጠንካራ የትግል ክንዳችንን ያዝላል። ለሽንፈትና ለዉርደትም ይዳርገናል።

ስለሆነም የትግልና የድል ጉዞአችን እንዳይገታ ከልዩነቶቻችን ይልቅ አንድ በሚያደርጉን ነገሮች ላይ አትኩረን እንሻገር። ከተሻገርን በሗላ በልዩነቶቻችን ዙሪያ በሰከነ እና በሰለጠነ አግባብ ተወያይተን መፍታት እንችላለን።

ነፃነት፣ ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ!

©አቶ አዲሱ አረጋ(OPDO)
@tsegabwolde @tikvahethiopia